የአርሴናል አዲሱ አሰልጣኝ ታውቀዋል

Wednesday, 23 May 2018 14:48

 

የአርሴናል እግር ኳስ ክለብን ለ22 ዓመታት ክለቡን በአሰልጣኝነት ያገለገሉት ፈረንሳዊው አርሰን ቬንገር ስንብት እርግጥ ከሆነ በኋላ የክለቡን ደጋፊዎች ሲያሳስብ የነበረው ቀጣይ ተረካቢ ጉዳይ ሰኞ እለት መቋጫ አግኝቷል። አዲሱ አሰልጣኝ የቀድሞው የፓሪሰን ዠርመን አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሪ መሆናቸውን ክለቡ አሳውቋል።

ኡናይ ኤምሬ የፓሪሱን ክለብ በ2016 ከተቀላቀሉ በኋላ ቡድኑን ለሶስት ዋንጫ ባለቤት አድርገው በዚያው አመት መሰናበታቸው ይታወሳል። አሰልጣኙ በስፔኑ ሲቪያ ክለብ ስኬታማ ጊዜ ማሳለፋቸው አይዘነጋም።

የ46 አመቱ አሰልጣኝ የመሩት የፓሪሰን ዠርመን ክለብ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በ16 ጨዋታዎች ያለመረታት ጉዞው የተገታው በሪያል ማድሪድ ነበር። በውድድር አመቱ በቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ማንሳት ባይሳካለትም ኮከብ ተጫዋቾችን በማሰባሰብ ሶስት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችን መሰብሰብ ችሏል።

አሰልጣኙ በፈረንሳዩ ክለብ ስኬታማ አመትን ቢያሳልፉም የውድድር አመቱ ሲጠናቅ የኮንትራት ስምምነታቸው በማብቃቱ ከክለቡ ጋር ውላቸውን አድሰው ከመቆየት ይልቅ መለያየትን መርጠዋል።

ኤምሬ በእንግሊዙ አርሴናል ክለብ ጋር የረዥም ጊዜ ኮንትራት እንደሚፈራረሙም ተገቷምል።¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
217 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 480 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us