ቁጥሮች ይናገራሉ

Wednesday, 28 March 2018 12:49

በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ ገዳይ ከሚባሉት አደጋዎች የትራፊክ አደጋ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ቤተሰብ እንደወጣ ቀርቷል። ሚስት ከባሏ፣ ባል ከሚስቱ፣ ልጆች ከእናትና አባታቸው፣ ከአሳዳጊዎቻቸው በድንገት እንዲለያዩ ምክንያት ሆኗል። የብዙዎች ቤት ፈርሷል፣ ኑሮአቸው ተናግቷል። ይህ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የመጣ አስከፊ አደጋ ከፍተኛ ማህበራዊ ምስቅልቅልን በመፍጠርም ይታወቃል። 

 

በዚህ አሳሳቢና ወቅታዊ ጉዳይ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ቅንጅት በመፍጠር የህብረተሰቡን ግንዛቤን ለማሳደግ እንዲቻል የፌዴራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን አንድ አገር አቀፍ የሚዲያ ፎረም ሰሞኑን እንዲመሰረት እገዛ አድርጓል። በዚህ ፎረም ምስረታ ላይ ከቀረቡ ጥናታዊ ወረቀቶች መካከል በስታስቲክስ የተደገፈ የትራፊክ አደጋ መረጃ ከዚህ በታች ተስተናግዷል።

የትራፊክ አደጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ

    • የመንገድ ትራፊክ አደጋ ገዳይ ከሚባሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ በሽታዎች ውስጥ በ9ኛ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን አሁን ባለበት ሁኔታ መቆጣጠር ካልተቻለ በ2030 3ኛ የዓለማችን ገዳይ በሸታ ይሆናል፤
    • የዓለም ጤና ድርጅት በ2015 ባወጣው መረጃ መሰረት እድሜያቸው ከ15 እስከ 29 ዓመት ክልል ውስጥ ላሉ ሰዎች መሞት 10 ዋና ዋና ምክንያቶች ብሎ ከዘረዘራቸው ውስጥ የመንገድ ትራፊክ አደጋ አንደኛ ሆኖ እናገኘዋለን
    • የትራፊክ አደጋ አምራች ኃይሉን በመግደል የመሪነቱን ቦታ ይዟል፤

 

   • 25በመቶ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በሆስፒታል ውስጥ አልጋ ይዘው ክትትል ያደርጋሉ፤
    • እንደ ዓለም ጤና ድርጅት እ.አ.አ የ2015 ሪፖርት መሠረት፤
   • በዓለማችን ከ600 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ንብረት ይወድማል
   • በዓለማችን በዓመት ከ1 ነጥብ 24ሚሊዮን በላይ ሠዎች በመንገድ ላይ ሆነው አልያም በትራንስፖርት ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በቤታቸው ውስጥ ሀገር አማን ብለው በተቀመጡበት፣ በተኙበት ድንገት ባላሠቡት እና ባልጠበቁት ሁኔታ ህይወታቸውን ያጣሉ፤
   • ቁጥራቸው ከ20 እስከ 50 ሚሊዮን የሚደረሱት ሰዎች ደግሞ ለከባደና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።
   • አደጋው ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች በጣም የከፋ ነው
   • አነስተኛ የተሽከርካሪ ቁጥር ያላቸው የአፍሪካ ሀገራት ተጉዳቱ ሰለባ በመሆን ቀዳሚ ችግር ሆኖባቸዋል፤
   • እነዚህ ሀገሮች ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ከሚደርስባቸው የሞት አደጋ ጋር ሲነጻጸር ቁጥሩ ከፍተኛ ነው፤
   • በአለም ላይ ከሚደርሰው ሞት አደጋ 90በመቶ በእነዚህ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሀገሮች የሚድረስ ነው።
   • በተለይም አፍሪካ ካላት በጣም ዝቅተኛ ከሆነ የተሽከርካሪ ቁጥር አኳያ የሚመዘገብባት የአደጋ መጠን እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየደረሰ ነው፤
   • የመንገድ ትራፊክ አደጋ በአሁን ሰዓት በአለም ላይ አጠቃላይ ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች ውስጥ በ9ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው።


በአፍሪካ

 • በዓለም አንድ በመቶ የሚሆን የተመዘገበ የተሽከርካሪ ቁጥር ያላት
 • ከ 90 በመቶ ያላነሰ አደጋ የሚመዘገብባት፤
 • ለዓለም 16 በመቶ ሞት አስተዋፅዖ ያላት
 • ከ ዓመታዊ የምርት ገቢዋ ላይ ከ1 እስከ 3 ዓመታዊ የኢኮኖሚ ዕድገት (GDP) የሚደርስ ሀብቷን የምታጣ ናት።

 

 • እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ዳሰሳዊ ጥናታዊ መረጃ መሠረት (እ.ኤ.አ. 2013)
 • በየዓመቱ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ከ300 ሺ ያላነሱ አፍሪካውያንን ህይወት ይቀጥፋል ብሎ ግምቱን አስቀምጧል።
 • የአደጋ ቁጥሮችን ትክክለኛነት መዝግቦ መያዝ ላይ ክፍተት ስላለ ቁጥሩ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፤
 • ዕድሜያቸው ከ5 እስከ 44 የሚገኙ ሰዎች የመሞት ምክንያት በመሆን 4ኛ ደረጃን ይይዛል፤ 65 በመቶ ያህል የመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች እግረኞች ናቸው።

 

በኢትዮጵያ በ2009 ዓ.ም ብቻ


4ሺ 479 ሞት፤ በወር 373፣ በቀን 12 ዜጎቸ ህይወታቸው አልፏል።

 

 • በዓመት ከ 15 ሺህ በላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን በወር ከ1ሺ 250 በቀን ከ 42 በላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፤

 

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት በገንዘብ ሲተመን ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ደርሷል።

 

 • ከ2005 እስከ 2009 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በፖሊስ የተመዘገበ መረጃ እንደሚያሳየው 15 ሺ በላይ ዜጎች በመኪና አደጋ ህይወታቸውን ተነጥቀዋል፤
 • በ2008 ዓ.ም ከተመዘገበ 4 ሺ 352 የሞት አደጋ ውስጥ፡- 48 ነጥብ 1 በመቶ ተሳፋሪዎች፣ 43 ነጥብ 2 በመቶ እግረኞች፣ 8 ነጥብ 7 በመቶ አሽከርካሪዎች መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማል።
ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
766 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

 • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

 • Aaddvrrt5.jpg
 • adverts4.jpg
 • Advertt1.jpg
 • Advertt2.jpg
 • Advrrtt.jpg
 • Advverttt.jpg
 • Advvrt1.jpg
 • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1067 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us