የመጀመሪያውብሔራዊ የሰብዓዊመብትየድርጊትመርሃግብርበመንግሥት ዕይታ

Thursday, 01 December 2016 15:38

·         የሞት ቅጣት 18 ዓመት ባልሞላቸው ታዳጊዎችና ነፍሰጡር ሴቶች ላይ አይፈፀምም፣

·         በሶስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከ57 ሺህ በላይ ታራሚዎች በይቅርታ ተፈተዋል፣

·         በአራት ዓመታት 470 አዳዲስ የሃይማኖት ተቋማት ሕጋዊ ሆነዋል፣

 

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃግብር (ከ2005-2007 ዓ.ም) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጸድቆ በሥራ ላይ መቆየቱ ይታወሳል። ሰነዱ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶችን፣ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ መብቶችን እንዲሁም ለመብት ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መብቶች (የሴቶች የህጻናት፣ የአረጋዊያን፣ ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች መብቶችን) እንዲሁ፣ም የልማትና የአካባቢ ደህንነት መብቶችን በዝርዝር ያካተተ ነበር።

መርሃግብሩ የሰብዓዊ መብት አፈጻጸም ይበልጥ ማረጋገጥ ላይ ያለመ ነው። ዋና ዓላማው በሃገር አቀፍ ደረጃ ተቀናጀ አኳሃን የዜጎች ዴሞክራሲዊና ሰብዓዊ መብቶች የበለጠ ጥበቃ የሚያበጁ ስልቶችና አቅጣጫዎችን መቀየስ ነው።

ባለፈው ዓመት ተጠናቀቀው የአምስት ዓመት መርሃግብር አፈጻጸም ምነብ እንደሚመስል በሁለተኛው የድርጊት መርሃግብር ሰነድ ላይ ተመልክቶአል። ሰነዱ በአሁኑ ሰዓት በሚኒስትሮች ም/ቤት ጸድቆ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ውይይት እየተደረገበት ይገኛል። የአንደኛውን መርሃግብር ውስጥ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ  መብቶች አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የተቀመጠውን በከፊል እንደሚከተለው ቀርቧል

  *         *      *

የድርጊት መርሐ ግብሩ በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ እንደመሆኑ የሚያስገኛቸው በርካታ ጠንካራ ጎኖች እንደተጠበቁ ሆኖ ሰነዱን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የሚያጋጥሙ ችግሮችና ተግዳሮቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል። በዚህ ክፍል የድርጊት መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በመደረጉ የተገኙ ጥቅሞችና የነበሩ ደካማ ጎኖች ጠቅለል ተደርገው ቀርበዋል።

 

በመርሃ ግብሩ አፈጻጸም የታዩ ጠንካራ ጎኖችና የተገኙ ጥቅሞች

የድርጊት መርሐ ግብሩ ተግባራዊ መደረግ በጀመረበት 2006 ዓ.ም እንዲሁም በዝግጅት ሂደት ላይ በ2004 እና 2006 ዓ.ም ሰፊ ሃገራዊ የሰብዓዊ መብት መነቃቃትን ለመፍጠር ችሏል። ለዚህ ማሳያ የሚሳያ ተደርጎ የሚነሳው ድርጊት መርሐ ግብሩ ከዝግጅት ሂደቱ ጀምሮ የፌዴራል እና የክልል መንግስት የስራ ሃላፊዎችን፥ በፌዴራልና ክልል ደረጃ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱ የብዙሃንና የሙያ ማህበራትን፥ በሰብዓዊ መብት ዙሪያ እንዲሰሩ በህግ የተፈቀደላቸው የሲቪክ ማህበራት፥ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች እንዲሁም የውጭ ሃገር መንግስታትን ባሳተፈ መልኩ እንዲዘጋጅ፥ ህገመንግስታዊ ጥበቃ የተደረገላቸውን መብቶች ከማክበር፥ ከመጠበቅና ከማሟላት አንጻር የተገኙ ውጤቶችን እውቅና የሚሰጥ፥ የሚስተዋሉ ችግሮችን ነቅሶ የሚያወጣ እንዲሁም ሊተገበሩ የሚችሉ ችግር ፈቺ የመፍትሔ እርምጃዎችን የሚያስቀምጥ እንዲሆን መደረጉ ነው።  የዝግጅት ሂደቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትንና ሰፊውን ህብረተሰብ ለማሳተፍም ችሏል። ሃገር አቀፍ የሚዲያ ሽፋን ባላቸው የመገናኛ ብዙሃን ለሁለት ተከታታይ ሳምንታት በተደረገ ጥሪ የድርጊት መርሐ ግብሩ ሊያካትታቸው ይገባል የሚባሉ ጉዳዮችን እንዲያነሱ በተደሬገ ጥሪ በርካታ ዜጎችና ማህበራት ግብ ዓቶችን ለማሰባሰብ ተችሏል።

በሁሉም ክልሎች፥ ከተማ መስተዳድሮች አና ፌዴራል ደረጃ በተደረጉ ከሰላሳ ሶስት በላይ የውይይት መድረኮችም የየአካባቢው የሚስተዋሉ የስብዓዊ መብት ችግሮች ጎልተው እንዲወጡና መርሐ ግብሩ የሁሉንም የሃገሪቱ አካባቢዎች ነባራዊ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ እንዲሆን ለማድረግ ተችሏል።   ይህ ሂደት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሰብዓዊ መብት ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሳድጉ እና ለመብቶቹ መከበር ይበልጥ ተነሳሽነት እንዲያድርባቸው ለማድረግ አስችሏል። 

የድርጊት መርሃ ግብሩ ንቅናቄን ከመፍጠር ባለፈም በትግበራው ሂደት በርካታ ለውጦችን ለማስገኘት ችሏል። ሆኖም የድርጊት መርሃ ግብሩ በመተግበሩ የተገኙ ጥቅሞችን ስንመዝን ልብ ልንልው የሚገባው ነጥብ በሰነዱ የተካተቱት የሚከናወኑ ተግባራት ሁለት ዓይነት ባህሪ ያላቸው መሆኑን ነው። የመጀመሪያውና አብዛኞቹን የሚከናወኑ ተግባራት የሚገልጸው ተግባድራቱ ቀድሞውንም ቢሆን በፈጻሚ ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ እየተካተቱ ሲተገበሩ የቆዩ ሲሆኑ ወደ ድርጊት መርሃ ግብሩ የተካተቱት ስራዎቹን ከሰብዓዊ መብት ዕይታ አንጻር እየቃኙ አንዲተገብሩ ለማሰቻል ብቻ ነው። ስለሆነም በነዚህ ተግባራት ክንውን ሂደት የድርጊት መርሃ ግብሩ የነበረውን አስተዋጾ ለመለካት አስቸጋሪ ይሆናል፤ በድርጊት መርሃ ግብሩ ባይካተቱ ኖሮ አይተገበሩም ለማለት የሚያስችል መነሻ ስለማይኖር። 

በሌላ በኩል የድርጊት መርሃ ግብሩን አስተዋጽኦ ግልጽ በሆነ መንገድ ለመመልከት የሚያስችሉት ከዚህ ቀደም በፈጻሚ ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ ያልነበሩ በድርጊት መርሃ ግብሩ እንዲተዋወቁ የተደረጉ አዳዲስ ተግባራት ናቸው። እነዚህ ተግባራት ያላቸውን አፈጻጸም መገምገም መርሃ ግብሩ ያመጣቸውን ተጨማሪ እሴቶች አጉልቶ ለማውጣት ያስችላል። ለማሳያነት ያክል፡- የተከሰሱ ሰዎች በግላቸው ጠበቃ ማቆም የማይችሉ እንደሆነ በቁጥጥር ሥር ከዋሉበት ጊዜ ጀምሮ ነፃ የህግ ምክር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ስትራቴጂ ለመቅረጽ የታቀደ ሲሆን ይህ ተግባር በህይወት የመኖር መብት፥ የተከሰሱ ሰዎች መብት እንዲሁም ፍትህ የማግኘት መብት ውስጥ የተካተተ ሲሆን በባህሪው እጅግ ሰፊ ስራን ከሚጠይቁ የድርጊት መርሃ ግብሩ ተግባራት አንዱ ነው። ይህን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ግን በመርሃ ግብሩ የተመለከተው የብሔራዊ ነጻ የህግ ድጋፍ አግገልግሎት ስትራቴጂ ዝግጅት ሊቀድም እንደሚገባና ስትራቴጂው በሚያስቀምጣቸው ስልቶች መሰረት ተከሳሾአ የህግ ድጋፉን እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ የታመነበት በመሆኑ ይሔው ቅድሚያ እንዲሰጠው ተደርጓል። በአሁኑ ወቅትም ስትራቴጂው ረቂቅ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ የሆነ ሲሆን በ2008 ዓ.ም እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ሌላው የፖሊስ አባላት የኃይል አጠቃቀም ተመጣጣኝነትን የሚመለከቱ የህግ ድንጋጌዎችን በጥናት ላይ ተመሥርቶ የማዳበር እና የማስረፅ፤ እንዲሁም የተዘረጋውን የተጠያቂነት ሥርዓት የማጠናከር ሥራዎች እንዲከናወኑ በመርሃ ግብሩ የተቀመጠ ሲሆን የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት በብሔራዊ ጽ/ቤቱ ስር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ የሰነዱን ረቂቅ ያዘጋጀ ሲሆን የሃይል አጠቃቀምን የሚመለከተው ክፍል ከፌዴራል ፖሊስ፥ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደርና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት መሰረት እንዲዳብር ተደርጓል። በመቀጠልም የሃይል አጠቃቀምና የተጠያቂነት ስር ዓቱን የተመለከቱት ክፍሎች በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት፥ ማርቀቅና ማስረጽ ዳይሬክቶሬት አስተያየት እንዲሰጥበት ተደርጓል። በተሰጡት አስተያየቶች ላይ አስተባባሪ ኮሚቴው አቅጣጫ ከሰጠበት በኋላ ሰነዱ ለተጨማሪ ውይይት የሚቀርብና የሚጸድቅ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህም ድርጊት መርሃ ግብሩ ካስተዋወቃቸው አዳዲስ ተግባራት አንዱን ተፈጻሚ ለማድረግ የተወሰነ ርቀት መኬዱን ያመለክታል። 

በሌላ በኩል የድርጊት መርሐ ግብሩ ተግባራዊ በመደረጉ በሃገር ውስጥ የዜጎችን ህገመንግስታዊ መብቶች ተግባራዊነት ለማሻሻል ካደረገው አስተዋጾ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሃገራችንን ገጽታ ለመገንባት የራሱን በጎ አስተዋጾ አበርክቷል።  ለዚህ ሲባልም የድርጊት መርሐ ግብሩ ረቂቅ የእንግሊዝኛ ትርጉም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል በመላው ዓለም ለሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንጽላዎች እንዲሰራጭ ተደርጓል። ከሁሉም በበለጠ የድርጊት መርሃ ግብሩ መዘጋጀት እ ኤ አ በ2104 ሃገራችን ባቀረበችው የሁሉን አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (Universal Priodic Review) ሪፖርት ወቅት ከፍተኛ እውቅና እንድታገኝ ያስቻላት መሆኑ ይጠቀሳል።

በመርሃ ግብሩ አፈጻጸም የተስተዋሉ ደካማ ጎኖች

·         በፌዴራልና በክልል ደረጃ የድርጊት መርሃ ግብሩን እንዲተገብሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት ተገቢውን ትኩረት ያለመስጠታቸው (ይህም ጥራታቸውን ያልጠበቁ እና በመርሃ ግብሩ መሰረት ያልተቃኙ ዕቅዶችን እና ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ይገለጻል።)

·         የድርጊት መርሃ ግብሩን አፈጻጸም ለመምራት እና ለማስተባበር የተቋቋሙ ሃገራዊና ክልላዊ አደረጃጀቶች ውጤታማ ስራ ለማከናወን ያለመቻላቸው።

·         የመርሐ ግብሩን በሰፊው የማስተዋወቅና የኮሙኒኬሽን ስራ ያለመከናወኑ

·         የሰነዱ የእንግሊዝኛ ትርጉም ተጠናቅቆ ለህትመት ያለመብቃቱ

ቀጣይ የድርጊት መርሃ ግብር ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች

·         በመጀመሪያው ድርጊት መርሐ ግብር የነበሩና ውጤት ያላስገኙ አደረጃጀቶችን በተለይም በክልል ደረጃ ያሉትን በሁለተኛው መርሀ ግብር ተገቢውን ውጤት ለማስገኘት በሚያስችል መልኩ መቀየር፣

·         የድርጊት መርሃ ግብሩ ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ እንዲኖረው ማስቻል፣

·         በመርሃ ግብሩ ትግበራ የብዙሃን እና የሙያ ማህበራት፣ በህግ የተፈቀደላቸው የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ህብረተሰቡ ተገቢውን ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማስቻል፣

·         የሁለተኛው ድርጊት መርሐ ግብር ዝግጅት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ መልኩ እንዲዘጋጅ ማድረግ ናቸው።

የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች

በህይወት የመኖር መብት

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 14 እና 15 ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ፍጡር በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በህይወት የመኖር መብት ያለው መሆኑ የተደነገገ ሲሆን ይህንን ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ብሔራዊ ህጎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛሉ። አገራችን በህይወት የመኖር መብትን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ፈርማ የተቀበለች ሲሆን መብቱን ለማረጋገጥ፤ መብቱን የሚጥሱ የወንጀል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከል፣ ተፈጽመው ሲገኙም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመመርመር፣ ክስ አቅርቦ ለመከራከር እና የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችሉ ተቋማዊ ደረጃጀቶተፈጥረዋ

አስተዳደራዊና ህግ የማውጣት እርምጃዎችን በሚመለከት መንግስት መብቱን ከማስከበር አንጻር የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ከዚህ በታች እደሚከተለዉ ቀርበዋል::

የሞት ቅጣትን አስመልክቶ ቅጣቱ በተወሰኑና እጅግ ከባድ በሆኑ ወንጀሎች ላይ ብቻ እንዲጣል የሚደረግ ሆኖ ቅጣቱ በሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ከጸደቀ ብቻ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን ቅጣቱ የተወሰነበት ሰው ይቅርታ ወይም ምህረት እንዲደረግለት ሊያመለክት የሚችልበት ስርት ተዘርግቷል። ቅጣቱ ዕድሜያቸ 18 ዓመት ባልሞላ ህጻናትና ነፍሰ ጡር ሴቶላይ እንዳይፈጸም በህግ ተደንግጓል። በተጨማሪም የሞት ቅጣት ሲፈጸም ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ መሆን እንደማይገባና የሞት ቅጣት ከመፈጸሙ በፊት በተቀጪው ላይ ማናቸውንም የስቃይ፣ የበቀል እርምጃ ወይም የአካል ጉዳት እንዲደርስበት ማድረግ የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል።

የሞት ቅጣት ሊያስከትል በሚችል ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች በህግ ባለሙያ የሚደገበት አሰራር የተፈጠረ ሲሆን በእነዚህ ወንጀሎች ተከሰዉ በግላቸው ጠበቃ ማቆም ለማይችሉ ተከሳሾች መንግስት በሚመደበው ተከላካይ ጠበቃ አማካኝነት ነጻ የህግ አገልግሎት እንዲያገኙ በመደረግ ላይ ይገኛል።

በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰውን የሽብርተኝት ወንጀል ለመከላከልና አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ የጸረ ሽብር አዋጅ ወጥቶ በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና ዘረፋን ለመከላከል የጦር መሳሪያ አመዘጋገብና አያያዝ  የግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ዉይት እየተደረገበት ይገኛል።

በመጀመሪያው የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር በተመለከተው መሰረት በጥናት ላይ በመመርኮዝ የህግ አስከባሪ ተቋማትን የሃይል አጠቃቀምና የተጠያቂነት ስርዓት የማዳበር ስራ የተጀመረ ሲሆን በዚሁ መሰረት ረቂቅ የሃይል አጠቃቀም ህግ እንዲሁም የተጠያቂነት ስርዓት ህግ ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸው አካላት ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ለበካታ ዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነውንህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀልን በተመለከተ ከዚህ በፊት በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ያለዉን አደረጃጀት አጠናክሮ ዉጤታማነታቸዉን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል እንዲሁም ለአጥፊዎች ከፍ ያለ ቅጣትን የሚደነግግ “ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ስደተኞችን በህገወጥ መንገድ ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ ዋጅ ቁጥር 909/2007 ጸድቆ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል።

የበቀል ግድያንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና አጥፊዎችን በህግ የማስጠየቅ ስራዎች በመሰራታቸው የበቀል ግድያ ወንጀል እንዲቀንስ ተደርጓል። በተጨማሪም በሰው ህይወት ላይ ጉዳት የሚያስከትለውን የጎሳና የብሔር ግጭት ለመከላከል ጤታማ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በርካታ አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል።

የህጻናትን ሞት ለመቀነስ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተቀርጸው ተግባራዊ ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን በ2003 ዓ.ም በተጀመረው የጤና ልማት ሰራዊት በመታገዝ የቅድመ ወሊድ ና ድህረ ወሊድ ክትትል ስራዎች፤ የህጻናት የአመጋገብ ስርዓት ለማሻሻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችና የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት አሰራር በመዘርጋት የጨቅላ ህጻናት ሞት ምጣኔ በ1990 ዓ.ም ከነበረበት በ2007 ዓ.ም 67 በመቶ እንዲቀንስ ተደርጓል።

በመከላከል ላይ ያተኮረ የጤና ፖሊሲ እና የተለያዩ ስትራቴጂዎችን እንዲሁም ፕሮግራሞችን ቀርጾ በመንቀሳቀስ ለሞት የሚያበቁ ዋና ዋና በሽታዎችን ስርጭትለመቀነስ ተችሏል። በኤች አይ ቪ ኤድስ ምክንያት የሚከሰተውን ሞት ለመቀነስ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም የሚተገበር የፀረ ኤች አይ ቪ ኤድስ ዘርፈ  ስትራቴጂ እና ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በበሽታው ምክንያት የመሞት ምጣኔን በ1998 ዓ.ም ከነበረው በ2005 ዓ.ም በ54% መቀነስ ተችሏል፤ ወባ በሽታን በተመለከተ በተሰራዉ ሰፊ ስራ አማካኝነት በሽታዉ በወረርሽኝ መልኩየማይከሰትበት ደረጃ ላይ በማድረስ በበሽታዉ የሚያዙ ስዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ስርጭቱን ለመቀነስ ተችሏል። የጤና አገልግሎትና ጥራት ተደራሽነትን ለማሻሻልመንግስት ባደረጋቸዉ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች  የዜጎችን በህይወት የመኖር ዕድሜ በ2003 ዓ.ም ለሴት 60.4 እና ለወንድ 58.4 ዓመት ከነበረው በ2006 ዓ.ም በሁለቱም ጾታ በአማካኝ 64.1 እንዲሆን ማድረግ ተችሏል።

የምግብ ዋስትናን በአገር አፍ ደረጃ ለማሳካት ተችሏል። በቤተሰብ ደረጃም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የቤተሰብ ጥሪት ለመገንባት፤ በጥናት ላይ የተመሰረተ ምርታማነትን የመጨመርና ገቢ ማስገኘት የሚችል የስራ ዕድል ለመፍጠር የስችሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተው በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም አደጋን ለመከላከል፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ለመውሰድና ተከስቶ ሲገኝም አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል ጠንካራ ስርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የኝ ሲሆን በነዚህ ጥረቶች መነሻነትም በምግብ እጥረት ምክንያት የዜጎች ህይወት እንዳያልፍ ለመከላከል የተቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

በትራፊክ አደጋ በሰው ህይወት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ብሔራዊ የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት የመንገድ ደህንነት የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅቶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ሲሆን በትራፊክ ህጎች ላይ ግንዛቤ የመፍጠር፣ የመንገድ ደህንነት ቁጥጥርና አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራዎች በሰፊው ተሰርተዋል።

 

የአካል ደህንነት መብትና የኢ-ሰብዓዊ አያያዝ ክልከላ

ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ፍጡር በመሆኑ የማይደፈር እና የማይገሰስ የአካል ደህንነት መብት ያለው መሆኑንና ከማንኛውም ጭካኔ ከተሞላበት-ሰብዓዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት፣ በባርነት ወይም በግዴታ አገልጋይነት የመያዝ እና ለማንኛውም ዓላማ በሰው የመነገድ ተግባር ክልከላ እንዲሁም በኃይል ተገዶ ወይም ግዴታን ለማሟላት ሥራ ማሰራት ክልከላዎችን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 16 እና 18 ላይ ተደንግጓል። በተጨማሪም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ብሔራዊ ህጎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን አገራችን መብቱን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን አጽድቃ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ትገኛለች። መብቱን ለማረጋገጥ፤ መብቱን የሚጥሱ የወንጀል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከልና ተፈጽመው ሲገኙም ውጤታማ በሆነ መልኩ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ተቋማዊ አደረጃጀቶች ተፈጥረዋል።

አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በሚመለከት መንግስት መብቱን ከማስከበር አንጻር የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ከዚህ በታች እንደሚመለከተዉ ቀርበዋል::

የህግ አስከባሪ አካላትና የአገር መከላከያ አባላት የሰብዓዊ መብቶች አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የተለያዩ ህጎችና መመሪያዎች ወጥተው ሲተገበሩ ቆይቷል። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 በማውም የሠራዊቱ አባል የሚፈጸም የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድርጊት እንደከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት እንደሚቆጠር የተመለከተ ሲሆን ይህንን በዝርዝር ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ እና የተቋሙ መመሪያዎች ጸድቀው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛሉ። ተመሳሳይ የህግ ማዕቀፎች በሁሉም የክልል እና ከተማ መስተዳድር ፖሊስ ኮሚሽኖች ተፈጥረዋል። እነዚህ ህጎችና ደንቦች በህግ አስከባሪ አካላት ማሰልጠኛ ተቋማት ስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተቱ የተደረገ ሲሆን ለሁሉም የፖሊስ አባላት በህጎቹበአካል ደህንነት መብትና የኢ-ሰብዓዊ አያያዝ ክልከላን ጨምሮ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ተከታታይ ስልጠናዎች በመጠት ላይ ይገኛሉ።

የፖሊስና የማረሚያ ቤት ተቋማት እንዲሁም ሌሎች የህግ አስከባሪ አካላት ስራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የዜጎችን የአካል ደህንነትና ከኢ-ሰብዓዊ አያያዝ የመጠበቅ መብት ባከበረ መልክ እንዲንቃሳቀሱ ለማስቻል የህግና የአሰራር ስርዓት ዝርጋታ እንዲሁም የስልጠና ስራዎች  በሰፊው ተከናውነዋል።

የአካል ደህንነት እና ኢሰብዓዊ አያያዝ ክልከላን እንዲሁም ሌሎች ሰብዓዊ መብቶችን በይበልጥ ተፈጻሚ ለማድረግ የሚያስችል የህግ አስከባሪ አካላት የሃይል አጠቃቀም እና የተጠያቂነት ስርዓት የህግ ማዕቀፍ በብሔራዊ ሰብዓዊ መብት ድርጊት መርሐ ግብር ጽ/ቤት አስተባባሪነት በመዘጋጀት ላይ ይገኛል።

በፖሊስ ጣቢያዎችና በምርመራ ተቋማት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት የቅሬታ ማቅረቢያ ቢሮ የተደራጁ ሲሆን በርቡ ቅሬታዎች መነሻነት የወንጀልና የዲሲፕሊን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል፡

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የብሔራዊ ምክር ቤት በማቋቋም በጉዳዩ ላይ መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ሲሆን ለመንግስት ፈጻሚ አካላትና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችና አዘዋዋሪዎች በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራዎች ተሰርተዋል። ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከመዳረሻ ሀገራት ጋር ስምምነቶችን ለማድረግ ጥረት ተደርጓል። በተጨማሪም ወንጀሉን በተሻለ ሁኔታ ለመከላከል፣ አጥፊዎችን ለመቅጣት እና ተጎጂዎችን ለመርዳት የሚያስችል አዲስ ዋጅ ጸድቆ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል።

በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የተለያዩ አደረጃጀቶችና አሰራሮች ተፈጥረው በርካታ ስራዎች ሲከናወኑ የቆየ ሲሆን ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶችና ህጻናት ለመርዳት እና የህክምናና የህግ አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት የቅንጅታዊ አሰራር የቅብብሎሽ ስርዓት ለመፍጠር ጥረት ተደርጓል፤ ለበርካታ ተጎችም የህግና የስነ ልቦና ድጋፍ ተሰጥቷል። በባህር ዳር፣ በሃዋሳና በአዳማ የህጻናት የህግ ከለላ ማዕከል ለማቋቋም ዝግጅት በመደረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመመርመርና ውሳኔ ለማሰጠት በፖሊስ ጣቢያዎች ልዩ ስልጠና የወሰዱ መርማሪዎችና ዐቃቤ ህጎች ተመድበው እንዲሰሩ በመደረጉ አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ከማድረግና ተጎጂዎችን ከመርዳት አንጻር አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና አጥፊዎችን በህግ የማስጠየቅ ስራዎች ተሰርተዋል። በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች፣ በህጻናት ማሳደጊያ ተቋማትና በወላጆች የሚወሰድ የአካላዊ ቅጣት እንዲቀርአማራጭ የቅጣት ዘዴዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ ለማድረግ ሰፊ ጥረት የተደረገ ሲሆን አበረታች ውጤቶችም ተገኝተዋል።

የተያዙ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብት

ሕገ መንግስቱ የተያዙ፣ በጥበቃ ሥር ያሉ እና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች የተለያዩ መብቶች እንዳሏቸው የሚደነግግ ሲሆን መብቶቹን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ብሔራዊ ህጎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪም አገራችን መብቱን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ፈርማ ያጸደቀሲሆን መብቱን ለማረጋገጥ፤ መብቱን የሚጥሱ የወንጀል ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ ለመከላከልና ተፈጽመው ሲገኙም ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ተቋማት ተደራጅተዉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በሚመለከት መንግስት መብቱን ከማስከበር አንጻር  የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ከዚህ በታች የተመለከቱት ናቸው።

የህግ አስከባሪ አካላት የተያዙና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች እና በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን መብቶች እንዲያከብሩ ለማድረግና ጥሰት ሲከሰት ተጠያቂ ለማድረግ ህጎች ወጥተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ለህግ አስከባሪ አካላት በነዚህ መብቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን የመስጠትና መብቶቹን ጥሰው የተገኙትን በህግ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተከናዉኗዋል። ተጠርጣሪዎች ያሏቸውን መብቶች የሚያሳይ የመብቶቹ ዝርዝር በተለያዩ ቋንቋዎች ተጽፈው በፖሊስ ጣቢያዎች እንዲለጠፉ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። የተጠርጣሪዎን መብት በላቀ ደረጃ ለማስጠበቅ የሚያስችል በፌዴራልና አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙ ተጠርጣሪዎች አያያዝ መመሪያ ተዘጋጅቷል።

የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በሚያስቀምጠው መሰረት የቅድመ ፍርድ እስርን ለማሳጠር የማስረጃ መር የወንጀል ምርመራ ዘዴን መሰረት ባደረገ መልኩ መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) እና የተፋጠነ የፍትህ አሰጣት ሂደት (RTD) ተግባራዊ መደረግ በመቻሉ የተጠርጣሪዎች የቅድመ ፍርድ እስርን ከማሳጠርና በተፋጠነ ሁኔታ ፍትህ ከመስጠት አንር አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል።

በፖሊስ ጣቢያዎችና በማረሚያ ቤቶች የሚገኙትን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን በቋሚነት በዐቃቤ ህግበፖሊስ እና በማረሚያ ቤትኃላፊዎች ጉብኝት የሚደረግበትና የሚታዩ ችግሮች የሚፈቱበት አሰራር ተፈጥሮ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።

በፖሊስ ጣቢያዎችና በማረሚያ ቤቶች ያለውን ምግብ፣ውሃና የንጽህና መጠበቂያ አገልግሎት አቅርቦት ለማሻሻል ጥረት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎች የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በበካታ ማረሚያ ቤቶች የህክምና መስጫ ተቋማት እንዲደራጁ እና ክሊኒኮች ባልተደራጁባቸው ማረሚያ ቤቶችም በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የህክምና መስጫተቋማት ጋር ትስስሮችን በመፍጠር አገልግሎቱ ተደራሽ እንዲሆን በመሰራት ላይ ይገኛል።

በወል ድርጊት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉ እንዲሁም በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ለቤተሰቦቻቸው፣ ለህግ እና ለሐይማኖት አማካሪዎቻቸው ወይም ለሌላ ከመረጡት ሰው ጋር እንዲገናኙ በመደረግ ላይ ይገኛል።

በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን በወንጀል አይነት፣ በዕድሜ ለያይተው የማቆየትና ዕድሜያቸው 18 ዓመት ያልሞላቸው ተጠርጣሪዎች ከሌሎች ተለይተው እንዲያዙ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ የሚገሲሆን በዚህ ረገድ በርካታ ማረሚያ ቤቶች ወጣት ጥፋተኞችን ሙሉ በሙሉ ለያይተው የሚያቆዩ ሲሆን መንግስት በሚመድበው በየጊዜው እያደገ  በሚሄድ በጀትምበሁሉም ማረሚያ ቤቶች አዋቂና ወጣት ጥፋተኞችን ለያይተው ለማቆየት ዕቅድ ይዘው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ህጻናት ከእናቶቻቸው ጋር ወደ ማረሚያ ቤቶች እንዳይገቡ ለማድረግ አማራጭ እርምጃዎችን ለመውሰድና ከእናቶቻቸው ወደ ማረሚያ ቤቶች የገቡ ህጻናት እንክብካቤ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል።

በርካታ ታራሚዎች በአመክሮ እንዲፈቱ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የይቅርታ ስርዓቱን ተደራሽና ውጤታማ ለማድረግ አዲስ የይቅርታ አዋጅ ጸድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል። በዚህ መሰረት ከ2003 እስከ 2005 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 57036 ያህል ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ ተደርጓል። ታራሚዎች የእስር ጊዚያቸውን ጨርሰው ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ አምራችና ህግ አክባሪ ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል በተለያዩ ሙያዎች ላይ እንዲሳተፉና የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን በዚህም ከማረሚያ ቤቶች ከወጡ በኋላ በአነስተኛና ጥቃቅን ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ህይወታቸውን ለመምራት የሚያስችል አቅም እንዲያገኙ ተደርጓል።

የተያዙ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች መብትን ለቀጣይ አምስት አመታት ይበልጥ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ከዚህ በታች የተመለከቱት ተግባራት ይከናወናሉ።

የተከሰሱ ሰዎች መብት

የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በኋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት የመቅረብ እና ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመዳኘት  መብት በፍርድ ሂደት በተከሰሱበት ወንጀል እንደ ጥፋተኛ ያለመቆጠር እንዲሁም በምስክርነት እንዲቀርቡ ያለመገደድ የቀረበባቸውን ማስረጃ የመመልከት የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ (የማስቀረብ) እና ምስክሮች እንዲሰሙላቸው የመጠየቅ መብት፤ በመረጡት የህግ ጠበቃ መወከል አቅም የሌላቸው እንደሆነ እና ይህም ፍትህን የሚያጓድል ሲሆን ከመንግስት ጠበቃ የማግኘት ጉዳዩን በሚመለከተው ፍርድ ቤት ትዕዛዞች እና ፍርድ ላይ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ ክርክሩ በማይረዱት ቋንቋ በሚካሄድበት ጊዜ በመንግስት ወጪ እንዲተረጎምላቸው የመጠየቅ መብት እንዳላቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 20 ሥር ተደንግጎ ይገኛል።

በተጨማሪም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ብሔራዊ ህጎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን አገራችን መብቱን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተቀብላ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ትገኛለች። መብቱን ለማረጋገጥ፤ መብቱ እንዳይጣስ ለመከላከልና ጥሰት ሲፈጸምም ውጤታማ በሆነ መልኩ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ተቋማዊ አደረጃጀቶች ተፈጥረዋል።

አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በሚመለከት መንግስት መብቱን ከማስከበር አንጻር  የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ ከዚህ በታች የተመለከቱት ናቸው::

የወንጀል ፍትህ ፖሊሲ በሚያስቀምጠው መሰረት የቅድመ ፍርድ እስርን ለማሳጠር የማስረጃ መር የወንጀል ምርመራ ዘዴን፣ መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ (BPR) እና የተፋጠነ የፍትህ አሰጣት ሂደት (RTD) ተግባራዊ ማድረግ በመቻሉ የተጠርጣሪዎችን የቅድመ ፍርድ እስር ጊዜ ለማሳጠርና ለተከሰሱ ሰዎች የተፋጠነ ፍትህ ለመስጠት ተችሏል።

የዳኝነት ስርዓቱን ተገማችነትና ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ በ2002 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ሲተገበር የቆየ ሲሆን በአተገባበሩ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲባል መመሪያው በ2006 ዓ.ም ተሻሽሎ ተግባራዊ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪም በመመሪያው ሌሎች የወንጀል ድንጋጌዎችን ለማካተት እንዲቻል ቀጣይነት ያላቸው ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ።

የፍትህ ስርዓቱን ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ የተለያዩ የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ፕሮግራሞች ሲተገበሩ የቆዩ ሲሆን የባለሙያዎችን ውጤታማነትና ክህሎት ለማሳደግ ለበርካታ ዳኞች፣ ዐቃቤ ህጎችና የፖሊስ አባላት ተከታታይ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።

ለተከሰሱ ሰዎች የዋስትና መብት ለማስጠበቅ በዝርዝር ህጎች በሰፈረዉ መሰረት የህጉን አላማ በሚያሳካ አግባብ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

በፍርድ ቤቶች የሚደረገውን የችሎት ክርክር ተከሳሾቹ በሚረዱት ቋንቋ እንዲሆን ለማድረግ በቂ የቋንቋ አስተርጓሚዎች ለመመደብ ጥረት የተደረገ ሲሆን ቁጥ በየጊዜው እያደገ በመሔድ ላይ ይገኛል።

የፍትህ ስርዓቱን ለህጻናት ምቹ ለማድርግ የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን በወንጀል ተግባር ውስጥ ገብተው ሚገኙ ህጻናትን ለማረም የሚረዱ አማራጭ የእርምት እርምጃ ማዕከላት በአንዳንድ አካባቢዎች እንዲገነቡ ተደርጓል። በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ለህጻናት የሚመቹ ችሎቶች እንዲቋቋሙ የተደረገ ሲሆን ህጻናት ወንጀል ፈጽመው ወይም ተፈጽሞባቸው ሲገኙ ነጻ የህግ፣ የጤናና የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማድረግ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል።

በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱና በግላቸው ጠበቃ ማቆም የማይችሉ ሰዎች በመንግስት የሚመደብ ነጻ የህግ አገልግሎት በተከላካይ ጠበቆች አማካኝነት እንዲያገኙ  የተደረገ ሲሆን በቂ ተከላካይ ጠበቆች እንዲኖሩ ለማድረግና ክህሎታቸውን ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል። በተጨማሪም የግል ጠበቆች እንዲሰጡ የሚጠበቅባቸውን ነጻ የጥብቅና አገልግሎት አቅም ለሌላቸው በርካታ አገልግሎቱን የሚፈልጉ የተከሰሱ ሠዎች እንዲሰጥ ተደርጓል።

 

ፍትህ የማግኘት መብት

ማንኛውንም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ወይም በህግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው ሌላ አካል የማቅረብ እና ፍርድ የማግኘት መብት እንዳለውሁሉም ሰዎች በህግ ፊት እኩል ስለመሆናቸው እና በመካከላቸውም ማንኛውም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ በህግ እኩል ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆኑ በሕገ መንግስአንቀፅ 37 እና 25 ሥር ተደንግጎ ይገኛል። መብቱን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ብሔራዊ ህጎች ተዘጋጅተው እየተፈጸሙ የሚገኙ ሲሆን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተፈርመው ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛሉ። መብቱን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ተቋማዊ አደረጃጀቶች ተፈጥረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በሚመለከት መንግስት መብቱን ከማስከበር አንጻር  የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለዉ ቀርበዋል::

ፍርድ ቤቶችን ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በአብዛኛው ፍርድ ቤቶች ተጨማሪ ምድብ ችሎቶችን የማደራጀት፣ የተዘዋዋሪ ችሎት አገልግሎት የመስጠትና የቪዲዮ ኮንፈራንስ ችሎት (e-litigation) አገልግሎት እንዲጀመር ከማድረግ ባሻገር ፖሊሳዊ አገልግሎቶችን በይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎትን የማስፋፋት ስራ በማከናወን አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።

ለበርካታ የፍትህ አካላት ፈጻሚዎች በትምህርትና ስልጠና አቅምን የማሳደግ ስራ የተሰራ ሲሆን የፍትህ አሰጣጥ ውጤታማነትና ቅልጥፍናን ማሻሻል በመቻሉ ለጉዳዮች አፋጣኝ ዉሳኔዎች መስጠት ተችሏል። በፍትህ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎች፣ የሚከናወኑ የለውጥ ተግባራት እንዲሁም አስተማሪ ውሳኔዎች በሚዲያ ለህብረተሰቡ እንዲደርሱ ሲደረግ ቆይቷል።

የህብረተሰቡን የህግ ግንዛቤን ለማሳደግ በተለያዩ ሚዲያዎች፣ በስልጠናዎች፣ ጽሑፎችን በማሰራጨት ትምህርት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ግንዛቤ እንዲፈጠር ከተደረጉ እንቅስቃሴዎች መካከል የህጻናትና ሴቶች መብቶች፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የአካል ጉዳተኞች መብቶች፣ የውልና የቤተሰብ ህጎች፣ ሙስና መከላከል፣ በሀይማኖት አክራሪነትና በሰላም አብረው መኖር ይገኙበታል።

በፍትህ ተቋማት የሚሰጡ አገልገሎቶችን እና የሚከናወኑ ተግባራትን በሚዲያ በሰፊዉ የማስተዋወቅ እንዲሁም የህረተሰቡ የህግ ግንዛቤ የሚያሳድጉ የተለያዩ ስራዎች በሰፊዉ ተሰርተዋል።

ፈርመን ከተቀበልናቸው የተለያዩ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ስምምነቶች በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ተተርጉመው እንዲሰራጩ ተደል። በተጨማሪም የሰብዓዊ መብት አጠቃላይ ወቅታዊ ግምገማ (ዩፒአር) ምክረ ሀሳቦች እንዲተረጎሙና እንዲሰራጩ ተደርጓል።

የህጎችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ የተለያዩ አዋጆች፣ ደንቦችና የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔዎች ለተለያዩ ተቋማት፣ ለፍትህ አካላትና ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ ተደርጓል።በተጨማሪም ከ1987ዓ.ም ጀምሮ ያሉትን የፌዴራል ህጎችን የማሰባሰብ እና የማደራጀት ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የሰብዓዊ መብት ተቋማትን ተደራሽ ለማድረግ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቅርንጫፎችን የማስፋፋትና በየትምህርት ቤቶች የሰብዓዊ መብት ክበባትን የማቋቋም ስራ ተከናውኗል።

 

የአመለካከት እና ሀሳብን በነፃ የመያዝና የመግለጽ መብት

ሕገ መንግስቱ በአንቀፅ 29 ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት የመያዝ መብት እንዳለው፤ እንዲሁም ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለፅ ነፃነት እንዳለይደነግጋል። ይህም ነፃነት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሐፍ ወይም በህትመት፣ በሥነ-ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነፃነቶችን ያካትታል። በተጨማሪም ሕገ መንግስቱ የኘሬስና የሌሎች መገናኛ ብዘሃንን በተመለከተ ቅድሚያ ምርመራን የሚከለክል ከመሆኑም ባሻገር፤ የህዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን በተመለከተ ጥበቃ ያደርጋል። እንዲሁም የሥነ-ጥበብ ፈጠራ ነፃነት በሕገ መንግስቱ ተረጋግጧል። ተያይዞም ሕገ መንግስቱ ማንኛውም ዜጋ እነዚህን መብቶቹን የጦርነት እንቅስቃሴዎችን ለማድረግና የሰብዓዊ ክብርን የሚነኩ የአደባባይ መግለጫዎች በመስጠት መጠቀም እንደማይችል ገደብ አስቀምጧል። በተጨማሪም አገራችን መብቱን ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ አለም አቀፍ ስምምነቶች ፈርማ የተቀበለች ሲሆን መብቱን ከማስጠበቅ አኳያ ተቋማት በማደራጀት የተለያዩ ስራዎች ተከናዉኗል።

መንግስት ዜጎችን መረጃ ማግኘት የሚችሉባቸዉ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ቴሌቪዥን ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የኬብልና የሳተላይት ቴሌቪዥን ጥናቶች ተደርገው ወደ ተግባር ተሸጋግረዋል። እንዲሁም የሚዲያ አዋጅና የዲጂታል ኔትወርክ አስተዳዳር ደንብ ተዘጋጅቶ በስራ ላይ እንዲዉል ተደርጓል። በተጨማሪም ዜጎች የመገናኛ ብዙኃን አሰራርና አፈጻጸም በቂ መረጃና ግንዛቤ  እንዲኖራቸዉ ለማድረግ ጋይድላይኖችና የአሰራር መመሪያዎች በማዘጋጀት እንዲሰራጭ ተደርጓል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የመገናኛ ብዙኃን አሠራር ለዜጎች ግልጽና ተጠያቂነት ያለዉ መሆኑን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ  ስንታንዳርዶችማንዋሎችና ጋይድላይኖች ተዘጋጅተዋል።

የመገናኛ ብዙኃንን ተደራሽነት በማስፋፋት ረገድ ህብረተሰቡ በራሱ ቋንቋ ባህልና ወግ መረጃ እንዲደርሰዉና ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዎችን አዲስ ፈቃድ በመስጠት የማሳደግ ሥራ ተሰራቷል። ይህም ህብረተሰቡ የልማት ተግባራት ላይ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ከፍተኛ እገዛ አድርጓል።  የንግድ እና የማህበረሰብ ሬዲዩ ብሮድካስት አገልግሎት ከማስፋፋት አንጻር አገልግሎቱን ለሚሠጡ ጠያቂዎች ብቃታቸዉን በማረጋገጥ ፈቃድ በመስጠት የመገናኛ ብዝሃንን ተደራሽነት እንዲጨምርና የዜጎች መረጃ የማግኘት አድማስ እንዲሰፋ አድርጎታል።  በተጨማሪም በህትመት ሚዲያው ዘርፍ ዜጎች ወቅታዊ መረጃዎችን በስፋት እንዲያገኙ ለማስቻል የህትመት ሚዲያ ተቋማት ምዝገባ እና ድጋፍ ስራ በሰፊው ተከናውኗል።

መንግስት ማንኛዉም ሰዉ ያለ ምንም ጣልቃገብነት ሀሳቡን የመግለጽ መብቱን ለማስከበር የተለያዩ ሥራዎች የተሰሩ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ በ2007 ዓ.ም በተካሄደዉ ሀገራዊ አምስተኛ ዙር ምርጫ ተወዳዳሪ የፓለቲካ ፓርቲዎችና እጩዎች በምርጫዉ ወቅት ዓላማቸዉንና ፕሮግራማቸዉን ለህዝብ በ17 የፌዴራልና የክልል የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እና በስራቸዉ የሚገኙ የተለያዩ ሚዲዎች በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ አድርገዋል። በተጨማሪም በምርጫ ወቅት የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ እንዲሁም ነጻ የምርጫ ዘመቻዎችን በማድረግ በአደባባይ ሀሳባቸዉን መግለጽ እንዲችሉ ተደርጓል።

የመገናኛ ብዙኀን ለዜጎች የሚሰጡት መረጃዎች አግባብነት እንዲሁም ለአገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋፆ የሚያበረክት እንዲሆን ባለሙያዎችና የሚመለከታቸዉ አካላትን ብቃት ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ በመገናኛ ብዙኃን ህጎች እና አሰራሮች ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተችሏል።

የሴቶች፣ ህጻናት፣ ወጣቶች እና የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በሚዲያ ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች፣ ከግልና ከመንግስት ለተዉጣጡ የኤሌክትሮኒክስና ህትመት ባለሙያዎች ሙያዊ ስልጠናዎች ተሰጥቷል።

የመደራጀት መብት

ሕገ መንግስቱ በአንቀፅ 31 ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብቱ የተረጋገጠና ዋስትና ያገኘ ሲሆን አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በህገ ወጥ መንገድ ለማፍረስ መደራጀት የተከለለ መሆኑን በመግለፅ የመብቱ ገደብ ተደንግጓል። በዚሁ መሰረት መብቱን ይበልጥ ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ከመብቱ ጋር የተገናኙ ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፍ፤ የፓሊሲ እርምጃ እና ብሔራዊ ህጎችን በማካተት ወደ ስራ ተገብቷል።

ከመደራጀት መብት ጋር በተያያዙ ህጎችና የአሰራር ስርዓቶች ላይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ በማድረግ ተልዕኳቸዉን በአግባቡ ለመወጣት እንዲችሉ በአዋጆች፣ በደንቦችና መመሪያዎች ዙሪያ ተከታታይ ሰልጠናዎችን ተሰጥተዋል። እንዲሁም የአደረጃጀት ግልጽነት በጎደለባቸው የብዙኀን ማህበራት በተለይ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የገቢ መብት ዙሪያ ላይ በነበሩ የግንዛቤ እጥረቶች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት ተግባራቸዉን በአግባቡ እንዲወጡ ተደርጓል።

የዜጎች መደራጀት መብትን ለማስፈጸም ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር ባሻገር መብቱን በአግባቡ ለመተግበር የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማኅበራት የጋራ ህብረት የምክክር መድረክ እንዲመሰርቱ በማድረግ አደረጃጀቱ ውጤታማ እንዲሆን በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲው በኩል ተገቢ የሆነ ስልጠናና ድጋፍ ተሰጥቷል። በዚህም በየደረጃው ለዜጎች መደራጀት እንቅፋት የሆኑ ህጋዊና ልማዳዊ አስተሳሰቦች ላይ በመመካከር መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ ማህበራቱ በመንግስታዊ የሴክተር ተቋማት ምክክር መድረኮች ላይ እንዲሳተፉና በኤጀንሲው የቦርድ አመራር ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ በመደረጉ የውሳኔ ሰጪነት ሚናቸዉ እንዲጎለብት ተደርጓል

ከዚህ ባሻገር የዜጎችን የመደራጀት መብት ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ተፈጻሚ ለማድረግ አገር በቀል የሆየበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትንእንቅስቃሴ ለመደገፍ እንዲቻል በገቢ ማስገኛና በህዝባዊ መዋጮ ስራዎች ድጋፍ ለማሰባሰብ እንዲችሉ ምቹና ግልጽ የሆነ አሰራር ተዘርግቷል። በተጨማሪም በፌዴራል ደረጃ የተመዘገቡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትበክልል መንግስታት የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲመቻች ተደርጓል።

የፓለቲካ ፓርቲዎች ለዲሞክራሲያዊ ግንባታ የሚያደርጉት ተሳትፎ ወሳኝ ነዉ። በዚህም መሰረት በ2007 ዓ.ም በሀገሪቱ በተካሄደዉ ጠቅላላ ምርጫ 58 ተወዳዳሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1,819፣ ለክልል 3,988 ዕጩዎች አቅርበዋል። ይህም በ2007 በተካሄደዉ ምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሴቶች በመራጭነት፣ በዕጩ ተወዳዳሪነት፣ በምርጫ አስፈጻሚነት፣ በምርጫ ታዛቢነት ያለምንም ልዩነት በአግባቡ ማሳተፍ እን ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ በመያዙም በ229,060 የምርጫ ጣቢያዎበአስፈጻሚነከተመለመሉት ዉስጥ 40% ሴቶች እንዲኑ ተደርጓል። ከ1987 ዓ.ም እስከ 2007 ዓ.ም በተካሄዱትአምስት ተከታታይ ጠቅላላ ምርጫዎሴቶች በመራጭነት የነበራቸዉ ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ታይቷል። በዚህም መሰረት በ1987 ዓ.ም ከነበረዉ 9,601,820 በ2007 ዓ.ም ወደ 16,554,131 ደርሷል። በሌላ መልኩ ሴቶች በተወዳዳሪነት ያላቸዉ ተሳትፎ በ1987 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቁጥር 13 ከነበረዉ  በ2007 ዓ.ም ወደ 212 የደረሰ ሲሆን፣ በክልል ምክር ቤት 1987 ከነበረዉ 77 በ2007 ዓ.ም ወደ 803 ከፍ ብሏል። ይህም አሃዝ የሴቶች የፖለ ተሳትፎ በእጅጉእያደገ መምጣቱን ያሳያል።

የብዙኀን ማህበራት እንዲስፋፉና እንዲጠናከሩ ድጋፍ ከማድረግ አንጻር 3.94 ሚሊዮን ሴቶች በተለያዩ ነባር ማኅበራት ዉስጥ በአባልነት ከመደራጀታቸዉ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት 6.3 ሚሊዮን ሴቶች እንዲደራጁ ድጋፍ ተደርጓል። በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን 11.9 ሚሊዮን ሴቶችን በአባልነት ያቀፉ 477,369 የሴቶች ልማት ቡድኖች እና 2.2 ሚሊዮን (1ለ5) የሴቶች ኔትዎርኮችን ተደራጅተው ወደ ተግባር ገብተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ዜጎች የመደራጀት መብታቸዉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግን በተመለከተ ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አኳያ 4.89 ሚሊዮን ወጣቶች በጥቃቅንና አነስተኛ የገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞች ተደራጅተዉ በተለያዩ የሥራ መስኮች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። በግብርና የስራ መስኮች 2.21 ሚሊዮን እንዲሁም ከግብርና ዉጭ በሆኑ የገቢ ማስገኛ ስራዎች 2.43 ሚሊዮን ወጣቶች በመደራጀት ተጠቃሚ ሆነዋል። ለ358,175 የደረጃጀአመራሮች በተለያዩ ርዕሶች ላይ ስልጠና በመስጠት አቅማቸዉን ማጎልበት ተችሏል። 3.97 ሚሊዮን ወጣቶች በተለያዩ ነባር ማህበራት ዉስጥ አባል የሆኑ ሲሆን በአሁኑ ወቅት 8.7 ሚሊዮን ወጣቶች እንዲደራጁ ድጋፍ ተደርጓል።

በአገራችን የዜጎች የመደራጀት መብት ተግባራዊ ለመሆኑ እንደ ማሳያ ከሚጠቀሱት አንዱ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው። በሌላ በኩል በመጀመሪያዉ የእድገትና በትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ  የስራ እድል ፈጠራ በተመለከተ 3.2 ሚሊዮን የስራ እድል ለመፍጠር በማቀድ 8.33 ሚሊዮን (278%) ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ተፈጥሯል። በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በተመለከተ በ2002 በጀት ዓመት የነበሩት 131,75 የስራ እድል ፈጠራ መስኮች ወደ 26,350  እንዲያድጉ ሰፊ ርብርብ ተደርጓል። ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት አንቀሳቃሾች የተደረገ ድጋፍን በተመለከተም 15745 ሄክታር ቦታ፤ 567 ህንጻዎች እና 16,753 ሼዶች ተዘጋጅተዉ አገልግሎት ላይ እንዲዉሉ ተደርጓል። የገበያ ትስስርን በተመለከተ ለ2.9 ሚሊዮን የሚሆኑ አንቀሳቃሾች የብር 25.6 ቢሊዮን በአገር የዉስጥ የገበያ ትስስር የተፈጠረላቸዉ ሲሆን፤ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተፕራይዞች ምርቶቻቸዉን ኤክስፐርት አድርገዉ 65 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ የዉጭ ምንዛሪ ማግኘት ችለዋል።

የሃይማኖትና እምነት ነጻነት መብት

ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ላይ ማንኛውም ሰው የማሰብ፣ የህሊናና የሃይማኖት ነፃነት እንዲኖረው በግልፅ ያስቀምጣል። ይህም መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለፅ መብትን ያካትታል። ከዚህ በተጨማሪም የሃይማኖት ተከታዮች ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችቸው የሃይማኖት ትምህርትና የአስተዳደር ተቋማት ማቋቋም እንደሚችሉና ወላጆችና ህጋዊ ሞግዚቶች በእምነታቸው መሠረት የሃይማኖታዊና የመልካም ሥነ-ምግባር ትምህርት በመስጠት ልጆቻቸውን የማሳደግ መብት እንዳላቸው ተቀምጧል። በሕገመንግስቱ አንቀጽ 11 ላይም መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን፤ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንዳይገባ ከመከልከሉም ባሻገር መንግስታዊ ሃይማኖት እንደማይኖር ይደነግጋል። በተጨማሪም አገራችን መብቱን በይበልጥ ለማስከበር የሚያስችሉ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ፈርማ የተቀበለች ሲሆን መብቱን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችሉ ተቋማትን በማቋቋም የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስደዋል።

በህግ መንግስቱ ላይ በተደነገገዉ መሰረት ያለመንግስት ጣልቃ ገብነት የሃይማኖትና እምነት ተቋማት ተግባራቸዉን ማከናወን እንዲችሉ በፌዴራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ድጋፍ ለመስጠት 10 አስተባባሪ ኮሚቴዎችና 16 የክትትልና ድጋፍ ቡድን ተቋቁመው በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን በ”ማዳመጥ እና የመተማመን ፕሮግራም “አማካኝነት ሰፊ ቁጥር ያለው የህብረተሰብ ክፍል በሃይማኖትና እምነት ነጻነት መብት ላይ የጠራ አመለካከት እንዲኖራቸው ለማድረግ ተችሏል።

በክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በሚገኙ የሃይማኖትና እምነት ተቋማት እና ተከታዮቻቸው መካከል የሰላምና የመከባበር ባህል ለመገንባት እንዲሁም ለተለያዩ የመንግስት አካላት እና ለ9,845,178 ለሚደርሱ ዜጎች እምነትና ሃይማኖትን በሚመለከቱ ህገመንግታዊ ድንጋጌዎችና በፀረ አክራሪነት ዙሪያ የግንዛቤ ማጎልስልጠናዎተሰጥተዋል። እንዲሁም ከ31 ዩኒቨርስቲዎች ለተውጣጡ 372,418 ተማሪዎችና ማህበረሰብ አባላት ዲሞክራሲና የሃይማኖት አክራሪነት፤ ሃይማኖታዊ የአመጋገብ፣ የአለባበስና የአምልኮ ሥርዓትን ለመደንገግ በተዘጋጀው መመሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

በመንግስት ተቋማት የሚገኙ ሰራተኞች ለዜጎች ያለምንም አድልዎና ወገንተኝት የሴኩላሪዝም መርህን በመከተል ለሚቀርቡ የአገልግሎት ጥያቄዎች ምላለመስጠት እንዲችሉ ተከታታስልጠናዎና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋ

የሃይማኖትና እምነት ተቋማት ህጋዊ በሆነ መንገድ ሃይማኖትና እምነታቸዉን ማካሄድ እንዲችሉ የሚመመዘገቡበት፣ ፈቃድ የሚያገኙበት፣ ፈቃዳቸውን የሚያድሱበት እና ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በዚሁም መሰረት ከ2004 - 2007 ዓ.ም ለ470 የሃይማኖት ተቋማት ህገ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት፤ ለ1570 የሃይማኖት ተቋማት የፈቃድ እድሳት እንዲሁም የ1229 ሃይማኖት ተቋማት መረጃ የማደራጀት ስራ ተከናውኗል

ለሀይማኖት ተቋማትና ተከታዮቻቸው የሃይማኖትና እምነት ነፃነት መብትን በተመለከተ ሰፊ ስራ ከመሰራቱ ባሻገር አለመግባባቶችና ቅሬታዎች ሲከሰቱ ከሚመለከታቸውአካላት ጋር በመተባበር ጉዳዩ በተለመደው የመቻቻልና የመከባበር አግባብ መፍትሄ እንዲያኙ ተደርጓል። 

የሃይማኖትና እምነት ነጻነትና እኩልነት መብትን በተገቢዉ ለመተግበር እንዲቻል ተቋማቱ በተለያዩ ጊዜያት ለቀረቡ ሃይማኖት ነክ የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች የቤተእምነት ግንባታ ፈቃድ ጥያቄዎች፣ የአምልኮና የቀብር ቦታ ጥያቄዎችን በማስመልክት ከቀረቡ 1244 ጥያቄዎች ውስጥ ባለው የህግ እና አሰራር አግባብ 829 ለሚሆኑት መፍትሄ እንዲያገኙ ተደርጓል።

 የሃይማኖትና እምነት ነጻነት መብትን በተመለከተ ዜጎች ያላቸውን አረዳድና ግንዛቤ በሚያዛባ መልኩ የሚወጡ የመጽሄትና ጋዜጣ ህትመቶችየኤሌክትሮኒክስ ዘገባዎች እና ማህበራዊ ድረ-ገጾች መረጃዎችን በመለየት እና  በመተንተን እንዲሁም የቆየውን የመቻቻልና የመከባበር ባህል መሰረት በማድረግ ዜጎች መብቱን በትክክለኛው መንገድ እንዲረዱና እንዲጠቀሙበት የማድረግ ስራ በሰፊው እየተሰራ ይገኛል።  ይህንንም ለማሳካት ከፌዴራልና ከሁሉም ክልሎች፤ ከመንግስታና ከግል ሚዲያዎች ለተውጣጡ የኮሙኒኬሽን የስራ ኃላፊዎች፣ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ባለሙያዎች መብቱን በተመለከተ በርካታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰጥቷል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
534 ጊዜ ተነበዋል

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us