የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው የሜክሲኮ ድል

Wednesday, 20 June 2018 13:21

 

የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ከተጀመረ በኋላ ከታዩ አስደናቂ ክስተቶች መካከል ሜክሲኮ በሻምፒዮና ጀርመን ላይ ያስመዘገበችው የ1ለ0 ድል አንደኛው ነው።

እሁድ እለት ሁለቱ ቡድኖች ባደረጉት የምድብ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ የአሸናፊነት ግምቱ የተሰጠው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ነበር። ባለፈው የዓለም ዋንጫ የብራዚል ቡድን 7ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ታሪካዊ ሽንፈት ያከናነበው ቡድን ግን ለሜክሲኮ እጅ ሰጥቶ ተገኝቷል።

በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በ35ኛው ደቂቀ ላይ ሂርቪንግ ሎዛኖ የተባለው ተጨዋች ብቸኛና የመጀመሪያዋን ግብ ያስቆጠረ ሲሆን፤ ከጨዋታው በኋላ የሜክሲኮ ተጫዋቾች ሜዳ ውስጥ በደስታ እንባ ሲራጩ ታይተዋል። ግቧ ስትቆጠር ደግሞ በሀገራቸው ሜክሲኮ ደግሞ የመሬት መንቀጥቀጥ ማስነሳቱን ዘገባዎች አመላክተዋል።

ከሜክሲኮ የወጡ መረጃዎች እንዳመላከቱት ከሆነ በዋና ከተማዋ ሁለት አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጥሯል። የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተውም ጨዋታውን ተሰብስበው የሚመለከቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች ባሰሙት የደስታ ጩኸት መሆኑን ነው የመስኩ ባለሞያዎች የገለጹት።

የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጥሯዊ በሆኑ አደጋዎች የሚፈጠር ሲሆን፤ በሜክሲኮ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥን ደግሞ “ሰው ሰራሽ” ሲሉ ገልጸውታል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
63 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 505 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us