በውዝግብ የታጀበው ፌዴሬሽኑ ምርጫ በውዝግብ ተጠናቋል

Wednesday, 06 June 2018 14:21

 

ለስምንት ወራት ተጓቶ የቆየው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአመራሮች ምርጫ እሁድ ግንቦት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ መቋጫውን አግኝቷል።

አጠቃላይ የምርጫ ሒደቱና ፍጻሜውም በውዝግብ የተሞላና ፍትሐዊነት የጎደለው መሆኑን በስፍራው የነበሩ በርካታ ዘጋቢዎች መታዘብ ችለዋል። እግር ኳሱ አሁንም በእውቀት የሚያስተዳድር አመራር አለማግኘቱ የስፖርት ቤተሰቡን አሳስቧል።

በፕሬዝዳንታዊ ፉክክሩ የቀረቡት አራት እጩዎች አቶ ጁነዲን ባሻ ከድሬደዋ፣ አቶ ተካ አስፋው ከአማራ ክልል፣ አቶ ኢሳያስ ጂራ ከኦሮሚያ እና አቶ ተስፋይ ካሕሳይ ከትግራይ ክልል መሆናቸው ይታወሳል። በመጀመሪያው ዙር በተሰጠው ድምጽ መሰረትም አቶ ኢሳያስ 66፣ አቶ ተካ 47፣ አቶ ጁነዲን 28 እና አቶ ተስፋይ 3 ድምጽ አግኝተዋል። አቶ ኢሳያስ ከፍተኛ ድምጽ በማግኘታቸው ማሸነፋቸው ተገልጾ ቀጣዩ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት መሆናቸውን ተነገረ።

ይሁንና ምርጫውን ለመታዘብ በስፍራው የተገኙት የካፍና ፊፋ ታዛቢዎች አሸናፊ የሚሆነው ተወዳዳሪ በህጉ መሰረት 50 ከመቶ በላይ የመራጩን ድምጽ ማግኘት እንደሚኖርበት ነው ያስታወቁት። አቶ ኢሳያስ ደግሞ ከፍተኛ ድምጽ ቢያገኙም ከመራጩ 46 ከመቶ በመሆኑ አሸናፊ እንደማያደርጋቸው በመግለጽ ምርጫው በድጋሚ መካሔድ እንዳለበት አሳሰቡ።

ቀደም ሲል አስመራጭ ኮሚቴው አብላጫ ድምጽ ያገኘ አሸናፊ እንደሚሆን አስታውቆ ስለነበር ምርጫው ድጋሚ እንዲካሔድ የቀረበው ሀሳብ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። በውሳኔው ቅር የተሰኙ የጉባኤው አባላት አዳራሹን ጥለው ወጥተውም ነበር። በመጨረሻ በተደረገው ማግባባት አዳራሹን ጥለው የወጡትን መራጭ ጉባኤተኞች ወደ አዳራሹ እንዲገቡና ምርጫው በድጋሚ እንዲካሔድ ስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል።

በድጋሚ ምርጫውም አቶ ተስፋይ ካሕሳይ እና የድሬደዋው ተወካይ አቶ ጁነዲን ራሳቸውን ከድጋሚ ምርጫው በማግለላቸው ፉክክሩ በአቶ ተካ አስፋው እና በአቶ ኢሳያስ ጂራ መካከል ሆኗል። የድምጽ አሰጣጡ ስነ ስርአት ከተካሔደ በኋላም አቶ ኢሳያስ 87፤ አቶ ተካ ደግሞ 58 ድምጽ አግኝተዋል። አቶ ኢሳያስም ምርጫው አሸናፊነታቸው ተገልጾ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት መሆናቸው ታውጇል።

ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነትም እጩዎች ቀርበው በተካሔደው ምርጫ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ከቀረቡ እጩዎች ብቸኛዋ ሴት የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልን ወክለው የቀረቡት ወይዘሮ ሶፊያ አላሙን አመራሩን ተቀላቅለዋል።

የደደቢት እግር ኳስ ክለብ መስራችና ፕሬዝዳንት የነበሩት ኮሎኔል አወል አብዱረሂም በምክትል ፕሬዝዳንትነት ተፎካክረው የብዙሀኑን መራጭ ድምጽ በማግኘት አሸንፈዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ የነበሩት አቶ ሰውነት ቢሻውም ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ መግባት ችለዋል። አቶ አብዱረዛቅ ሀሰን፣ አቶ ኢብራሂም መሐመድ እና አቶ ቻን ጋት ኮት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ውስጥ በአባልነት መመረጣቸው ታውቋል።

በአቶ ጁነዲን ባሻ አመራር ጋር የነበሩት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ፣ አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ፣ አቶ አበበ ገላጋይ እና አቶ አሊ ሚራህ በድጋሚ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ መቀጠል የሚያስችላቸውን ድምጽ አግኝተዋል። የአፋር ክልል ተወካይ የሆኑት አቶ አሊ ሚራህ ለሶስተኛ ጊዜ በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት መቅረባቸውና መመረጣቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

በቀድሞው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ የነበሩና ስማቸው ከጥፋቶች ጋር ተያይዞ የሚነሳ ግለሰቦች በድጋሚ መመረጣቸው ምርጫው በእውቀት ላይ ተመሰረተ ነው ተብሎ ለመናገር አያስችልም። አጠቃላይ ሒደቱንም ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
51 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 536 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us