የዋንጫው ማረፊያ ያልተለየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ ፍፃሜ ያገኛል

Wednesday, 11 July 2018 13:27

 

በተለያዩ ጥቃቅን ምክንያቶች ሲቆራረጥ የከረመው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እሁድ ይጠናቀቃል።

የዋንጫው ማረፊያ ያልታወቀው የዚህ ዓመት ውድድር ጅማ አባ ጅፋር ከአዳማ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሐዋሳ ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ የዋንጫውን ማረፊያ ይለያል። ሊጉን በዚህ ዓመት የተቀላቀለው ጅማ አባ ጅፋር እና የ13 ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ እኩል ነጥብ እና እኩል የጐል ክፍያ የያዙ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ የሁለቱን ጨዋታ በተመሳሳይ ሰዓት እንዲካሄድ ወስኗል። ጅማ አባ ጅፋር ከዋንጫ ተፎካካሪነቱ በተጨማሪ አጥቂው አካኮ አፎላቢ የሊጉን ኮከብ ጎል አግቢነት በ19 ጎሎች እየመራ ሲሆን፤ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌም ለኮከብ አሰልጣኝነት ይጠበቃል።

በሌሎች ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ከመቀሌ ከተማ፣ ወልድያ ከነማ ከወላይታ ዲቻ፣ መከላከያ ከደደቢት፣ ወልዋሎ ከድሬዳዋ ከነማ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና እና አርባ ምንጭ ከነማ ከፋሲል ከነማ የሊጉ 30ኛ ሳምንት መርሃ ግብር አካል ናቸው።

በተለይ የወራጅነት ሥጋት ያለባቸው ኢትዮ-ኤሌክትሪክ፣ አርባ ምንጭ ከነማ፣ ድሬዳዋ ከነማ፣ ወላይታ ዲቻ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጨዋታውን በትኩረት የሚጠብቁት ይሆናል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
40 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 670 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us