የሮናልዶ ኮከብነት ደምቋል

Wednesday, 20 June 2018 13:19

 

የአለማችን ኮከብ ተጫዋች ፖርቱጋላዊው ክርስቲኖ ሮናልዶ በሩስያው የአለም ዋንጫው የበለጠ ደምቆ ተገኝቷል። ተጨዋቹ ፖርቱጋል ከስፔን ጋር 3ለ3 በተለያየችበት የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ ሶስቱንም ግቦች አስቆጥሮ አድናቆትን አግኝቷል። ሶስተኛዋ የቅጣት ምት የተገኘችው ሶስተኛዋ ግብ ደግም እርሱ የአለም ኮከብ ለምን እንደተባለ የምታስረዳ ሆናለች።

ከስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ጋር የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ያነሳው ሮናልዶ፤ በሩስያው የአለም ዋንጫ ሀገሩ ፖርቹጋልን ከሽንፈት መታደግ ችሏል። በጨዋታው ፖርቱጋል በስፔን 3ለ2 እየተመራች የነበረ ሲሆን ጨዋታውም ሊጠናቀቅ በነበረበት ሰአት ተገኘችውን የቅጣት ምት ሮናልዶ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት መቀየር ችሏል። ሮናልዶ የፖርቹጋልን ሶስቱንም ግቦች በማስቆጠር በአለም ዋንጫው ሀትሪክ የሰራ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል። በኮከብ ግብ አግቢነት ስሙን አጽፏል። በእግር ኳስ ተጫዋችነቱ በክለቡም ሆነ ለብሔራዊ ቡድኑ 51ኛ ሀትሪክ ሆኖ ተመዝግቦለታል።

የ33 አመቱ ሮናልዶ በአራት ተከታታይ የአለም ዋንጫ መድረኮች ላይ በመሰለፍና ግቦችንም በማስቆጠር ከጥቂቶች ተርታ መሰለፍ ችሏል። ተጨዋቹ እድሜው እየገፋ በሔደ ቁጥር የላቀ ብቃት ማሳየቱ አድናቆትን አሰጥቶታል። በሩስያው የአለም ዋንጫም የመጨረሻው እንሚሆን ይገመታል። በአለም ዋንጫው መድረክ ኮከብ ሆነ ለመድመቅ የላቀ ክህሎቱን እንደሚያሳይም ይጠበቃል።

ይምረጡ
(3 ሰዎች መርጠዋል)
91 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 302 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us