የሳውዲ ተጫዋቾች ቅጣት ይጠብቃቸዋል

Wednesday, 20 June 2018 13:16

 

የሩስያው የአለም ዋንጫ ላይ ዝቅተኛ ግምት ከተሰጣቸው ቡድኖች መካከል የሳውዲ አረቢያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ዋነኛው ነው። ቡድኑ በአለም ዋንጫው ከአዘጋጇ ሩስያ ከምትገኝበት ምድብ የተደለደለ ሲሆን በመክፈቻው እለትም በሩስያ ጋር በአደረገው ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ተሸንፏል።

የሳውዲ አረቢያ ቡድን ዝቅተኛ ግምት ቢሰጠውም በርካታ ግቦችን ይሸነፋል ተብሎ አልተጠበቀም ነበር። በጨዋታው ያሳየው ደካማ አቋምም ደጋፊዎቹን አሳዝኗል። የሀገሪቱን መሪም አሳፍሯል።

ጨዋታውን የሁለቱ አገሮች መሪዎች በስታዲየሙ ተገኝተው የተከታተሉት ሲሆን፤ የሳውዲው መሪ ልኡል መሀመድ ቢን ሰልማን ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት ብሔራዊ ቡድናቸው እጅጉን እንዳሳፈራቸው ነው የገለጹት።

‹‹ይህንን ብሔራዊ ቡድን ለአለም ዋንጫው ለማብቃት ባለፉት ሶስት አመታት ከፍተኛ ወጪ መድበን እንዘጋጁ አደርገናል። ከፍተኛ የሆነ ወጪም ተደርጎለታል። ቡድኑ ምንም ነገር እንዳይጎድልበት ሁሉንም አድርገናል። ነገር ግን ሜዳ ውስጥ ላሳየው አቋም ከጠበቅነው በታች ነው። አሳፍሮኛል›› ሲሉ መናገራቸው ተዘግቧል።

የሳውዲ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ቡድኑ በመጀመሪያው ጨዋታው የወረደ አቋም ማሳየቱን በመግለጽ በተለይም ለሽንፈቱ የጎላ አስተዋጽኦ አድርገዋል የተባሉ ሶስት ተጨዋቾች ላይ ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስታውቋል። ከቡድኑ አባላት መካከል ቅጣት ይብቃቸዋ የተባሉት ተጫዋቾችም ግብ ጠባቂው አብደላህ አል ማዩፍ፣ የፊት መስመር ተጫዋቹ መሀመድ አል ሳሀለዊ እና ተከላካዩ ኦማር ሀዋሲ ናቸው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
42 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 786 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us