ሉሲዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆኑ

Wednesday, 13 June 2018 13:41

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከጋናው የ2018 የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ ሆነዋል። ቡድኑ በሜዳ ውሥጥ ብቃት ያላቸው ተጫዋቾችን አለማካተቱ ዋጋ አስከፍሎታል።

ከግብ ጠባቂ ጀምሮ በሁሉም የቡድኑ ክፍሎች ብቃት ያላቸው ተጫዋቾች አለመኖራቸው ቡድኑ በሜዳ ውስጥ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን አልቻለም። ጠንካራ የማይባለው የአልጄረያ ቡድን በራሱ ሜዳም ሆነ በአዲስ አበባ ስታዲየም በቀላሉ ግቦችን በማስቆጠር ማሸነፍ ችሏል። አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ እና ረዳቶቿ ለተመዘገበው ውጤት በተለይም ከተጫዋች ምርጫ ጋር በተያያዘ ሀላፊነት ሊወስዱ እንደሚገባ መናገር ይቻላል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እሁድ እለት አልጄሪያን የሚያስተናግዱትን ሉሲዎቹን ያ ተመልካች ክፍያ በነጻ ገብቶ እንዲደግፍ ያስተላለፈው ውሳኔ ቢደነቅም ሜዳ ውስጥ ግን የቡድኑ እንቅስቃሴና ውጤት ደጋፊውን አስከፍቷል። በሜዳቸው እንግዳ ቡድን የመሰሉት ሉሲዎቹ 3 ግቦችን አስተናገደውና 2 ግቦችን አስቆጥረው በድምሩ 6 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፈው ከአፍሪካ ዋንጫ ውጭ ሆነዋል።

አሰልጣኝ ሰላም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድንን ይዛ በናይጄሪያ በመሸነፍ ከውድድሩ ውጭ ከሆነች በኋላ ዋናውን ብሔራዊ ቡድን መረከቧ ተገቢ እንዳልሆነ የሚናገሩ ወገኖች እሁድ እለት ውጤቱ የሚገባን እንደሆነ ይናገራሉ። አሰልጣኟ እንደ ብርቱካን ገብረክርስቶስ ያሉ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾችን ቡድኗ ውስጥ አለማካተቷ ለትችት ዳርጓታለ። በተለይም ልዩ ክህሎት ያላትና ባለፈው አመት የምስራቅ አፍሪካ ኮከብ ተጫዋች የሆነችው ብርቱካን አለመካተቷ ቡድኑን ዋጋ እንዳስከፈለው መናገር ይቻላል።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአብዛኛው አማካይ ቦታው ላይ ሰፊ ክፍተት እንዳለበት አልጄሪያ ላይ በግልጽ የታየ ቢሆንም አሰልጣኝ ሰላም እና ረዳቶቿ ክፍተቱን በአዲስ አበባው ጨዋታ ለመሙላት ሳይችሉ ቀርተዋል። ቡድኑም ከተጋጣሚዎቹ የበለጠ ሰፊ ጊዜ ዝግጅት የማድረጉን ያህል ውጤታማ አለመሆኑ አሰልጣኞቹ ላይ ቅሬታ እንዲነሳ አድርጓል።

የሉሲዎቹ ቡድን ባለፈው የአፍሪካ ዋንጫ በውዝግቦች ታጅቦ በመጨረሻው ሰአት ወደ ማጣሪያው ገብቶ በአልጄሪያ ተሸንፎ ካሜሮን አዘጋጅተው ከነበረው አህጉራዊ መድረክ መውጣቷ ይታወሳል። ቡድኑ አሁንም ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ በአልጄሪያ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጪ መሆኑ ብዙዎችን አሳዝኗል። ብሔራዊ ቡድኑ ልምድና ውጤት ያላቸው አሰልጣኞች አግኝቶ በታላላቅ ውድድሮች ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የሚጠበቅ ሀላፊነት መሆኑን ብዙዎች የሚስማሙበት እውነት ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
43 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 429 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us