ሉሲዎቹ ለሴካፋ ዋጫ ዝግጅት ጀምረዋል

Wednesday, 11 July 2018 13:12

 

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን በሩዋንዳ አስተናጋጅት ለሚካሔደው የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ዋንጫ (ሴካፋ) ዝግጅት ጀምረዋል።

በአፍሪካ እጅግ ደካማ የሚባለው ሴካፋ በዞኑ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር መድረክን በድጋሚ እንዲያካሂድ ማድረጉ ይታወሳል። ውድድሩ በድምቀት ቢካሔድ የዝግጅት ጉድለት የታየበት ነበር። ይኸው ችግር ዘንድሮም ሳይቀረፍ ውድድሩን ሩዋንዳ እንድታስተናግድ ተደርጓል። ውድድሩ ከሁለት ወር በፊት ለማካሄድ የተያዘው ቀጠሮ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ተሰርዞ በድጋሚ ከጁላይ 19 ጀምሮ እንደሚካሔድ ነው የተለጸው። የውድድሩ አዘጋጅ አካል በድጋሚ ጥሪ ሲያደርግ ግን በተፈለገው መጠን በርካታ ተሳታፊ ሀገሮችን ማገኘት አልቻለም።

የውደድሩ መድረክ መራዘሙን ተከትሎ የተሳታፊ ሀገሮች ቁጥር ቀንሷል። ከዞኑ አባል ሀገሮች መካከልም አምስቱ ብቻ እንደሚሳተፉ ተረጋግጧል። ከአምስቱ ሀገሮች መካከልም ኢትዮጵያ አንደኛዋ ሀገር ስትሆን፤ በቅርቡ ከአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በአልጄረያ የተሰናበተው የሉሲዎቹ ስብስብ መሳተፉ ታውቋል። ብሔራዊ ቡድኑም ዝግጅቱን መጀመሩ ታውቋል።

አሰልጣኝ ሰላም ዘርአይ ለሴካፋው የሴቶች ዋንጫ 22 ተጨዋቾች የጠራች ሲሆን ብዙዎቹም በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ የተሳተፉ ናቸው። ብርቱካን ብረክርስቶስ ጥሪ የተደረገላት ሲሆን፤ አጥቂዋ ረሂማ ዘርጋው አልተካተተችም። ሎዛ አበራ ደግሞ ስዊድን ሀገር ለሙከራ በመሄዷ በሉሲዎቹ ስብስብ ውስጥ አትገኝም።

በሩዋንዳ ኪጋሊ በሚካሔደው የ2018 የሴካፋ የሴቶች ዋንጫ ላይ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የሚሳተፉት አስተናጋጇ ሩዋንዳ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ እና ያለፈው ውድድር አሸናፊ ታንዛኒያ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ጁላይ 21 ቀን ከኡጋንዳ ጋር ታደርጋለች። ከሁለት ቀን በኋላ ደግሞ ከአስተናጋጇ ሩዋንዳ ጋር ትጫወታለች። በተመሰሳይ ከሁለት ቀን በኋላ ሶስተኛ ጨዋታዋን ከሻምፒዮኗ ታንዛኒያ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

ተሳታፊ ሀሮች ቁጥር እጅጉን ማነስ ውድድሩን በተለመደው ፎርማት በምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ለማድረግ አላስቻለም። ስለሆነም የውድድሩ ፎርማት እንደ ሊግ ውድድር እንዲሆንና አሸናፊው እንዲለይ ይደረጋል።

ከሁለት አመት በፊት ኡጋንዳ ባስተናገደችው ያለፈው ውድድር ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ኡጋንዳን አሸንፎ ሶስተኛ ደረጃን ማግኘቱ ይታወሳል። በፍጻሜ ጨዋታው ደግሞ ታንዛኒያ ኬንያን አሸንፋ ነበር ዋንጫውን ያነሳችው።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው በሩዋንዳ አስተናጋጅነት ከሐምሌ 12 እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2010 ዓ.ም ለሚካሄደው የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) የሴቶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከሐምሌ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከዚህ በታች ለተገለፁት እጩ ተጨዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል።


 


ከመከላከያ እግር ኳስ ክለብ

1.       እመቤት አዲሱ

ከሀዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ

1.       ምርቃት ፈለቀ

2.       ልደት ቶሎ

ደደቢት እግር ኳስ ክለብ

1.       ገነት አክሊሉ

2.       መስከረም ኮንካ

3.       ሠናይት ቦጋለ

4.       ብርቱካን ገ/ክርስቶስ 

5.       ትግስት ዘውዴ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1.       ንግስት መዓዛ

2.       ታሪኳ ዴቢኮ

3.       ዙሌይካ ጁሀድ

4.       ሕይወት ደንጊሶ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ

1.       መሠሉ አበራ

2.       ብዙአየሁ ታደሠ

3.       ቤዛዊት ተስፋዬ

ኢትዮ ኤሌትሪክ እግር ኳስ

1.       ቤቴልሔም ከፍያለው

2.       አለምነሽ ደመቀ

ኢትዮ/ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ

1.       አረገሽ ካልሳ

ጥረት ኮርፖሬሽን

1.       ምስር ኢብራሂም

2.       አሣቤ ሞኢሶ

3.       ታሪኳ በርገና 

አዳማ ከተማ እግር ኳስ

ሴናፍ ዋቁማ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
28 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 705 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us