መፍትሔውን ሌሎችም ቢለምዱት

በርካታ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች ዘንድሮ የበጀት እጥረት ስላጋጠመን ወጪያችንን መቀነስ አለብን በማለት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ። እየተወሰዱ ካሉት እርምጃዎች መካከል አንዱ በስብሰባ  እና በስልጠና ምክንያት ያለ አግባብ ይባክን የነበረውን ገንዘብ መቀነስ ነው። አሁን እየሰማን እና እያየን ያለነው ቀድሞ በታላላቅ ግብዣዎች ታጅበው ይካሄዱ የነበሩ ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች አሁን ግን በቆሎ እና በዳቦ ቆሎ እየተካሄዱ መሆኑን ነው። ጉድለቱ እሰየው ባያስብልም እየተወሰደ ያለው መፍትሄ ግን ጥሩ ተሞክሮ ነው። ነገር ግን ቀድሞውኑ በጀቱን በአግባቡ መጠቀም ቢቻል ኖሮ እዚህ ደረጃ ላይ ባልተደረሰ ነበር። በተለይ ከስብሰባ እና ስልጠና ጋር ተያይዞ ያለ አግባብ የሚባክን ንብረትን በተመለከተ በተደጋጋሚ ትችት ሲቀርብ ቆይቷል። አሁን ቁርጡ ሲታወቅ የተወሰደው እርምጃ ቀደም ብሎ ታስቦበት ቢሆን መልካም ነበር። ነገር ግን እያለ መቆጠብ እና አርቆ ማሰብ ካለመቻል የተነሳ አስገዳጅ ሁኔታዎች ላይ ልንደርስ ችለናል። የበጀት ጉድለቱ ሊከሰት የቻው በብዙ ምክንያቶች እንደመሆኑ መጠን በሁሉም መስክ የመፍትሔ እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል። በየምክንያቱ ከመንግስት ካዝና እየተመዘዘ እየወጣ ለግለሰቦች መጠቀሚያ የሚሆነውን የህዝብ ሃብት በአግባቡ በመጠቀም ከመሰል ችግሮች መዳን ይቻላል። ነገር ግን አሁን እየተወሰደ ያለውን እርምጃ ሳናደንቅ ማለፍ ያለብን አይመስለኝም።

 

                  አቶ አስቻለው ለማ - ከኮተቤ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us