ጥሩነሽ ዲባባ በማንቸስተር የ10 ኪ.ሜ. ሩጫን አሸነፈች

Wednesday, 23 May 2018 14:45

 

በእንግሊዝ የንጉሳውያን ቤተሰብ የሰርግ ስነ ስርአት መነጋገሪያ በሆነበት የሳምንት መጨረሻ ቀን በተካሔደው የማንቸስተር ግሬት ረን ጥሩነሽ ዲባባ ድል አስመዝግባለች። በወንዶች ሞ ፋራህ ቀዳሚ ሆኗል።

ከሁለት ወራት በፊት እንግሊዝ በተዘጋጀው የለንደን ማራቶን ላይ ሩጫዋን አቋርጣ የወጣችው ጥሩነሽ፤ እሁድ እለት በሀገሪቱ በተካሔደው የማንቸስተር ግሬት ረን የ10 ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫን በበላይነት አጠናቃለች። ጥሩነሽ ርቀቱን በ31፡08 በማጠናቀቅ ነው ያሸነፈችው። በውድድሩ መድረክም ለአምስተኛ ጊዜ በማሸነፍ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የረጅም ርቀት ንጉስ ሀይሌ ገብረስላሴ ጋር እኩል ታሪክ መጋራት ችላለች።

ሀይሌ ገብረስላሴ የማንቸስተር ግሬት ረን የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን ለአምስት ጊዜ በማሸነፍ ይጠቀሳል። ቀነኒሳ በቀለ ሶስት ጊዜ ድል በማድረግ በወንዶች ከሀይሌ ቀጥሎ ብዙ ጊዜ ያሸነፈ ኢትዮጵያዊ አትሌት ነው።

በዘንድሮው የ2018 የማንቸስተር ከተማ ሩጫ በሴቶች ጥሩነሽ ዲባባ ቀድማ በመግባቷ በመድረኩ ለአምስት ጊዜ ድል ያደረገች በመባል ለመጠራት ችላለች። ከጥሩነሽ በተጨማሪ ከፍተኛ ግምት የተሰጣቸው የኬንያ ሯጮች ጠንካራ ፉክክር አድርገዋል። በተለይም ደግሞ ርቀቱን ከ30 ደቂቃ በታች በማጠናቀቅ (29፡43) ብቸኛዋ ሴት አትሌት የሆነችውና የአለም የግማሽ ማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ኬንያዊቷ ጆይሲሊን ቺፕኮስጊ ጥሩነሽን በመከተል ሁለተኛ ሆና ስትገባ፤ ሌላዋ ኬንያዊት ቤትሲ ሳኒያ በ32፡25 ሶስተኛ ሆና ገብታለች።

በወንዶች መካከል የተደረገውን ፉክክር ደግሞ ሶማሊያ እንግሊዛዊው አትሌት ሞ ፋራህ በቀዳሚነት አጠናቋል። ርቀቱንም 28፡27 ነው ያጠናቀቀው። ዩጋንዳዊው ሞሰስ ኪፕሴሮ ሁለተኛ ሲሆን፤ ኬንያዊው አቤል ኪሩ ሶስተኛ ደረጃን አግኝቷል።¾

Last modified on Wednesday, 23 May 2018 14:48
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
56 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 498 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us