የወልዋሎ ክለብ የይግባኝ ውሳኔ

Wednesday, 23 May 2018 14:47

 

የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ክለብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከመከላለከያ ክለብ ጋር በነበራቸው ጨዋታ በተፈጠረ ሁከት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲስፕሊን ኮሚቴ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። የቅጣት ውሳኔውን ተከትሎም ወልዋሎ ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን፤ በአቶ ጳውሎስ ተሰማ ሰብሳቢነት የሚመራው የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የመጨረሻ የተባለ ውሳኔውን ማክሰኞ እለት ይፋ አድርጓል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አራት አባላት የሚገኙበት የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ለመገናኛ ብዙሀን በላከው መረጃ ላይ እንዳስታወቀው ከሆነ ቀደም ሲል በዳኛ እያሱ ፈንቴ ላይ ድብዳቤ በፈጸሙት የወልዋሎ የቡድን መሪ አቶ ማሩ ገብረጻድቅ ላይ ያስተላለፈውን የ200 ሺህ ብር ቅጣት ክለቡ ሳይሆን ግለሰቡ እንዲከፍሉ ብሏል። ከዚህ በተጨማሪም አቶ ማሩ ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ እንዲታገዱ ሲል የተጣለው የእድሜ ልክ ቅጣቱ ደግሞ እንዲጸና አድርጓል።

የወልዋሎ ክለብ 250 ሺህ ብር እንዲከፍልና ጨዋታውን ሶስት ግብ ተቆጥሮበት በሶስት ነጥብ እንዲሸነፍ የተላለፈው ውሳኔው ጸንቷል።

በእለቱ የዳኛ እያሱ ፈንቴን ውሳኔ በመቃወም ግብ አልተቆጠረችም ብሎ እየሮጠ ሲከታተል የነበረው የወልዋሎ ግብ ጠባቂ በረከት አማረ ላይ የተላለፈው የ10 ሺህ ብር ቅጣትና የ6 ወር እገዳ እንዲጸና ተደርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም በተጨዋች አስር አልማዲ ላይ ተላልፎ የነበረው የ6 ወር ከሜዳ እገዳ ወደ አንድ አመት፤ የ10 ሺህ ብር ቅጣቱ ወደ 20 ሺህ ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል።

በሌላ በኩል የወልዋሎን ይግባኝ ተከትሎ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ቅጣት የቀነሳባቸው ውሳኔዎችም ተላልፈዋል። ይኸውም አለምነህ ግርማ፣ ማናዬ ፋንቱ በረከት ተሰማና አፈወርቅ ሀይሉ በወቅቱ ዳኛውን በመክበብ ተቃውሞ ቢገልጹም ጥቃት አላደረሱም በሚል የተጣለባቸው የ6 ወር እገዳ እና የ10 ሺህ ብር ቅጣት ተነስቶ በከባድ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ተደርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም የወልዋሎ ተጫዋች ዋለልኝ ገብሬ ላይ የተጣለው የሁለት አመት እገዳ እና የ15 ሺህ ብር ቅጣት ወደ 5 ሺህ ብር ቅጣት እንዲቀንስና ከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፍ ተደርጓል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተሰጡትን ውሳኔዎች እንዲያስፈጽምና የተላለፉት የገንዘብ ቅጣቶችንም ገቢ መሆናቸውን ተከታትሎ ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው እንዲያቀርብ ሲል ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው አሳውቋል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
83 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 467 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us