ደደቢት ከኢትዮጵያ ዋንጫ ራሱን አገለለ

Wednesday, 20 June 2018 13:10

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የኢትዮጵያ ዋንጫ በተለምዶ የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ተብሎ የሚጠራው ውድድር ዛሬ በአዲስ አበባ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል። በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ተብለው ከሚጠበቁ ጠንካራ ተፎካካሪዎች መካከል አንዱ የሆነው የደደቢት እግር ኳስ ቡድን ራሱን ከውድድሩ ማግለሉን በደብዳቡ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ በአደረገው መርሀግብር መሰረት የኢትዮጵያ ዋንጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ሁለት ጨዋታዎች ይካሔዳሉ። የመጀመሪያው ጨዋታ መከላከያ ከድሬደዋ ከተማ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን በ9 ሰአት ይጀመራል። ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ ኢትዮ ኤሌትሪክ ከመቀሌ ከተማ የሚያካሒዱት ነው። ጨዋታውም 11 ሰአት ላይ ይከናወናል።

ውድድሩ በቀጣይ ቀናትም የሚካሔድ ሲሆን፤ ነገ ሐሙስ እለት ሐዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና፤ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወላይታ ዲቻ እንደሚጫወቱ የወጣው መርሀግብር ያመለክታል። ሰሞኑን በደቡብ ኢትዮጵያ ከተሞች ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ የሐዋሳ ከተማ ክለብ ልምምድ ማድረግ እንዳቆመ የተሰማ ሲሆን በነገው እለትም በኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ቡድኑ ስለመሳተፉ የሚታወቅ ነገር የለም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በውድድሩ ላይ ይሳተፋል ተብሎ የሚጠበቀው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል። ለዚህም ሁለት ምክንያቶችን አስቀምጧል። ክለቡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው በኢትዮጵያ ዋንጫ ላይ ክለቡ ከጅማ ከተማ ጋር እንዲጫወት የተደለደለ እና በቀጣይም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ጅማ ላይ ከጅማ ከተማ ጋር የጨዋታ መርሀግብር እንዳለው አስታውሶ፤ ለወጪ የሚዳርገኝ ነው ብሏል። ሁለተኛው ምክንያትም የደህንነት ጉዳይ እንደሆነ ነው ክለቡ ያስታወቀው።

“ያለው የወጪ ጫና እና የደህንነት ስጋት ከግምት ውስጥ በማስገባት ከጥሎ ማለፍ ውድድሩ ማግለላችንን በማክበር እንገልጻለን” ሲል ደደቢት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላከው መግለጫ ላይ አስታውቋል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
35 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 673 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us