የሜሲን ፍጹም ቅጣት ምት ያከሸፈው የአይስላንዱ ግብ ጠባቂ

Wednesday, 20 June 2018 13:18

 

በአለም ዋንጫው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳትፎ ታሪክ ያስመዘገበችው አይስላንድ አስደናቂ የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። አነስተኛ የህዝብ ብዛት ካለው የአለማችን ሀገሮች የተገኘው ብሔራዊ ቡድኑ ሀያል ከሚባለው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ጋር 1 ለ 1 መለያየቱ ይታወሳል።

በባርሴሎናው አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ የሚመራውን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድንን በመቋቋም ነጥብ ተጋርቶ የወጣው የአይስላንድ ብሔራዊ ቡድን ውጤቱ የአሸናፊነት ያህል ያስፈነጠዘ ነበር። ለአርጀንቲና ደግሞ አስከፊ ውጤት ነው። በጨዋታው የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት ወደ ግብነት መቀየር አለመቻሉም እጅግ አሳዛኝ ነበር።

በአንፃሩ ደግሞ የሊዮኔል ሜሲን ቅጣት ምት ያከሸፈው የአይስላንዱ ግብ ጠባቂ ሀነስ ሆልዶርሰን ደግሞ አድናቆትን ማትረፍ ችሏል። ተጫዋቹ ከእግር ኳስ ሌላ ሙያው በፊልም ዳይሬክተርነት የሚሰራ መሆኑ ልዩ አድናት አሰጥቶታል። የሚሲን የቅጣት ምት ለማዳን የቻለው የሚሴን የጨዋታ እንቅስቃሴና የፍጹም ቅጣት ምት ላይ ያለውን ክህሎት በፊልሞች ላይ አጥንቶ መገኘቱን አስተውቋል።

“ከአርጀንቲና ጋር ስንጫወት የቅጣት ምት ወይም የፍጹም ቅጣት ምት ሊከሰቱ እንደሚችሉ አውቅ ነበር። ስለዚህም የቡድኑን አጨዋወት በደንብ አጥንቻለሁ። በተለይም ደግሞ የሜሲን የፍጹም ቅጣት ምቶች በቪዲዮዎች ላይ በደንብ ነው የተመለከትኩት። ምናልባት ይህንን ማድረጌ ማናልባት ፍጹም ቅጣት ምቱን ለማክሽፍ አስሎኛል ብዬ አምናለሁ” ሲል ተናግሯል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
43 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 465 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us