የ2018 የሩስያ የዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል

Wednesday, 13 June 2018 13:55

 

የአፍሪካ ቡድኖች ታሪክ ይቀይሩ ይሆን

 

የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፊፋ የሚያዘጋጀው የ2018 የአለም እግር ኳስ ዋንጫ በሩስያ አስተናጋጅነት ከሚሳተፉ አምስት የአፍሪካ ቡድኖች የአህጉሪቱን የተሳትፎ ታሪክና ውጤት የመቀየር አቅማቸው የሚፈተሽበት መልካም አጋጣሚ እንደሆነ ይታሰባል።

የአፍሪካ አህጉርን የሚወክሉት አምስት ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች ግማሽ ፍጻሜና ከዚያ በላይ በመድረስ በውድድሩ ታሪክ አዲስ ውጤት ያስመዘግቡ ይሆን የሚለው ጥያቄ መነጋገሪያ ነው።

በሩስያው የ2018 የፊፋ አለም ዋንጫ መድረክ የአፍሪካውያን ኩራት ሊሆን የሚችለው ቡድን ማን ይሆን? ግብጽ፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዝያ፣ ሞሮኮ ወይስ ናይጄሪያ?

ግብጽ

የግብጽ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከአስተናጋጇ ሩስያ፣ ሳኡዲ አረቢያ እና ኡራጋይ ጋር ተመድቧል። ከ28 አመት በኋላ ወደ አለም ዋንጫ የተመለሱት ፈርኦኖቹ ከምድቡ ከሩስያ በተጨማሪ ኡራጋይ ፈታኝ ተጋጣሚ እንደምትሆንባቸው መናገር ይቻላል።

በሊቨርፑሉ አጥቂ መሀመድ ሳላህ ላይ ጥገኛ የነበረችው ግብጽ ተጫዋቹ ጉዳት በማስተናዱ ከምድብ ማጣሪያ የማለፍ ተስፋዋ መንምኗል። ሳላህ በመጀመሪያው የቡድኑ ጨዋታ ላይ መሰለፍ እንደማይችል የተነገረ ሲሆን በቀጣዮቹ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ ቡድኑን ሊጠቅም እንሚችል ተገምታል። ቡድኑ ከምድብ ማጣሪያው ማለፍ ከቻለ ግን ተጫዋቹ የተሻለ ብቃት ላይ በመገኘት ቡድኑን እንደሚጠቅም ታምኖበታል።

ቱኒዝያ

የቱኒዚያ ቡድን በምድብ ሰባት ከቤልጂየም፣ ፓናማ እና እንግሊዝ ጋር ይገኛል። በምድቡ በማጣያው የማለፍ ተስፋ ካለው ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በስተቀር ፈታኝ ተጋጣሚ እንደማይገጥመው ተገምቷል። በአለም ዋንጫው የምድብ ማጣሪያውን በማለፍ ወደ ሩብ ፍጻሜ ውድድር መግባት እንደሚችሉ ከሚጠበቁ የአፍሪካ ቡድኖች መካከል የቱኒዝያ ቅድሚያ ግምት ተሰጥቶታል።

ሴኔጋል

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን በምድብ ስምንት ከፖላንድ፣ ጃፓን እና ኮሎምቢያ ጋር ይገኛል። ሰይዱ ማኔ እንደ ክለብ አጋሩ ሞ ሳላህ ሁሉ ቡድኑን በአለም ዋንጫው መድረክ ውጤታማ እንደሚያደርግ ተስፋ ተጥሎበታል። ይሁንና ስብስቡ ከ2002ቱ የጃፓንና ደቡብ ኮሪያ የአለም ዋንጫ ተሳታፊው የሴኔጋል ቡድን አንጻር ሲታይ ደካማ የሚባል በመሆኑ ከማጣሪያው የማለፍ ተስፋው የመነመነ እንደሆነ ነው የሚገመተው።

ናይጄሪያ

በምድብ አራት ከአይስላንድ፣ ክሮሽያ እና አርጀንቲና ጋር ይገኛል። በሊዮኔል ሜሲ የሚመራው የአርጀንቲና ቡድን ከምድቡ ቀዳሚ ግምት የተሰጠው ሲሆን፣ ናይጄሪያ በሁለተኛነት የማለፍ እድል እንዳለው ይገመታል። ይሁንና በተናጥል የሚታወቁ ተጫዋቾች የሌሉት የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ያልተጠበቀ ውጤት በማስመዝገብ ከአርጀንቲና ቀጥሎ ምድብ ማጣሪያውን ሊያልፍ እንደሚችልም ይታመናል።

ሞሮኮ

በአለም ዋጫው አፍሪካን ከሚወክሉ አምስት ሀገሮች ሶስተኛዋ የሰሜን አፍሪካ ቡድን የሆነችው ሞሮኮ በምድብ ሁለት ከፖርቹጋል፣ ስፔን እና ኢራን ጋር ተመድባለች። ምድቡ የአለማችን ሀያል የእግር ኳስ ቡድኖች የሚባሉት የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀገር ፖርቹጋል እና ስፔን የሚገኙበት ከመሆኑ አንጻር ሞሮኮ ከምድቡ የማለፍ ተስፋዋ የመነመነ እንደሆነ መናገር ይቻላል። ያልተጠበቀ ውጤት በማስመዝገብ ሩብ ፍጻሜውን ለመቀላቀል ከቻለች በሚል እንጂ ተጋጣሚዎቿን አሸንፋ በውድድሩ መድረክ አዲስ ታሪክ ታስመዘግባች የሚል እምነት የሚጣልባት አይደለችም።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
183 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 44 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us