ሉሲዎቹ ዛሬ አልጄሪያን ይገጥማሉ

Wednesday, 06 June 2018 14:14

ጋና ለምታስተናግደው ለ2018 የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ፉክክር ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን (ሉሲ) ዛሬ አልጄርስ ላይ የአልጄሪያን ቡድንን ይገጥማል።

በመጀመሪያው ዙር ማጣሪያ ሊቢያን በደርሶ መልስ 15 ለ 0 በሆነ በሰፊ የግብ ልዩነት ያሸነፈውና በአሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ የሚመራው የሉሲዎቹ ቡድን የአልጄሪያ ቡድንን በሜዳውና በሜዳው ፊት ይገጥማሉ። ጨዋታውም ከባድ ፉክክር እንደሚገጥማቸው ይገመታል። በጨዋታው ማሸነፍ አሊያም ግብ አስቆጥረው አቻ ነጥብ ይዞ መመለስ ለቀጣዩ የመልስ ጨዋታ የማሸነፍ እድላቸውን ሰፊ ያደርገዋል።

የአልጄሪያ ሴት ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሴኔጋልን በደርሶ መልስ አሸንፎ ወደ ሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ማለፉ ይታወሳል። ቡድኑ ሴኔጋልን በመጀመሪያ ጨዋታ በሜዳው 2ለ0 በመልሱ አሸንፎና በመልሱ ጨዋታ 2ለ1 ተሸንፎ በድምሩ 3ለ2 በመርታት ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈው።

ኢትዮጵያና የአልጄሪያ ቡድኖች ከሁለት ዓመት በፊት ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ተገናኝተው አልጄሪያ ላይ ሉሲዎቹ 1ለ0 ተሸንፈው፤ አዲስ አበባ ላይ ደግሞ 1ለ1 ነበር የተለያዩት። በደርሶ መልሱ ውጤት አልጄሪያዎች 2ለ1 አሸንፈው ሉሲዎቹን ከአፍሪካ ዋንጫ ማስቀረታቸው ይታወሳል።

በወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫው ማጣሪያ ሳይመዘገብ ቀኑ አልፎበት ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱና በመጨረሻም ከውድድሩ ራሷን ያገለለችው ቶጎን ተክቶ በማጣሪያው እንዲሳተፍ መደረጉ ይታወሳል። የአሁኑ የሉሲ ስብስብ ለረጅም ጊዜ ለውድድሩ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ከመሆኑ አንጻር በተራው አልጄሪያን ከውድድሩ በማስቀረት ብድሩን እንደሚመልስ ይጠበቃል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ዛሬ አልጄሪያ ላይ ምሽት አምስት ሰአት ላይ የሚጫወቱ ሲሆን፤ የመልስ ጨዋታቸውን እሁድ ዕለት ያደርጋሉ።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
48 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 697 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us