“አሁን ያለው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች አስተሳሰብ ደረጃ እና የእግር ኳስ እድገት አልተጣጣሙም”

Wednesday, 13 June 2018 13:47

 

“እግር ኳስ ሃይማኖቴ ነው” የሚለው አሰልጣኝ አብርሃም ተክለሀይማኖት (የካፍ ኢንስትራክተር)

 

አሰልጣኝ አብርሃም ተክለሃይማኖት ከብሔራዊ ቡድን መልስ ባሉ ሁሉም የእግር ኳስ ጨዋታዎች ተጫውቶ ያለፈ ጎልማሳ ሲሆን አሁን በግሉ የታዳጊዎች የህጻናት እግር ኳስ አካዳሚ ከፍቶ እየሰራ ይገኛል። ከጎጃም ምርጥ እስከ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ድረስ በዘለቀው የእግር ኳስ ህይወቱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያለፈ ሲሆን በአሰልጣኝነት ደግሞ የትውልድ ከተማውን (መቀሌ) ጉና ንግድን አሰልጥኗል። ደደቢት እና ታላቋን ኢትዮጵያ ቡድንም አሰልጥኖ አልፏል። ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነትን በመረከብ አሀዱ ብሎ የጀመረው የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ስራው በሁሉም ደረጃዎች የሚገኙ ወንዶች ብሔራዊ ቡድኖችን አሰልጥኗል። ከሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጋር ደግሞ ለአፍሪካ ዋንጫ መቅረብ ችሏል።

በቅርቡ እግር ኳሳችን እና የኋሊት እርምጃው በሚል ርዕስ አንድ ጥናታዊ መፅሀፍ ለአንባቢያን ያቀረበው አሰልጣኝ አብርሃም በተሌዩ ጉዳዮች ላይ በሰንደቅ ጋዜጣ የሰጣቸውን አስተያየቶች ከዚህ በታች አቅርበነዋል።

“አሁን ያለው የኢትዮጵያ ተጫዋቾች አስተሳሰብ ደረጃ እና የእግር ኳስ እድገት አልተጣጣሙም። እግር ኳሳችን ወደ ታች ያደገውም ይህ ነገር ስላልተጣጣመነው” ሲል የወቅቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ይገልጸዋል። ኢንስትራክተሩ አያይዘው በአንድ ወቅት መነቃቃት ተፈጥሮ በነበረው የእግር ኳስ እድገት ዙሪያ ሲናገር “ለዋልያዎቹ መነቃቃት የፈጠርኩት እኔ ነኝ ቲፎዞ ስለሌለኝ እንጂ” በማለት ይናገራል። ሃሳቡን ሳያብራራም “ዋሊያዎቹ መጥፎ ደረጃ ላይ በነበሩበት ወቅት እኔ ይዤው በነበረበት ጊዜ እንደ እንደ ጋና እና ኮንጎ ያሉ ቡድናችን እያሸነፈ ለአፍሪካ ዋንጫ እና ለኦሎምፒክ ማጣሪያ እየገሰገሰ ነበር። ደቡብ አፍሪካ ለለንደን ኦሎምፒክ ያፈው ጋናን አሸንፎ ነው” ይላል። ከዚያ ምድብ ጠንካራዎቹን ጋናን እና ኮንጎን ያሸነፈው የአሰልጣኝ አብርሃም ቡድን ሥራው ደግሞ ከኳቶሪያል ጊኒ አዘጋጅተው በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ እንደነበሩ ገልፆ “እንደ ግብፅና ታንዛንያ ያሉ ቡድኖችን በሰፊ ጎል እያሸነፍን ነበር” ይላል። ሆኖም ይህ ስኬቱ አንድ ድንቅና ብርቅ ሊታይ አይገባውም ይላል። ምክንያቱም ሲያስቀምጥም የአፍሪካ ዋንጫ እና የካፍ መሥራቿ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ የሚያንሳት እንጂ የሚበዛባት አይደለም ባይ ነው። “ትልቅ አገር ሆነን ትንሽ ውጤት ይዘን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ደረቴን ነፍቼ ስኬታማ ነኝ ብዬ ለመናገር አያስችለኝም” ብሎ ይናገራል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውጤት ከሚያስቆጫቸው ሰዎች አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ሰው የቁጭቱን መነሻ ሲናገርም “በኢትዮጵያ ጉዳይ የማይቆጭ ዜጋ አለ ማት ይከብደኛል” ሲል ንግግሩን ይጀምራል። “የእኔ ቁጭት ይህን እግር ኳስ ሰርተን ትልቅ ደረጃ ማድረስ ስንችል አለመቻላችን ነው። ምንም የሚያጣላ ነገር በሌለበት በቁር------- በግለሰቦች ፍላጎት እግር ኳሳችንን እየገደልን ስለማይ ያስቆጨኛል። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራች ሆና አሁን ወደ ኋላ መቅረቷ ደግሞ ያበሳጫል። በፊፋ 151ኛ ደረጃ ስንባል በጣም ያስፈራል” የሚለው አሰልጣኙ፤ በአፍሪካ ሶስተኛ ደረጃ የነበረች አገር አሁን ከአፍሪካ 42ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ ለቁጭቱ መነሻ እንደሆነው ይናገራል። የዚህ ችግር መንስኤው በእጃችን ነው ሲል የሚናገረው ኢንስትራክተሩ “መደማመጥ አለመኖር፣ ውዝግብና ሽኩቻ መስፈኑና ግለኝነቱ ነው” ይላል የችግሩን ምንጭ ከስሩ ሲገልጸው። ይህ በመሆኑ ደግሞ የአገሪቱ ገንዘብ፣ የወጣች እድሜ እና የአገሪቱ አጠቃላይ ሀብት እየባከነ መሄዱን ተመልክቶ እንደሚያሳዝነው ይናገራል። አያይዞ መፍትሄውን ሲያስቀምጥም ተግባብቶ መስራት፣ መደማመጥ እና ሙያን ለባለሙያዎች መተው እንደሆነ ይገልፃል።

ለእግር ኳስ እድገት መሠረታዊ የታዳጊዎች ስልጠና አስፈላጊ መሆኑን የሚያምነው ኢንስትራክተር አብርሃም በግሉም በዚህ መስክ ፈቃድ ወስዶ፣ ቢሮ ተከራይቶና ሰራተኛ ቀጥሮ ወደስልጠና ቢገባም የማሰልጠኛ ቦታ ችግር ህልሙን ወደ ቅዠት እንደቀየረበት ይናገራል። አንድ ህጻን ኳስ የሚጫወት ከሆነ የአእምሮ እድገትና የአካል ጥንካሬ ስለሚያገኝ አምራች ዜጋ እንደሚሆን የሚያምነው አብርሃም “ከብዙ ህጻናት መካል ነገ ራሳቸውንና ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ታዳጊዎችን ማፍራት ይቻል ነበር። ሆኖም የመስሪያ ቦታ ችግሩ እቅዳችንን አደናቀፈው። ቀደም ሲል እኔም ሆንኩ ሟቹ ወዳጄ አሰግድ ተስፋዬ ስልጠና የምንሰጠው በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ነው። ነገር ግን ምክንያቱን ሳይገልፁ ከግቢው የምንሰጠውን ስልጠና ከለከሉን። አሁን የምሰራው በቦሌ መድሃኒአለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ነ ው። ይህንም የፈቀደልን የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ዳንኤል ነው” በማለት የገጠመውን ችግር ተናግሯል።

አሰልጣኝ አብርሃም ተክለሀይማኖት በብራዚል ሪዮዲጄኔረዮ እና በስፔን ባርሴሎና አካዳሚዎችን ጎብኝቶ ያገኘውን ልምድ ሲናገርም “ብራዚል በ2017 ብቻ 1800 ተጫዋቾች አውሮፓ ውስጥ እንደሚጫወቱ ታውቋል። ህንድ በተማሩ ዜጎቿ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንደሆነችው ሁሉ ብራዚልም ከእነዚህ ልጆቿ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ፣ የሚከፈቱት ኢንቨስትመንት እና ለወላጆቻቸው የሚያደርጉት ድጋፍ ብራዚልን ተጠቃሚ ያደርጋታል። በዚህ የተነሳም እያንዳንዱ ብራዚላዊ ህጻን ልጁን እጁን እየጎተተ የሚወስደው ወደ እግርኳስ ሜዳ ነው። መንግሥትም ይህን ተረሰድቶ ለህጻናት መጫወቻ የሚያገለግሉ በርካታ ሜዳዎችን አጋጅቷል” ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥትም ለዚህ ትኩረት እንዲያደርግ አቅርቧል።    

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
71 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 45 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us