የአርቲስት ወጋየሁ ደግነቱ አልባሳት ለመቄዶኒያ ተበረከተ

Wednesday, 20 July 2016 14:10

የአንጋፋው አርቲስት ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ ቤተሰቦች የአርቲስቱን አልባሳት ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መረጃ ማዕከል ባሳለፍነው ቅዳሜ ሐምሌ 8 ቀን 2008 ዓ.ም አበረከቱ። የአርቲስት ሻለቃ ወጋየሁ ደግነቱ 7ኛ ሙት አመትን ምክንያት በማድረግ ቀኑን ከማዕከሉ ጋር ያሳለፉት ቤተሰቦቹ ከአርቲስቱ አልባሳት በተጨማሪ የ10ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ፣ እንዲሁም የመኮረኒና የመመገቢያ ሰሃኖችን በስጦታ ማበርከታቸው ታውቋል። ላበረከቱት አርአያነት ያለው ተግባርም ማዕከሉ ምስጋናውን ለቤተሰቦቻቸው ገልጿል። አርቲስት ወጋየሁ ደግነቱ ከአንጋፋዎቹ ጥላሁን ገሰሰና መሐሙድ አህመድ ጋር የሰራና በርካታ ዜማዎችንም የተጫወተ ከያኒ እንደነበር ይታወቃል።

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
203 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us