“ተፈፀመ” በሉን!!!

Wednesday, 12 April 2017 12:18

 

ትንሽ ቤት ሰራሁ እንዳቅመኛ

 ሁለት ሶስት ሰው የሚያስተኛ

አላስገባ አለች እሷም ጠባ

ሰው በሰው ላይ እየገባ።

     (ከአርቲስት ቴዎድሮስ ታደሰ “ዘለሰኛ” የተወሰደ)

እንኳን ለፋሲካ በዓል አደረሳችሁ!!!. . . የበዓሉ ሽር-ጉድ እንዴት ይዟችኋል?. . . መቼም የፋሲካ በዓል በህዝበ ክርስትያኑ ዘንድ ብዙ ትርጉም አለው። ከውርስ ኃጢያታችን ይቅር የተባልንበት፤ ክርስቶስ በሞቱ ሞታችንን ድል የነሳበት፤ የኃጢያት ዘመናችንን ሁሉ በቃችሁ የተባልንበትና ነገራችን የተፈፀመበት ወቅት ነው።. . . የክርስትና መስረት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዓለም የመጣበትን ተልዕኮ ሁሉ እንደተናገረው ፈፅሟል።

መፅሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ መከራ መቀበልና ፍፃሜ በተመለከተ እንዲህ ይላል፤ “ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈፀመ አውቆ የመፅሐፉ ቃል ይፈፀም ዘንድ ተጠማሁ አለ፡፤ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በስፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድገው ወደ አፉ አቀረቡለት። ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ “ተፈፀመ” አለ። ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። (ዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 19÷18-20)

ይህ የክርስቶስ ተግባር በህይወታችን በእጅጉ ሊገለጥ የሚገባው ነው። ሂደቱ መራራም ቢሆን በቃሉ መሰረት ህይወቱን ለኛ አሳልፎ በመስጠት “ተፈፀመ” ብሎናል። .  . . እኛ ግን ይህው ከዘመናት በኋላም ቢሆን ሊፈፀሙ የሚገባቸው ብዙ እቅዶችን በእንጥልጥል ወይም በጅምር አስቀርተን “ተፈፀመ” የሚለንን እንናፍቃለን። እናም በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ጉዳዮቻችን ዙሪያ “ተፈፀመ” የሚለን ተቋም እንፈልጋለን። ተደጋግመው የሚሰሙ የመልካም አስተዳደና የፍትህ ችግሮች አሉብን፤ አቤት ባልነው ልክ ሰምቶ ችግሮቻችን “ተፈፀመ” የሚለን አመራር እንፈልጋለን። ብዙ አይነት በሽታዎች አሉብን። ከምርመራ፣ ከመርፌና ከመድሃኒት በኋላ (ብዙ ገንዘባችንን ወስዶብን ቢሆንም እንኳን) የህመማችንን  ነገር “ተፈፀመ” “ከህመማችሁ ተፈውሳችሁ” የሚለን ሀኪምና የህክምና ተቋማት እንፈልጋለን። ይቅር ባይነትንና መቻቻልን የሚያሳውቁ የሃይማኖት አባቶችና ተቋማት እንፈልጋለን። ያኔ የግጭት መንገዳችን ሳይረዝም “ተፈፀመ” የምንልበት ጊዜ ይመጣል። . . . እናላችሁ እንደ ኢየሱስ ነፍስን እስከመስጠት ባይደርስ እንኳን ቃል የተገቡልን የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በተግባር መሬት ወርደው ችግሮቻችንን “በቃችሁ” የሚለን እንፈልጋለን።

እኛው ራሳችን ተጋግዘን ይህን ክፉ ጊዜ ማለፍ እስካልቻልን ድረስ የባሰው ይመጣና ለሁላችንም የማይጥም፤ ለሁላችንም የማይመጥን ህይወት ሊገጥመን ይችላል። በግፍ የተጫነው ሁሉ ሲወርድ ገፈቱ ለናንተም ነውና።. . . እናም “ፋሲካውን” ምክንያት አድርገን አንድዬ “ተፈፀመ” እንዲለን ሁሉ እኛም እርስ በእርሳችን ክፋትና ተንኮል፣ ቂምና በቀልን “በቃን” ብንባባል ምን ይለናል ጎበዝ!?

ይህቺን ታሪክ የምታጎላ አንዲት ወግ ከኤዞፕ ተረቶች መካከል የምትከተለዋን እንመዛለን።. . . በአንድ ሀገር የሚኖር ከበርቴ ነጋዴ ነበር። እሱም አንድ ፈረስና አህያ ነበሩት። በሁለቱም እንስሳት እየጫነም ይገለገል ነበር። ሆኖም ብዙ ብጭናቸው ብዙ አገኛለሁ በማለት ከባድ ዕቃ ይጭናቸዋል። ወጪ ለመቀነስ ሲልም በቂ ጥራጥሬ በማቅረብ ፈንታ ወደሜዳ ወስዶ ሳር እንዲመገቡ ያደርጋቸዋል።

ከዕለታት አንድ ቀን ከአቅም በላይ ጭኗቸው ወደገበያ ሄደ። አህያውና ፈረሱ በሜዳው ላይ ያለምንም ችግር ተጓዙ። መንገዱ ዳገትና ቁልቁለት እንዲሁም ኮረኮንች ሲሆን ግን በተለይ አህያው ደከመ። መሄድ ሳያቅተውም ወደፈረሱ ጠጋ አለና ከጭነቱ ትንሽ ወስዶ እንዲያግዘው ጠየቀው። ፈረሱ ግን፣ “ትቀልዳለህ እንዴ ለራሴ ከብዶኛል አንተ ደግሞ አግዙኝ ትላለህ። እባክህ ራስህን ቻል” ሲል መለሰለት።

አህያው እንደገና “በእርግጥ የተሸከምከው ዕቃ ከባድ ነው። ነገር ግን እንደኔ አልከበደህም። ከኔ ትንሽ ወስደህ ብታግዘኝ ደግሞ እንደኔ አትደክምም” ሲል ለመነው። ፈረሱ ግን በጭራሽ አይሆንም አለ። ነጋዴውም ቢሆን አህያው መድከሙን እያየ አልረዳውም። እንዲያውም ወደፊት እንዲሄድ እየመታ ገፈተረው። በመጨረሻም አህያው ተደናቀፈና ወደቀ። ከወደቀበት ሳይነሳ ቀረ፤ ሞተ።

ባለአህያው በጣም ተናደደ። ነገር ግን ምንም ለማድረግ አለመቻሉን ሲረዳ የአህያውን ጭነት አወረደና በፈረሱ ላይ ጫነው። ቆዳውንም ለመሸጥ ገፈፈና ከሁሉም ጭነቶች በላይ ደረበው። ትንሽ አግዘኝ ብሎ ቢለምነው አይሆንም ብሎ ሁሉንም በመጫኑና ከዚያም በላይ እርጥብ ቆዳው የተጨመረበት ፈረስ፣ “ይበለኝ ዋጋዬን ነው ያገኘሁት። በመጀመሪያ ሲደክም ትንሽ ወስጄ ባግዘው ኖሮ እሱም አይሞትም። እኔም የሱን ሸክም በሙሉ አልጫንም ነበር” እያለ በፀፀት ተጓዘ ይባላል። . . . እናላችሁ ጎበዝ ኑሮ አድክሞናልና ብንተጋገዝ ምን ይለናል?. . .

እናም የኑሮ ክብደት እያንገዳገደን ነውና ከልብ በላይ ተጨነናልና ብንተጋገዝ መልካም ነው። ፈጣሪ ኃጢያታችንን “በቃችሁ” እንዳለን፤ መከራችሁም “ተፈፀመ” እንዳለን ሁሉ በመልካም አስተዳደርና በሥነ-ምግባር ጉድለት ምክንያት ተጀምረው ያልተፈፀሙ ፕሮጀክቶችን ሸክሙ የከበደብንን ኑሮ ፈፅሙልንና በማቅለል “ተፈፀመ!!!” በሉን። መልካም የትንሳኤ በዓል፤ ቸር እንሰንብት!!!

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
332 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 922 guests and no members online

Archive

« September 2018 »
Mon Tue Wed Thu Fri Sat Sun
          1 2
3 4 5 6 7 8 9
10 11 12 13 14 15 16
17 18 19 20 21 22 23
24 25 26 27 28 29 30

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us