የደደቢቱ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በድንገት ከዚህ ዓለም ተለዩ

Wednesday, 06 June 2018 14:19

 

የደደቢት እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለያታቸው ተሰማ። አሰልጣኙ ለሞት የተዳረጉት ከህክምና ስህተት ጋር በተያያዘ ስለመሆኑ ምርመራ እየተካሔደ ነው።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመከላከያ፣ የወልዲያ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ደደቢት ክለቦችን በማሰልጠን የሚታወቁት አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የስፖርት ቤተሰቡን ያሳዘነ ክስተት ሆኗል። ቡድናቸውን ማሰኞ እለት ከአርባ ምንጭ ጋር ላለበት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ዝግጅት ላይ የነበሩት አሰልጣኙ ከጨጓራ በሽታ ውጪ የከፋ የጤንነት እክል እንደሌለባቸው ነው የተነገረው።

አሰልጣኙ ሰኞ እለት ማታ 6፡00 አካባቢ የከፋ የህመም ስሜት ሲሰማቸው ወደ ጎፋ ጤና ጣቢያ በማምራት ህከምና ያደረጉ ሲሆን፤ ህመሙ ፋታ ስላልሰጣቸው የተሻለ ህክምና ለማግኘት ወደ ሀሌሉያ ሆስፒታል ቢያመሩም ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግባለች።

ለረጅም ጊዜ የቆየና የጠና ህመም እንደሌለባቸው የሚገልጹት የአሰልጣኙ የቅርብ ሰዎች በድንገት ህይወታቸው ማለፉ ከህክምና ስህተት ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ይጠረጥራሉ። የአስክሬን ምርመራም በምኒሊክ ሆስፒታል የተካሔደ ቢሆንም እስከአሁን በይፋ የታወቀ ነገር የለም።

የአሰልጣኙ ስርአተ ቀብር ቤተሰቦቻቸው በሚገኙበት በማይጨው እንደሚከናወን ታውቋል። ሰንደቅ በአሰልጣኙ ድንገተኛ ሞት የተሰማትን ሐዘን እየገለጸች ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆች መጽናናትን ትመኛለች።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
86 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 543 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us