ሚሱት ኦዚል አዲሱ የአርሴናል 10 ቁጥር ለባሽ ሆነ

Wednesday, 11 July 2018 13:27

 

ከጉዳት ጋር የሚታገለውና የአርሴናል አካዳሚ ፍሬ የሆነው እንግሊዛዊው ጃክ ዊልሼር ወደ ዌስትሃም ዩናይት ሊዘዋወር መሆኑን ተከትሎ ጀርመናዊው ሜሱት ኦዚል ለዓመታት ሲመኘው የነበረውን 10 ቁጥር ማሊያ ተረከበ።

በአርሴናል 196 ጨዋታ አካሂዶ 37 ጎሎችን ያስቆጠረውና ከ60 በላይ ኳሶችን ለአጥቂዎች ጣጣቸውን ጨርሶ ያቀበለው መልከ መልካሙ አማካይ፤ ከቀጣዩ የውድድር ዓመት ጀምሮ በአዲስ የማሊያ ቁጥር የሚታይ ይሆናል።

ታጋይነት ይጎድለዋል እየተባለ ትችት የሚወርድበት ቢሆንም ለትችቶች መስሚያ የሌለው ጀርመናዊ አማካይ በሚሊ ሜትር የተመጠኑ ኳሶችን ለአጥቂዎች በማቀበል ከፕሪሚየር ሊጉ ቀዳሚው ተጫዋች ነው። ካለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ጀምሮ ሰሜን ለንደኖቹን የተቀላቀለው ጋቦናዊው አጥቂ ፔር ኤምሪክ ኦባሚያንግ የሜሱት ኦዚልን ምጥን ኳሶች በአግባቡ መጠቀም ከቻለ ክለቡን ለድል ራሱንም ለኮከብ ጎል አግቢነት ያበቃል የሚሉ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል። አርሴናል ከጃክ ዌልሸር በተጨማሪም ሳንቲ ካዞርላን እና ፍራንሲስ ኮክለን ያሰናበተ በመሆኑ ለቦታው ኡራጋዊውን ካርሎስ ቶሬራን ከሳምፕዶሪያ አስፈርሟል።

ከጀርመኑ ቦርሲያ ዶርትመንድ ደግሞ ግሪካዊውን ተከላካይ ሶቅራጥስን፣ ከጁቬንቱስ ደግሞ ስዊዘርላንዳዊውን የቀኝ መስመር ተከላካይ ሌችተንስታይንን እና ከባየር ሊቨርኩሰን ደግሞ ግብ ጠባቂውን በርናንድ ሌኖን አስፈርሟል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
115 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 500 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us