የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ?

Wednesday, 22 June 2016 12:11

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ በማዘጋጀት በየደረጃው የሚመለከታቸው ወገኖች እንዲወያዩበት በማድረግ ላይ ይገኛል። ረቂቅ አዋጁ በተለይ የሠራተኞች የደመወዝ ገቢ ግብር በከፍተኛ ደረጃ ያሻሻለ ሲሆን እስከሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ጸድቆ ወደሥራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የረቂቅ አዋጁን ዋና ጭብጦች አለፍ አለፍ እያልን እንቃኛቸዋለን።

 

እንደ መግቢያ

የአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት ከደረሰበት ደረጃ ጋር የተጣጣመ እና የኢኮኖሚውን ዕድገት የሚያግዝ ዘመናዊና ቀልጣፋ የግብር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣ የግብር አከፋፈሉ ሥርዓት ፍትሀዊነት ያለው እንዲሆን እና ግብር የማይከፈልባቸው ገቢዎች በግብር መረብ ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቷል።

 

ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ስለመጣል

1. ማናቸውም ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከመቀጠር ከሚያገኘው ጠቅላላ የወር ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 በተወሰኑት መጣኔዎች መሠረት በእያንዳንዱ ወር ግብር ይከፍላል።

2.  በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ከመቀጠር በሚገኝ ወርሀዊ ገቢ ላይ የሚጣለው የገቢ ግብር ተቀጣሪው በአንድ ወር ውስጥ በሚያገኘው ጠቅላላ ወርሃዊ ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 መሠረት ተፈጻሚ የሚሆነውን መጣኔ መሠረት በማድረግ ይሰላል።

3.  ተቀጣሪው በመቀጠር የሚገኘውን ገቢ ለማግኘት የሚያወጣው ማንኛውም ወጭ በተቀናሽ ሊያዝለት አይችልም።

4.  ለዚህ ሠንጠረዥና ለዚህ አዋጅ አንቀጽ 86 አፈጻፀም ሲባል፤ በነሐሴና በጳጉሜ ወራት የሚከፈለው የቅጥር ገቢ ተደምሮ እንደ የአንድ ወር ደመወዝ ግብር ይከፈልበታል።

5.  በአንድ ተቀጣሪ ላይ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 81(1) ድንጋጌ ተፈጻሚ የተደረገ እንደሆነ በመቀጠር በተገኘው ገቢ ላይ ተቀጣሪው የከፈለው ታክስ የመጨረሻ ይሆናል። ቀጣሪው በአንቀጽ 86 መሠረት ከተቀጣሪው የሚፈለገውን የገቢ ግብር ቀንሶ ያስቀረ እንደሆነ ግብሩ እንደተከፈለ ይቆጠራል።

በመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች

ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ለሚጣለው ግብር ተፈጻሚ የሚሆኑት ምጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

በየወሩ ከመቀጠር

የሚገኝ ገቢ በብር

ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆን መጣኔ

0-585

0%

586-1,650

10%

1,651-3,145

15%

3,146-5195

20%

5,196-7,758

25%

7,759-10,833

30%

ከ10,833 በላይ

35%

    

 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ

1.  ዚህ አንቀጽዑስ አንቀጽ (2) እና (3) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ናቸው የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡-

ሀ/    ሠራተኛው ካለፈው፣ አሁን ካለው ወይም ወደፊት ከሚመጣው የቅጥር ውል ጋር በተያያዘ የሚያገኘው ደመወዝ፣ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ፣

ለ/    ያለፈን፣ የአሁኑን ወይም የወደፊትን ቅጥር አስመልክቶ ሠራተኛው የሚያገኘው የዓይነት ጥቅማ ጥቅም ዋጋ፣

ሐ/    የሠራተኛው የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በፍ/ቤት ውሳኔ አሠሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው ማንኛውም ክፍያ፣ እንዲሁም ከሥራ በመቀነስ ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈለው ክፍያ ወይም ሠራተኛው ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ ወይም ሥራውን እንዲለቅ በማግባባት የሚከፈል ገንዘብ፣

2.  በመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከግብር ነፃ የተደረገን ገቢ አይጨምርም።

3.  ማንኛውም ቀጣሪ ተቀጣሪው መክፈል የሚኖርበትን ግብር ከተቀጣሪው ገቢ ላይ ሳይቀንስ ራሱ ለተቀጣሪው በሙሉ ወይም በከፊል የከፈለለት እንደሆነ፣ በቀጣሪው የተከፈለው የግብር መጠን ተቀጣሪው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር በሚከፈልበት የገንዘብ መጠን ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል።

4.  የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከደመወዝ ሌላ በዓይነት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞች ዋጋ የሚወሰንበትንና ግብር የሚከፈልበትን ሁኔታ አስመልክቶ ደንብ ያወጣል።

ከቤት ኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ግብር ስለመጣል

1. ቤትበማከራየት ገቢ የሚያገኝ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14 በተመለከተው መጣኔ ወይም መጣኔዎች መሠረት በእያንዳንዱ የግብር ዓመት የኪራይ ገቢ ግብር ይከፍላል።

2.  በግብር ዓመቱ አንድ ግብር ከፋይ ከቤት ኪራይ በሚያገኘው ገቢ ላይ የሚከፈለው ግብር በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14 ሥር የተመለከቱትን መጣኔዎች ግብር በሚከፈልበት ዓመታዊ ገቢ ላይ ተፈፃሚበማድረግ ይሰላል።

3.  ይህ ሠንጠረዥ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 57 መሠረት የኪራይ ገቢ ግብር ለሚከፈልበት ገቢ ተፈጻሚነት አይኖረውም።

የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔዎች

1.  በድርጅቶችየኪራይገቢላይተፈጻሚየሚሆነውየግብርመጣኔ 30 በመቶነው።

2.  በግለሰቦች የኪራይ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑት መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው።

ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ በዓመት

የግብር መጣኔ

0-7,000

0%

7001-19,300

10%

19,301-37,750

15%

37,751-62,350

20%

62,351-93,100

25%

93,101-130,000

30%

ከ130,000 በላይ

35%

 

ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ

1. የአንድ ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ የኪራይ ገቢ ነው የሚባለው ግብር ከፋዩ በዓመቱ ውስጥ ቤት ወይምቤቶችን በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ነው።

2.  የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) እና (4) እንደተጠበቁ ሆነው፣ አንድ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ቤት ወይም ቤቶችን በማከራየት የሚያገኘውጠቅላላ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

ሀ/    የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ፣ በኪራይ ውሉ መሠረት ታክስ ከፋዩ በዓመቱ የሚያገኛቸው ማናቸውም ክፍያዎች፣

ለ/    በኪራይ ውሉ መሠረት ተከራዩ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች የሚከፍላቸው ክፍያዎች፤

ሐ/    ግብር ከፋዩ ጉዳቱን ለማስተካከል ያልተጠቀመበት እና በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ የያዘው እና በግብር ዓመቱ ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው ማንኛውም ቦንድ፣ ዋስትና ወይም ተመሳሳይ ገንዘብ፤

መ/   ለታክስ ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራዩ ውል መሠረት ተከራዩ ራሱ ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው ገንዘብ፤

3.  ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ፣ ግብር ከፋዩ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል።

4.  ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት የሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከገቢ ግብር ነጻ የሆነን ገቢ አይጨምርም።

5.  በአንድ የግብር ዓመት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለበት ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ የሚከተሉት ወጭዎች በተቀናሽ ይያዛሉ፡-

ሀ/    ታክስን ሳይጨምር  ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩለመንግሥት ወይም  ለከተማ አስተዳደር በግብር ዓመቱ ውስጥ የከፈላቸው ክፍያዎች፣

ለ/    ለቤቶች፣ ለቤት ዕቃና መሣሪያ ማደሻ፣መጠገኛና ለእርጅና መተኪያ የሚሆን ከቤት፣ ከቤት ዕቃ እና ከመሳሪያ ኪራይ ከሚገኘው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ ሃምሳ በመቶ፣

6.  የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 ድንጋጌ በማናቸውም ምክንያት በዚህ አዋጅ መሠረት የሂሣብ መዝገብ የመያዘ ግዴታ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም።

7.  የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ግብር ከፋይ የዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ ገቢውን ለማግኘት የወጣና በታክስ ከፋዩ የተከፈለ ወጭ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም ወጪየሚከተሉትን ይጨምራል፡-

ሀ/ ቤቱ ያረፈበት መሬት ኪራይ፣

ለ/ የጥገና ወጭ፣

ሐ/ የቤቱ፣ የቤት ዕቃዎችናየመሣሪያዎች የእርጅና ቅናሽ፣

መ/ ወለድና የመድን አረቦን፣

ሠ/ ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩለመንግሥት ወይም ለከተማ አስተዳደር የከፈላቸው ክፍያዎች፣

 

የተከራይ አከራዮች

1.  ተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራዩ በግብር ዓመቱ ከሚያገኘው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይየሚከፍለው ኪራይከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው ገንዘብ ነው።

2.  ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል።

የሚከራይ አዲስ ቤትን ስለማሳወቅ

1.  ለኪራይ የሚሰራ ቤት ተሰርቶ እንዳለቀ ወይም ቤቱ እንደተከራየ፣ ከሁለቱ በሚቀድመው ጊዜ የቤቱ ባለቤትና የቤቱ ሥራ ተቋራጭ የቤቱ ግንባታ የተጠናቀቀወይም የተከራየ መሆኑን ከቤቱ ኪራይ በሚገኘው ገቢ ላይ የሚፈለገውን ግብር መክፈል ያለበትን ሰው ስም፣ አድራሻና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ቤቱ ለሚገኝበት የቀበሌ አስተዳደር ወይም የአካባቢ አስተዳደር ማስታወቅ አለበት።

2.  የቀበሌው አስተዳደር እና የአካባቢው አስተዳደር በማስታወቂያው መሠረት የተገኘውን መረጃ ለባለሥልጣኑ መግለጽ አለባቸው።

ከንግድ ሥራዎች በሚገኝ ገቢ ላይ ግብርን ስለመጣል

1.  በዚህ ክፍል የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ያለው ሰውበእያንዳንዱ የግብር ዓመት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 19 በተመለከተው መጣኔ ወይም መጣኔዎች መሠረት የንግድ ገቢ ግብር ይከፍላል።

2.  አንድ ግብር ከፋይ በአንድ የግብር ዓመት የሚከፍለው የንግድ ሥራ ገቢ ግብር የሚሰላው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 19 የተመለከተው መጣኔ ወይም መጣኔዎች በግብር ከፋዩ የዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ ተፈፃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ነው።

ከንግድ ሥራ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎች

1.  በድርጅት ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የንግድ ሥራ ገቢ የግብር መጣኔ ሰላሳ በመቶ (30%) ነው።

2.  በግለሰቦች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የንግድ ሥራ ገቢ መጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው።

ከንግድ ሥራ የሚገኝ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በዓመት

የግብር ምጣኔ

0-7,000

0%

7,001-19,300

10%

19,301-37,750

15%

37,751-62,350

20%

62,351-93,100

25%

93,101-130,000

30%

ከ130,000 በላይ

35%

 

3.  የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ቢኖርም ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ግብር የሚከፍሉት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ሥር በተመለከቱት መጣኔዎች መሠረት ይሆናል።

4.  ለዚህ አንቀጽ አፈፃፀም "ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ" በፌዴራል የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲን ለማቋቋም በወጣው የሚነስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 201/2003 የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል።

ግብር የሚከፈልበት ገቢ

1.  የአንድ ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ የንግድ ሥራ ገቢ ነው የሚባለው ከንግድ ሥራ ከተገኝ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀዱት ወጭዎች ተቀናሽ ከተደረጉ በኋላ የሚገኘው የገቢ መጠን ነው።

2.  በዚህ አዋጅ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣቸው ደንቦች እና ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ የሚደረጉ ማሻሻያዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ የአንድ ግብር ከፋይግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ ገቢ የሚወሰነው ግብር ከፋዩ በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሠረት በሚያዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም ገቢ መግለጫ ላይ በመመስረት ይሆናል።

ከንግድ ሥራ የሚገኝ ገቢ

1.  በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፤ በአንድ የግብር ዓመት የአንድ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ከፋይ የንግድ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

/    ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በመሸጥና በመለወጥ የሚያገኘውን ገቢ ጨምሮ (ከመቀጠር የሚገኝ ገቢን ሳይጨምር) በግብር ዓመቱ ግብር ከፋዩ ከንግድ ሥራ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ፣

/    የትርፍ ድርሻን፣ ወለድን እና ሮያሊቲን ጨምሮ የንግዱን ሀብት ሥራ ላይ በማዋል  ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የሚያገኘው ጠቅላላ ገንዘብ፣

/ በግብር ዓመቱ የንግድ ሀብትን (ለንግድ የሚውል እቃን ሳይጨምር) በመሸጥ ወይም በመለወጥ የሚገኝ ገቢ፤

/በዚህ አዋጅ መሠረት ለግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርጎ የሚወሰድ ሌላ ማንኛውም ገቢ፤

2.  ከንግድ ሥራ የሚገኝ ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገን ገቢ አይጨምርም።

3.  የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1(ሐ) መሠረት በንግድ ገቢ ውስጥ የሚካተተው የንግድ ሀብትን በመሸጥ ወይም በመለወጥ የሚገኝ ገቢ ከንግድ ሀብቱ የመዝገብ ዋጋ በላይ የሆነው የንግድ ሀብቱ በሚሸጥበት ጊዜ ከተሸጠው ወይም ከተለወጠው ሀብት የተገኘው ገቢ ነው።

4.  አንድ የንግድ ሥራ ሃብት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 58 መሠረት ግብር የሚከፈልበት ከሆነ፡-

ሀ/    በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1(ሐ) መሠረት በንግድ ሥራ ገቢ ውስጥ የሚካተተውን የንግድ ሥራ ሀብትን በማስተላለፍ የሚገኝ ገቢ በሚመለከት ለንግዱሀብትየተደረገው ወጪ ከንግዱሀብት የመዝገብ ዋጋ በሚበልጠው የገንዘብ መጠን፣ እና

ለ/    ከወጪው በላይ በሚገኘው ጥቅም ላይ በአንቀጽ 58 መሠረት ግብር ይከፈልበታል።

 

ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች

1.  የዚሀ አዋጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ በግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩን ግብር የሚከፈልበት ገቢ ለመወሰን በተቀናሽ የሚያዙት ወጪዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-

/    በንግድ ገቢው ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት፣ ለንግዱ ዋስትና ለመስጠትና የንግድ ሥራውን ለማስቀጠል  በግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ውስጥ የተደረጉ አስፈላጊየሆኑወጪዎች፤

/    በፋይናንሽያል ሪፖርት ደረጃዎች በተመለከተው መሠረት የተሠላ  በግብር ዓመቱ በግብር ከፋዩ ለተሸጠ የንግድ ዕቃ የወጣ ወጭ፤

/    በዚህ አዋጅ አንቀጽ 25 በሚወሰነው መሠረት የንግድ ገቢን ለማግኘት ሥራ ላይ የዋሉ ዋጋቸው የሚቀንስ ንብረቶች እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው የንግድ ሀብቶች በግብር ዓመቱ የሚታሰበው ጠቅላላ የእርጅና ቅናሽ፣

/   ግብር ከፋዩ የንግድ ዕቃን ሳይጨምር በግብር ዘመኑ የንግድ ሥራ ሀብትን ሲሸጥ ወይም ሲለውጥ የሚገጥመው ኪሳራ፣

ሠ/    ለግብር ዘመኑ በዚህ አዋጅ መሠረት ለግብር ከፋዩ በተቀናሽነት የሚፈቀድ ሌላ ማናቸውም ወጭ፣

2.  ግብር የሚከፈልበት ሃብት የእርጅና ቅናሽ የሚታሰብበት ካልሆነ በስተቀር፣ ግብር የሚከፈልበት ሃብት በሚተላለፍበት ጊዜ ለሚደርስ ኪሳራ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 58 ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን የዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ(1) ግን ተፈጻሚ አይሆንም።

3.  ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1(መ) አፈጻፀም፤ የንግድ ሀብትን በማስተላለፍየሚደርስ ኪሳራ የሚባለው ሀብቱ በተሸጠበት ጊዜ የሀብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ሀብቱ ከተላለፈበት ዋጋ በሚበልጠው የገንዘብ ልክ ነው።

ወለድ ለመክፈል የሚወጣ ወጭ

1.  የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 እና የዚህ አዋጅ አንቀጽ 46 እንደተጠበቁ ሆነው፤  ግብር ከፋዩ የወሰደውን ብድር ወይም ሌላ ዕዳ ወይም ያደረገውን ስምምነት የንግድ ገቢውን ለማግኘት ተግባር ያዋለው እንደሆነ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተከፈለው ወለድ የግብር ከፋዩ ዓመታዊ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚወሰንበት ጊዜ እንደወጪ ይያዝለታል።

2.  ለሚከተሉት ወጭዎች ተቀናሽ አይፈቀድም፡

ሀ/   ወለዱ በብሔራዊ ባንክ እና በንግድ ባንኮች መካከል በተደረገ ብድር ከሚታሰብ የወለድ መጣኔ 2% የሚበልጥ ከሆነ በተቀናሽ አይያዝም፤ ነገር ግን ወለዱ በተቀናሽ የሚያዘው፡

3.  በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ለተሰጠው የገንዘብ ተቋም የተከፈለ ወይም

4.  በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሰዎች ብድር እንዲሰጥ ለተፈቀደለት የውጭሀገርባንክ የተከፈለ ከሆነ፣

ለ/    የወለዱ ገቢ ግንኙነት ባለው ሰው የንግድ ገቢ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ውስጥ ካልተካተተ በስተቀር፣ አንድ ግብር ከፋይ በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆነ ግንኙነት ላለው ሰው የከፈለው ወይም የሚከፍለው ወለድ፣

 

ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች

1. የግብር ከፋዩ ግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ ገቢ በሚወሰንበት ጊዜ ግብር ከፋዩ ያደረገው ስጦታ ተቀናሽ የሚደረገው ስጦታው ለሚከተሉት የተደረገ ሲሆን ነው፡-

ሀ/    በዚህ አዋጅ አንቀጽ 63 ትርጉም ለተሰጠው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት፣ ወይም

ለ/    መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሠረት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስከበር፣ ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ለመከላከል ወይም ለተመሳሳይ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት የተደረገ ከሆነ፣ ነው።

2.  በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት ለግብር ከፋዩ የሚፈቀደው ጠቅላላ ተቀናሸ ከግብር ከፋዩ ግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ ገቢ 10% (አሥር በመቶ) መብለጥ የለበትም።

የእርጅና ቅናሽ

1.  ግብር ከፋዩ ግብር የሚከፍልበትን ዓመታዊ  ገቢ ለመወሰን ግብር ከፋዩ ገቢውን ለማስገኘት ጥቅም ላይ ላዋላቸው  እና ዋጋቸው ለሚቀንስ ንብረቶች እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው የንግድ ሀብቶች የእርጅና ቅናሽ ለማድረግ ይፈቀድለታል።

2.  የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ፣ ዋጋቸው ለሚቀንስ ንብረቶች እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው የንግድ ሀብቶች በየዓመቱ የሚደረገው የእርጅና ቅናሽ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል።

3.  አንድ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ በሙሉ የንግድ ገቢውን ለማግኘት ዋጋቸው የሚቀንስ ንብረቶችን ወይም ግዙፋዊ ሀልዎት የሌላቸውን ሀብቶች ያልተጠቀመ እንደሆነ በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚደረገው የእርጅና ቅናሽ የሚሰላው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ሆኖ፣ የንግድ ሀብቱ ጥቅም ላይ ያልዋለበት ዓመት ሂሣብ ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ከተቀነሰ በኋላ ነው።

4.  አንድ ግብር ከፋይ በአንድ የግብር ዓመት  ውስጥ ዋጋው የሚቀንስ ንብረት እና ግዙፋዊ ህልዎት የሌለው ሀብት በከፊል የገቢ ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለማግኘት በከፊል ደግሞ ለሌላ አገልግሎት የተጠቀመበት እንደሆነ በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚደረገው የእርጅና ቅናሽ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሠረት የሚደረገው ማስተካከያ ከግምት ውስጥ ገብቶ በንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት የንግድ ገቢውን ለማግኘት በዋለው መጠን የሚሰላ ይሆናል።

5.  አንድ ግብር ከፋይ በአንድ የግብር ዓመት ውስጥ ዋጋው የሚቀንስን ንብረት እና ግዙፋዊ ሀልዎት የሌለው የንግድ ሀብት በከፊል የገቢ ግብር የሚከፈልበትን ገቢ ለማስገኘት በከፊል ደግሞ ለሌላ አገልግሎት ከተጠቀመበት በኋላ ይህንን ሀብት በዚያው የግብር ዓመት ውስጥ የሸጠው ወይም የለወጠው እንደሆነ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 21(1(ለ) ወይም 21(1(መ) የተደነገገው የትርፍ ወይም የኪሳራ መጠንየሚሠላው የንግድ ሥራው ያጋጠመው የትርፍ ወይም የኪሳራ መጠን ለንግድ ሥራው ገቢ በነበረው አስተዋጽኦ መጠን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እየተከፋፈለ ይሆናል።

6.  ዋጋቸው የሚቀንስ ንብረቶች ወይም ግዙፋዊ ሀልዎት የሌላቸው የንግድ ሀብቶች የእርጅና ቅናሽ መታሰብ የሚጀምረው ሀብቱ የንግድ ገቢውን ለማስገኘት ለአገልግሎት ዝግጁ ከሆነበትና አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ቀን አንስቶ ሲሆን፣ በግብር ከፋዩ የተገነባ ህንፃ በሚሆንበት ዜ ተቆጣጣሪው ባለስልጣን ለግብር ከፋዩ የህንፃው ግንባታ መጠናቀቁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከሰጠበት ቀን በፊት ሊሆን አይችልም።

በዚህ አንቀጽ ውስጥ፣

“ግዙፋዊ ሀልዎት የሌላቸው የንግድ ሃብቶች” ማለት በሙሉ ወይም በከፊል የንግድ ገቢን ለማስገኘት የሚውሉ የሚከተሉት ሀብቶች ናቸው።

ሀ/    የቅጅ መብት፣ ፓተንት፣ ዲዛይን ወይም ሞዴል፣ ፕላን፣ ምስጢራዊ ቀመር ወይም የአሠራር ሂደት፣ የንግድ ምልክት፣ ወይም ለተወሰነ ዘመን ብቻ የሚያገለግል ሌላ ተመሳሳይ ንብረት፣

ለ/    የደንበኞች ዝርዝር፣ የሥርጭት መስመር ወይም የተለየ ስም፣ ምልክት ወይም ስዕል ወይም ለተወሰነ ዘመን ብቻ የሚያገለግል ሌላ ግዙፋዊ ሀልዎት የሌለው የንግድ ዘይቤ፣

ሐ/    ከአንድ ዓመት በላይ ሆኖ ለተወሰነ ጊዜ የሚያገለግል ከውል የሚመነጭ መብት (ወጭው አስቀድሞ የተከፈለንም ጨምሮ)፣

መ/ ማንኛውንም ግዙፋዊ ሀልዎት ያለውን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ  ንብረት ለማግኘት የወጣን ወጭ ሳይጨምር፣ ከአንድ ዓመት በላይ ጥቅም የሚሰጥ ወጭ፤

“ዋጋው የሚቀንስ ሀብት” ማለት የሚከተሉትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ግዙፋዊ ሀልዎት ያለው የሚንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን፣ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ማሻሻያንም ይጨምራል።

/    ከአንድ ዓመት የሚበልጥ የአገልግሎት ዘመን ያለው፣

/    በእርጅና ወይም ጊዜው በማለፍ ምክንያት ዋጋው ሊቀንስ የሚችል፤

/    በከፊል ወይም በሙሉ የንግድ ሥራ ገቢ ለማግኘት ጥቅም ላይ የዋለ፤

"በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ ማሻሻያ" ማለት ቤት፣ ወይም  ሌላ የቤቱ አካል የሚሆን ወይም ከቤቱ ጋር ለዘለቄታው የተያያዘ በቤቱ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ጭማሪ ወይም ለውጥ ሲሆን መንገድን፣ መጋቢ መንገድ፣ የመኪና ማቆሚያ አጥር ወይም ግንብን ይጨምራል።

 

ኪሳራን ስለማሸጋገር

1.  በዚህ አንቀጽ መሠረት የሚፈቀደውን ተቀናሽ ሳይጨምር፣ ለግብር ዓመቱ ተቀናሽ የሚደረገው ወጭ ግብር ከፋዩ በግብር ዘመኑ ካገኘው ጠቅላላ ገቢ ከበለጠ በብልጫ የታየው የገንዘብ መጠን ግብር ከፋዩ  የደረሰበት ኪሳራ ይሆናል።

2.  የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ኪሳራ ካጋጠመው፣ በግብር ዓመቱ የደረሰውን ኪሳራ ለሚቀጥለው የግብር ዓመት ለማሸጋገር ይችላል፤ ስለሆነም የግብር ከፋዩ የሚቀጥለው ዓመት ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ የተሸጋገረው ኪሳራ በተቀናሽነት ይያዛል።

3.  ግብር ከፋዩ ኪሳራውን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት ሙሉ በሙሉ  መቀነስ ያልቻለ እንደሆነ ያልተቀነሰውን ኪሳራ ለሚቀጥለው የግብር ዓመት ማሸጋገር እናየተካካሰውን መጠን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) በተገለጸው መሠረት በዚያው የግብር ዓመት ከተገኘው ጠቅላላ ገቢ ላይ በመቀነስ ኪሣራው ሙሉ በሙሉ ተቀናሽ ተደርጐ እስከሚያልቅ ድረስ ማሸጋገር የሚችል ሲሆን ነገር ግን ግብር ከፋዩ የደረሰበትን ኪሣራ ኪሣራው ከተከሰተበት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ከሚቆጠሩ አምስት የግብር ዓመታት በላይ ማሸጋገር አይችልም።

4.  ግብር ከፋዩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ለኪሳራ የተዳረገባቸው ሁለት ዓመታት ያሉ እንደሆነ እና እያንዳንዱ ኪሳራ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት የተሸጋገረ እንደሆነ ግብር ከፋዩ በንዑስ አንቀጽ 2 መሠረት ሌላ ማንኛውንም ተጨማሪ ኪሳራ እንዲያሸጋግር ሊፈቀድለት አይችልም።

5.  ግብር ከፋዩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) እና (3) የተመለከተውን ኪሳራ ሊያሸጋግር የሚችለው በገቢ ግብር ደንቡ በተመለከተው መሠረት ይሆናል።

ተቀናሽ የማይደረጉ ወጭዎች እና ኪሳራዎች

1.    በዚህ አዋጅ ከተደነገገው በስተቀር የሚከተሉት ወጭዎች በተቀናሽ አይያዙም፡-

/    በዚህ አዋጅ አንቀጽ 22(1)(ሐ)ከተደነገገው በስተቀር የካፒታልነት ባህርይ ያላቸው ወጭዎች፣

/    የኩባንያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሠረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጭ፣

/    ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15% (አሥራ አምስት መቶኛ) በላይ የሚደረግ የጡረታወይም የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ ፣

መ/   የአክሲዮን ድርሻ እና የትርፍ ድርሻ ክፍፍል፣

/    በመድን፣ በካሳ ወይም በዋስትና ውል መሠረት የተመለሰ ወይም ሊመለስ የሚችል ወጭ ወይም ኪሳራ፣

/    ማንኛውንም ሕግ ወይም ውል በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ወይም የሚከፈል ካሳ፣

/    ግብር ከፋዩ በሂሳብ መዝገቡ የሚይዘው በወቅቱ ወጭ ያልተደረገ ነገር ግን ወደፊት ለሚከሰቱ ወጭዎች ወይም ኪሳራዎች መጠባበቂያ ይሆን ዘንድ የሚያዝ ገንዘብ ወይም የመጠባበቂያ ሂሣብ፣

/በዚህ አዋጅ ወይም በውጭ ሀገር የታክስ ሕግ መሠረት የተከፈለ የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣

/ መሥሪያ ቤቱን ወክሎ በተለያዩ ቦታዎች ለሚገኝ ተቀጣሪ ከተቀጣሪው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ 10% (አሥር በመቶ) በላይ የሚከፈል የኃላፊነት አበል፣

/ከሚከተሉት በስተቀር ለመዝናኛ የሚወጣ ወጪ፣

  1. የግብር ከፋዩ የንግድ ሥራ የመዝናኛ አገልግሎት መስጠት ሲሆን፤ወይም
  2. ሚኒስቴሩ በመመሪያ ተቀናሽ እንዲደረግ በሚፈቅደው ልክ በማዕድን ማውጣት፣ በማኑፋክቸሪንግ ወይም በግብርና ሥራ የተሠማራ ቀጣሪ ሠራተኞቹን ለማዝናናት የሚያወጣው ወጪ፤

/    በአንቀጽ 24 ከተመለከተው ውጭ የሚደረግ ስጦታ ወይም እርዳታ፤

ቸ/    ግብር ከፋዩ አንድን የንግድ ሃብት ግንኙነት ላለው ሰው ሲሸጥ ወይም ሲለውጥ የሚደርስ ኪሳራ፣

/     ግብር ከፋዩ ለራሱ የሚያወጣው ወጭ፤

/    ሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ ተቀናሽ የማይደረጉ ናቸው የተባሉ ወጭዎች፣

2.    ግብር ቀንሶ የመያዝ ግዴታ ያለበት ሰው ግብር ቀንሶ የሚያስቀርበት ክፍያ በዚህ አዋጅ ክፍል አስር መሠረት በተቀናሽ የሚያዝ ወጭ የሆነ እንደሆነ፣ ተቀንሶ የተያዘው ግብር ለባለሥልጣኑ እስከሚከፈል ድረስ ይህ ገንዘብ በተቀናሽ እንዲያዝለት ሊጠይቅ አይችልም።

3.    በዚህ አንቀጽ "መዝናኛ" ማለት ለማንኛውም ሰው የሚቀርብ ምግብ፣ መጠጥ፣ ትንባሆ፣ ማረፊያ፣ መደሰቻ ወይም ማናቸውም ዓይነት መስተንግዶ ነው።¢

ይምረጡ
(11 ሰዎች መርጠዋል)
1991 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us