“ለአኩራፊ ምሳው. . .”

Wednesday, 23 March 2016 12:23

እንደምን ሰነበታችሁ ወዳጆቼ!?. . . እኔ የምለው ፈረንጆቹ “ጊዜ ወርቅ ነው” የሚሉት ነገር እኛ ዘንድ እውን የሚሆነው መቼ ነው?. . . ግራ ግብት እኮ ነው የሚላችሁ፤ በህይወት ውስጥ የጊዜ ዋጋ በተጨባጭ የሚታይ ቢሆንም እኛ ዘንድ ግን ጊዜ ዋጋው በጣም ቀላል ከሆነ ሰነባብቷል። የጊዜ ነገር ከተነሳ አይቀር ቀጠሮን ማስታወስ ይቻላል። ስለቀጠሮ ሲነሳ ደግሞ የክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የምትመቸኝ ዘፈን ምን ትላለች መሰላችሁ፡-

“አርቆ ማሰቢያ እያለን አእምሮ

እንደምን ተሳነን ለማክበር ቀጠሮ?

ቸልተኞች ሆነን ወደኋላ እንዳንቀር

በሁላችንም ዘንድ ቀጠሮ ይከበር።”

እስቲ አሁን ማነው ቀጠሮን የሚያከብር? አንዳንዴ ሳስበው በመዘግየት ልክፍት የታሰርን ይመስለኛል። ከስራ አንጻር እንኳን በፍጥነት ሲሰራ እንዴት ነው ነገሩ፤ አዲስ ነገር መጣ እንዴ? በሚል መደነቃችን ተለምዷል። . . . አንድ ነገር ጊዜ ካልፈጀ፤ ብዙ ካልቆየ፤ ካላደከመና ላባችን ጠብ እስኪል ካላለፍን የተሰራ የማይመስለን ስንቶች እንደሆን ቤቱ ይቁጠረን።

እንዚህች’ጋ ትዝብታችንን የምታዋዛልን አንዲት ጨዋታ እነሆ። ሰውዬው ጥርሱን ያመውና ወደጥርስ ሀኪም ቤት ይሄዳል። እዛም ጥርሱን ለማስነቀል የተጠየቀው ገንዘብ በጣም በመብዛቱ ይማረራል። ይሄኔ ታዲያ የጥርስ ሀኪሙን በንዴት እየተመለከተ፣ “እንዴት አንዲት ደቂቃ ለማይሞላ ስራ ይህን ያህል ብር ክፈል እባላለሁ?” ሲል ዶክተሩ ሲመልስላት ምን ቢለው ጥሩ ነው? “ግድ የለም አንተ ብሩን ክፈል እንጂ ደቂቃውን ወደሰዓት ማሳደግ አያቅተኝም”  ብሎላችሁ እርፍ። ቂ-ቂ-ቂ! ይህቺ ናት ጨዋታ!. . . የጊዜ ነገር የማይገባው ሰው ስቃዩንም ቢሆን ለማራዘም እንዲህ ሊደራደራችሁ ይችላል። ጎበዝ ጊዜና ዕውቀት እኮ በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው አንጡራ ሃብቶቻችን ናቸው።

የጊዜ አጠቃቀም ችግር በተለይ ለህዝብ አገልግሎት በሚሰጡ መንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ እጅጉን የከፋ ነው። ባለጉዳይን ማንገላታትና ማመላለስ ስራቸው የሆነ ይመስል፤ ቀላሉን ስራ ጊዜ የሚወስድ ለማስመሰል (እየለፋ ነው ለማስባል) በሚል ትንሿን ጉዳይ ሳምንታት፣ ወራት ብሎም ዓመት ድረስ መለጠጥ የተለመደ ነው። . . . አንድ ጉዳይ ይዛችሁ ባለወንበሩ ጋር ስትሄዱ እርሳቸው ስብሰባ ላይ ናቸው፤ ስልጠና ላይ ናቸው፤  ከእንግዳ ጋር ናቸው፤ ብዙ መዝገቦችን እያዩ ናቸው፤ እየተባልን ስንቱን ጊዜ እንዳባከነው ባለጉዳይ የሆነ ያውቀዋል። ይህን የተሳሳተ የቢሮክራሲ አካሄድ ስላለመድነው ነው መሰለኝ አንድ ጉዳይ በቶሎ ሲያልቅ ከማስደሰቱ ይልቅ መደነቁ ይቀናናል። (እኔ የምለው ሰሞኑን “ጠቅላያችን” ከምሁራኑ ጋር ባደረጉት ውይይት “ስራ የሚያጓትት ከሌባ አይተናነስም” ማለታቸውን እንዴት አያችሁት?

እናላችሁ በጤናችን ጉዳይ ሳይቀር ከስራው ጥራት ይልቅ የሚወስደውን ጊዜ ለገንዘብ መደራደሪ ስናቀርበው ማየት ለጊዜ ያለንን ዋጋ ቁልጭ የሚያደርገው ይመስለኛል። . . . አንድ ስራ በምን ያህል ፍጥነትና በምን ያህል ጥራት አለቀ ብሎ ከማሰብ ይልቅ. . . ይህቺህ ለመስራት ነው እንዴ ይሄን ሁሉ ገንዘብ የምጠየቀው ማለታችን ይደንቃል?

እንዲህ ሆነ፤ በቅርቡ የሞባይል ጥገና አስፈልጎኝ ወደአንድ የሞባይል ማስጠገኛ አመራሁ። በስራ የተወጠረው ወጣቱ ባለሙያ ጊዜ ገንዘብ ሆኖለታል። አንድ ሌላ ሰው የተበላሸ ሞባይሉን ከሰጠውና ችግሩን ከመረመረ በኋላ “ትንሽ ዞር ዞር ብለህ ተመለስ ይሰራልሃል” አለው። ዋጋውን ተነጋግሮ ሰውዬው ከመሄዱ ሞባይሉን ከፍቶ ጥቂት ደቂቃዎችን ሲነካካ ቆየና ገጣጥሞ እንደነበረ መለሰው። ይሄን ጊዜ፣ “ችግሩ ይሄን ያህል በቀላሉ የሚፈታ ከሆነ ለምንድነው ሰውዬውን ቆይቶ እንዲመጣ ያደረከው? እዚሁ በቆመበት ሰርተህ አትሸኘውም ነበር?” ስል ጠየኩት። (የመስሪያ ቤቶቹ አላስፈላጊ ቢሮክራሲ እዚህም አለ እንዴ? በሚል አስተያየት ነበር ጥያቄዬን ያቀረብኩት) ወጣቱም ፈገግ እንደማለት እየቃጣው፣ “አየህ የኛ ሰው ብዙ ሰዓት ለፍተህ የሰራህለት ሲመስለው ብቻ ነው የጠየከውን ተገቢ ገንዘብ የሚከፍለህ፤ ካልሆነ ግን ‘ለዚህችማ ይሄን ያህል አልከፍልም’ እያለ የጭንቅላት ውጤትህን (ዕውቀትህን ማለቱ) ዋጋ ያሳጣዋል” አለኝ።

እንዲህ ስናወራ አንዲት ሴት መጣችና ሞባይሏ የድምጽ ችግር እንዳለበት ነግራው እንዲሰራላት ሰጠችው። የሆኑ ቁጥሮችን ነካቶ የድምፁን ችግር ከተመለከተ በኋላ፣ “ስፒከሯ ላልታ ነው፤ ይሰራሻል፤ መቶ ብር ትከፍያለሽ” አላት። አያጣላንም ግን ሰለምቸኩል አሁኑኑ ሰርተህ ስጠኝ አለችው” ወደኔ አይቶ ፈገግ እንደማለት ሲቃጣው፤ ከኔ አስቀድሞ እንዲሰራለት መስማማቴን በአይን ጥቅሻ አሳየሁት። ልጅቱ እዛው እንደቆመች ሞባይሏን ፈትቶ የሆነ ነገሩን ከነካካና ካጠባበቀው በኋላ ገጣጥሞ ሰጣት፡ በሁኔታው የተገረመች በመምሰል፣ “በቃ ሰራኸው?” ጠየቀች። “አዎ ከፈለግሽ ደውለሽበት መሞከር ትችያለሽ” አላት። እናም እዛው ቆማ ወደጓደኛዋ ጋር ከደወለችና የድምጽ ችግሩን መቀረፉን ካወቀች በኋላ ስልኩን ዘግታ ቦርሳዋን እየከፈተች ምን ብትለው ጥሩ ነው? “አሁን ለዚህች ስራ ነው መቶ ብር የጠየከኝ?” (ሁለታችን ታያይተን እንደመሳቅ ቃጣን). . . ከተሰራው ስራ ጥራት ይልቅ በፍጥነት መሰራቱና የእርሷ ጊዜ መቆጠቡ ከግምት አልገባም። ደግሞም እርሱ ሲሰራው ቀላል የመሰላት ነገር እርሷ የተቸገረችበት እንደሆነ መርሳቷን ሳስበው፤ “የኛ ሰው ለጊዜና ለዕውቀት ያለው ዋጋ አስተዛዛቢ ነው” አልኩኝ በልቤ። እናላችሁ የአገራችን ሰው፣ “ለአኩራፊ ምሳው እራቱ ይሆናል” ይሉት ነገር ይሄኔ ትዝ ይለኛል። ቸር እንሰንብት።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
804 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 815 guests and no members online

Archive

« September 2018 »
Mon Tue Wed Thu Fri Sat Sun
          1 2
3 4 5 6 7 8 9
10 11 12 13 14 15 16
17 18 19 20 21 22 23
24 25 26 27 28 29 30

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us