በዚህ ወር የሚተገበረው አዲሱ የደመወዝ ግብር

Wednesday, 27 July 2016 14:01

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በሕገመንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት የዘንድሮ ሥራውን ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም አብቅቶ ለዕረፍት ተበትኗል። ነገር ግን በም/ቤቱ የአባላት የሥነምግባር ደንብ አንቀጽ 15 መሠረት የም/ቤቱ አባላት በዕረፍት ላይ እያለ የም/ቤቱን ውሳኔ የሚሹ አስቸኳይ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ እንደሚችል በደነገገው መሠረት ትላንት ም/ቤቱ ተሰብስቦ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ አንዱ ሆኗል። አዋጁ በተለይ ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ ላይ የተጣለውን ምጣኔ በማሻሻል ከያዝነው ሐምሌ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል። ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ወይንም ደመወዝን በተመለከተ የአዋጁን ድንጋጌ የሚከተለውን አስቀምጧል።

 

ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ

ማናቸውም ተቀጣሪ በአንድ ወር ውስጥ ከመቀጠር ከሚያገኘው ጠቅላላ የወር ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 በተወሰኑት መጣኔዎች መሠረት በእያንዳንዱ ወር ግብር ይከፍላል።

በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት ከመቀጠር በሚገኝ ወርሀዊ ገቢ ላይ የሚጣለው የገቢ ግብር ተቀጣሪው በአንድ ወር ውስጥ በሚያገኘው ጠቅላላ ወርሃዊ ገቢ ላይ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 መሠረት ተፈጻሚ የሚሆነውን መጣኔ መሠረት በማድረግ ይሰላል። ተቀጣሪው በመቀጠር የሚገኘውን ገቢ ለማግኘት የሚያወጣው ማንኛውም ወጭ በተቀናሽ ሊያዝለት አይችልም። ለዚህ ሠንጠረዥና ለዚህ አዋጅ አንቀጽ 86 አፈጻፀም ሲባል፤ በነሐሴና በጳጉሜ ወራት የሚከፈለው የቅጥር ገቢ ተደምሮ እንደ የአንድ ወር ደመወዝ ግብር ይከፈልበታል።

በአንድ ተቀጣሪ ላይ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 81(1) ድንጋጌ ተፈጻሚ የተደረገ እንደሆነ በመቀጠር በተገኘው ገቢ ላይ ተቀጣሪው የከፈለው ታክስ የመጨረሻ ይሆናል። ቀጣሪው በአንቀጽ 86 መሠረት ከተቀጣሪው የሚፈለገውን የገቢ ግብር ቀንሶ ያስቀረ እንደሆነ ግብሩ እንደተከፈለ ይቆጠራል።

   የዚህ አንቀጽዑስ አንቀጽ (2) እና (3) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ናቸው የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡-

  • ሠራተኛው ካለፈው፣ አሁን ካለው ወይም ወደፊት ከሚመጣው የቅጥር ውል ጋር በተያያዘ የሚያገኘው ደመወዝ፣ ምንዳ፣ አበል፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ሌላ የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ፣
  • ያለፈን፣ የአሁኑን ወይም የወደፊትን ቅጥር አስመልክቶ ሠራተኛው የሚያገኘው የዓይነት ጥቅማ ጥቅም ዋጋ፣
  • የሠራተኛው የሥራ ውል በመቋረጡ ምክንያት በፈቃደኝነት፣ በስምምነት ወይም በፍ/ቤት ውሳኔ አሠሪው ለተቀጣሪው የሚከፍለው ማንኛውም ክፍያ፣ እንዲሁም ከሥራ በመቀነስ ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈለው ክፍያ ወይም ሠራተኛው ሥራውን በገዛ ፈቃዱ ሲለቅ ወይም ሥራውን እንዲለቅ በማግባባት የሚከፈል ገንዘብ፣
  • በመቀጠር የሚገኝ ገቢ ከግብር ነፃ የተደረገን ገቢ አይጨምርም።
  • ማንኛውም ቀጣሪ ተቀጣሪው መክፈል የሚኖርበትን ግብር ከተቀጣሪው ገቢ ላይ ሳይቀንስ ራሱ ለተቀጣሪው በሙሉ ወይም በከፊል የከፈለለት እንደሆነ፣ በቀጣሪው የተከፈለው የግብር መጠን ተቀጣሪው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር በሚከፈልበት የገንዘብ መጠን ላይ ተደምሮ ግብሩ ይሰላል።
  • የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከደመወዝ ሌላ በዓይነት የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞች ዋጋ የሚወሰንበትንና ግብር የሚከፈልበትን ሁኔታ አስመልክቶ ደንብ ያወጣል።

  

ይምረጡ
(16 ሰዎች መርጠዋል)
1409 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us