በማንቸስተር ሲቲ የሚፈለገው ናኦል ኢትዮጵያን አስቧል

Wednesday, 20 June 2018 13:31

 

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ስዊድን ሀገር ተወልዶ ያደገው የ14 ዓመቱ ናኦል ተስፋዬ በላቀ የእግር ኳስ ክህሎቱ ስመ ጥር ክለቦች የሚፈልጉት ተጫዋች ነው። በስዊድን የመገናኛ ብዙሀን አድናቆታቸውን በመግለጽ ለብሔራዊ ቡድናቸው የመጫወት ተስፋ እንዳለው ይናገራል። ይሁንና ታዳጊው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስለመጫወት ማሰቡ ታውቋል። ሰሞኑንም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚጫወትበት ሁኔታ ላይ ቤተሰቦቹ መምከር ፈልገዋል።

ሶከር ኢትዮጵያ እንደዘገበው ከሆነ ታዳጊው ናኦል ተስፋዬ ወደ አዲስ አበባ እየመጣ ሲሆን፤ ቤተሰቦቹም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚጫወትበት ሁኔታ ላይ ከሀገሪቱ አመራሮች ጋር ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል።

ናኦል ተስፋዬ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት የማግባባቱ ስራ የተጀመረው በቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ካስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በአቶ ጁነዲን ባሻ ሲሆን፤ አሁን ካለው በአቶ ኢሳያስ ጂራ ከሚመራው አመራር ጋር ቤተሰቦቹ እንደሚመክሩ ታውቋል።

“የቀድሞው ፕሬዝዳንት ወደ ኢትዮጵያ መጥቼ ሙከራ የማደርግበት እና ከአዲሱ ፕሬዝዳንት ጋር የምወያይበትን እድል አመቻችተዋል። ከቤተሰቦቼ ጋር ስለ ቀጣይ ሁኔታዎች ለመነጋገር ነው የምመጣው” ሲል መናገሩን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

ከዚህ በተጨማሪም ተጫዋቹ በኢትዮጵያ ቆይታው የሙከራ ጊዜ እንደሚኖረውና በእንግሊዝ ለሚገኝ አንድ ክለብ ፊርማውን እንደሚያኖር መግለጹን ዘገባው አስነብቧል።

በእንግሊዝ ከሚገኙ ክለቦች በማንቸስተር ሲቲ የበለጠ እንደሚፈለግ ተጫዋቹን በተመለከቱ የወጡ መረጃዎች ያስረዳሉ።

ናኦል ተስፋዬ በእግር ኳስ ስፖርት በግራ መስመር ተከላካይነትና በመስር ተጫዋችነት የላቀ ክህሎት ያለው ታዳጊ ነው።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
67 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 450 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us