ጠረጴዛ ቴኒስ በኦሮሚያ እና ንግድ ባንክ፤ ቼዝ ደግሞ በአቡጊዳ የበላይነት የተጠናቀቀበት ውድድር

Wednesday, 06 June 2018 14:18

 

ባሳለፍነው ሳምንት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ሁለት የስፖርት አይነቶች ውድድር ሲካሄድባቸው ቆይቶ ቅዳሜ እና እሁድ ተጠናቀዋል።

በጠረጴዛ ቴኒስ ሲካሄድ የነበረውን ሻምፒዮና በክልሎች ኦሮሚያ በበላይነት ሲያጠናቅቅ በክለቦች ደግሞ ንግድ ባንክ አስር ዋንጫዎችን በመውሰድ የአጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል። ውድድሩን አስመልክቶ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ጌታሁን ሽፈራው ‹‹በዚህ ውድድር ካለፉት ዓመታት በተለየ ዘንድሮ የተሳታፊ ቡድኖች ማነስ የታየበት ነው። የማይሳተፉ ቡድኖች ለምን እንደማይካፈሉ ችግራቸው ታይቶ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል›› ብለዋል።

ቡድናቸው ውጤታማ የሆነበትን ምክንያት ሲያስቀምጡም ለመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ዝግጅት ላይ መቆየታቸውና በመጨረሻም የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ስለተሰረዘ ቡድኑን ለዚህ ሻምፒዮና ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። ውጤታማ የሆኑት እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሉ ጠንካራ ቡድኖች ባለመሳተፋቸው ይሆን ወይ? ተብለው የተጠየቁት አሰልጣኝ ጌታሁን ‹‹የዚህ ዓመት ዝግጅታችን ከፍተኛ ስለነበረ የትኛውም ቡድን ቢመጣ ሊያሸንፈን እንደማይችል እርግጠኛ ነበርን›› ብለዋል። ነገር ግን ይህን ስፖርት በመንግስት ሳይቀር ትኩረት የተነፈገው መሆኑ እንደሚያስከፋቸው ተናግረዋል። ለውድድርና ለስልጠና የሚስፈልጉ ግብዓቶች እና የፋይናንስ ችግር እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ …. በበኩላቸው በዚህ ዓመት የጠረጴዛ ቴኒስ ፕሪሚየር ሊግ ለመጀመር ፌዴሬሽኑ እቅድ ቢኖረውም በበጀት እጥረት (ከመንግስት ስላልተመደበላቸው) ምክንያት ውድድሩ አለመጀመሩን ተናግረዋል። ሆኖም በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ፕሮጄክቶችና ጽ/ቤቶች ስላሉት ስፖርቱ በአደረጃጀት ህዝባዊ መሰረት አለው ብለዋል።

በሌላ ዜና የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው የመጀመሪያው የክለቦች ሻምፒዮና ለስድስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ፍጻሜ ያገኘው እሁድ ነው። ኢትዮ አፍሪካ ቤዛ ኮሌጅ፣ ቴራስ ሆቴል፣ አቡጊዳ እና አዲስ ቼዝ ክለብ የተባሉ ክለቦች የተሳተፉበት ይህ የመጀመሪያው የክለቦች ሻምፒዮና በአቡጊዳ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በውድድሩ መዝጊያ የተገኙት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ጸደቀ ይሁኔ ‹‹የክለቦቹን ቁጥር ማነስ አትናቁት። የአፍሪካ ዋንጫ ሲጀመርም በሶስት አገራት ነበር›› በማለት ንግግራቸውን ማሰማት ጀምረዋል። ባለጸጋው ሰው ስለ ፌዴሬሽኑ አጠቃላይ አቅመ ቢስነት ሲናገሩም በተለይ የፋናንስ ችግር መኖሩን ገልጸው ለዚህም በጅቡቲ ለሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅም አለመኖሩንም አስታውሰዋል።

ለአቶ ጸደቀ ይሁኔ ከተሳታፊ ክለብ ተወዳዳሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ነበር። በተለይ የተሳታፊ ክለቦችን ቁጥር በተመለከተ ወደፊት አንድ የባንክ እና የኮንስትራክሽን ክለብ ተሳታፊ እንደሚሆን በልበ ሙሉነት ተናግረዋል።

ሌላው በተወዳዳሪዎች ለሰንደቅ ጋዜጣ የቀረበው ቅሬታ ‹‹ስፖርቱ ትውልድን በመቅረጽ በኩል ያለው ሚና ከፍተኛ ሆኖ ሳለ አገር ወዳድ ባለሀብቶችና መንግስት በገንዘብ ሊደግፉት አለመቻላቸው ለምን ይሆን?›› የሚል ነበር። የቼዝ ስፖርት ማዕከል የሚያደርገው በአዕምሮ እድገት ላይ ሲሆን በተለይ ህጻናት በቤትና በትምህርት ቤት ቢማሩት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም አያይዘው ተናግረዋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
41 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 544 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us