በሰንደቅ ጋዜጣ 11ኛ ዓመት ቁጥር 570 ላይ “ዓይንን በብቸኝነት የሚያክም ማዕከል ስራ ጀመረ” በሚለው ዜና ዲማ የዓይን ህክምና “ማዕከል” ሳይሆን “ክሊኒክ” መሆኑ፤ የክሊኒኩ መስራቾች ዶ/ር መሠረት እጅጉ እና ዶ/ር ይልቃል አዳሙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና በምኒልክ ሆስፒታል የዓይን ህክምና ስፔሻሊስቶች መሆናቸው ተስተካክሎ እንዲነበብ፤ እንዲሁም ክሊኒኩ በብቸኝነት የሚሰጠው ጠቅላላ የዓይን ህክምናን ሳይሆን የእንባ መፍሰስ፣ የዓይን ቆብና የዓይን ዕጢ ቀዶ ህክምናን መሆኑን እንገልፃለን። በተጨማሪም በዜናው ሀገራችን ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 1 ነጥብ 8 በመቶ የዓይን ችግር አለባቸው የሚለው አገላለፅ “በአገራችን 1 ነጥብ 6 በመቶ ህዝብ የዓይነስውርነት ችግር አለበት” በሚል ተስተካክሎ እንዲነበብ በአክብሮት እንጠይቃለን። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us