በፌዴሬሽኑ ምርጫ ዶክተር አሸብር ራሳቸውን ሲያገሉ፤ ትግራይ ተወካዩን አንስቷል

Wednesday, 23 May 2018 14:43

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራሮች ምርጫ ድራማ አሁንም እንደቀጠለ ነው።

ለፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትነት የደቡብ ክልልን በመወከል ቀርበው ሲፎካከሩ የነበሩት ዶክተር አሸብር ወልደጊርጊስ ባልተጠበቀ ሁኔታ ራሳቸውን ከፉክክር ሲያገሉ፤ ትግራይ ክልል ደግሞ ተወካዩን አቶ አንስቷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ምርጫ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰ ይመስላል። በአዲስ ሁኔታ እንዲመረጥ የተደረገው የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አስመራጭ ኮሚቴው እጩዎቹን በይፋ ከማሳወቁ በፊት ባልተጠበቀ ሁኔታ ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ከፕሬዝዳንታዊ ፉክክር ራሳቸውን ማግለላቸውን ይፋ አድርገዋል። የትግራይ ክልል ደግሞ በእጩነት አቅርቦ የነበረውን ውክልና አንስቻለሁ ሲል መግለጫ ልኳል።

ዶክተር አሸብር በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ ላይ እንዳስታወቁት ከሆነ በራሳቸው ፍላጎት ከፉክክሩ ለመውጣት መወሰናቸውን ነው የተናገሩት። ውሳኔያቸውም የማንም ተጽዕኖ የሌለበት መሆኑን ነው የገለጹት። ይልቁንም ‹‹ለሀገሬ ክብር ስል የደረስኩበት ውሳኔ ነው›› ብለዋል።

‹‹እኔ እጩ ሆኜ በምርጫው እለት ብገኝ ምርጫው ሁሉ ላይካሔድ ይችላል የሚል ስጋት ስላደረብኝና የሀገራችን ገጽታ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እየጠፋ መሄዱ ስላሚያሳስበኝ ራሴን ከምርጫው ለማግለል ወስኛለሁ›› ሲሉ ምክንያታቸውን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ከሚመረጠው ማንኛውም ግለሰብ ጋር በእግር ኳሱ ላይ ተባብረው ለመስራት ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የደቡብ ክልልን በመወከል የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት በቦታ በመያዝ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር በድጋሚ ወደ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለመምጣት መወሰናቸው ከፍተኛ ውዝግብ ማስታናገዱ ይታወቃል።

ፕሬዝዳንታዊ ምርጫውን እንደሚያሸንፉ በተደጋጋሚ ሲናገሩ የነበሩት ዶክተር አሸብር አሁን ላይ ደግሞ ከፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ለማግለል መወሰናቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

ከምርጫው ጋር በተያያዘ መረጃ የትግራይ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫው በእጩነት ያቀረባቸውን አቶ ተስፋይ ካህሳይ ውክልናን ማንሳቱን ሰኞ እለት አስታውቋል። ክልሉ ግለሰቡን ስላላመንባቸው ነው ከማለት ውጪ ውክልናውን ያነሳበትን ምክንያት አላሳወቀም።

በፕሬዝዳታዊ ምርጫው ከፍተኛ ተፎካካሪ የነበሩት ዶክተር አሸብር አለመኖር ፉክክሩ በአቶ ጁነዲን ባሻ እና አቶ ተካ አስፋው መካከል እንደሚሆን ይጠበቃል። አቶ ጁነዲን ባሻ ፌዴሬሽኑን ላለፉት አራት አመት በፕሬዝዳንትነት የመሩ ሲሆን፤ በድጋሚ በኃላፊነታቸው ለመቀጠል ድሬዳዋ አስተዳደርን ወክለው በእጩነት ቀርበዋል።

በአቶ ጁነዲን የአስተዳደር ዘመን በእግር ኳሱም ሆነ በአመራር ስኬታማ የሚባል ጊዜን አላሳለፉም። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጤት የራቀውና የውስጥ ውድድሮችም በሁከት የታጀቡና ችግሮች የማይጠፋቸው ሆነዋል።

አቶ ተካ አስፋው በቀደመው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማገልገላቸው ይታወሳል። በእርሳቸው የአመራር ዘመን የነበረው ስራ አስፈጻሚ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2013 የአፍሪካ ዋንጫ ያለፈበትና ፌዴሬሽኑ በገንዘብና በሀብት ጠንካራ አቅም እንዲኖረው ማስቻሉ በስኬት ከሚጠቀሱለት ታሪኮች መካከል ናቸው።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
44 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 665 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us