ደደቢቶች በሴቶች የሊጉን ዋንጫ አንስተዋል

Wednesday, 11 July 2018 13:31

 

-    ሎዛ አበራ ኮከብ ግብ አግቢ ሆናለች

በኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደደቢት አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል። የቡድኑ አጥቂ ሎዛ አበራ ዘንድሮም የሊጉን የኮከብ ግብ አግቢነት ክብር ተጎናጽፋለች።

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ጠንካራ ከሆኑት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ደደቢት የ2010 ዓ.ም አሸንፎ ዋንጫውን አንስቷል። የቅርብ ተፎካካሪው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን በሁለተኛነት ሊጉን አጠናቋል።

ደደቢት ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ስታዲየም የጌዲዮ ዲላ ቡድንን ሲያስተናግድ የሊጉ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጦ ነበር። ወደ ሜዳ ሲጋባም የክብር አሰላለፍ በተጋጣሚው ቡድን ተደርጎለታል።

የሊጉን የመጨረሻ ጨዋታ በ3ለ1 አሸናፊነት ያጠናቀቀው የደደቢት ቡድን የሊጉን ዋንጫ በደማቅ ስነ ስርአት ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተቀብሏል። የቡድኑ ተጫዋቾችም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባላት የሜዳልያ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።

የደደቢትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አጥቂ የሆነችው ሎዛ አበራ በእለቱና ባለፈው አንድ ጨዋታ ላይ ተሰልፋ ባትጫወትም የሊጉን ኮከብ ግብ አግቢነት የወሰደባት አልነበረም። ተጨዋቿ ያስመዘገበቻቸው 17 ግቦች ሊጉን በኮከብ ግብ አግቢነት እንድታጠናቅቅ አስችሏታል። ሎዛ በኮከብ ግብ አግቢነት ስታጠናቅቅ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ ነው።

ሎዛ አበራ በክለቧና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በፊት መስመር ተጫዋችነት የምታሳየው ብቃት በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈላት ሲሆን፤ በውጭ ሀገር ክለቦች ዐይን ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። ሰሞኑንም ተጨዋቿ ለሙከራ ወደ ስዊድን ሀገር መጓዟን ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።

በዘንድሮው የኢትዮጵያ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ላይ 10 ክለቦች የተሳተፉ ሲሆን፤ ደደቢትና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በመከተል የመከላከያ ክለብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቋል። ከክልል ክለቦች ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረው የሐዋሳ ከነማ እግር ኳስ ክለብ አራተኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
29 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 324 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us