ጽ/ቤቱ የቤት ሥራውን ይስራ

የኤች አይ ኤድስ ስርጭት ዳግመኛ እያገረሸ መሆኑ እና በአሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ሰሞኑን ተገልጿል። ለዚህ ለቫይረሱ ስርጭት ዳግም ማገርሸት እንደምክንያት እየተጠቀሰ ያለውም ለጉዳዩ የሚሰጠው ትኩረት እየቀነሰ መምጣቱ እና መዘናጋት ነው ተብሏል። በእኛ ሀገር የተለመደው ነገር አንድ ክስተት ሲከሰት የአንድ ሰሞን አጀንዳ ማድረግ ነው። ኤች አይ መከሰቱን ተከትሎ ሁሉም ሲሯሯጥ ነበር። በሱ ሣቢያ በርካታ ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች ተደርገዋል፤ አበል ተበልቷል፤ ቲሸርት እና ኮፍያ ታትሟል። ነገር ግን ይሄ ሆይ ሆይታ ከአንድ ሰሞን አጀንዳነት እና ከግለሰቦች መጠቀሚያነት አልፎ ዘላቂ መፍትሄ ሊያመጣ አልቻለም። አሁን የተሰማው ነገር ስራውን ዳግመኛ ከስር ጀምረን መስራት እንደሚያስፈልገን የሚጠቁም ነው። አሁን የሚጠብቀን ስራ ከዚህ ቀደም ከነበረውም የሚከብድ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም በፊት ስለቫይረሱ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነበር ጥረትና ትዕግስትን ሊጠይቅ ስለሚገባ ቅድመ ዝግጅቱ ሰፋ ያለ መሆን ይኖርበታል። ለዚህ ተብሎ የተቋቋመው /ቤቱም አሁን ብዙ ስራዎችን መስራት ይጠበቅበታል። ካልሆነ ግን እንደ ከዚህ ቀደሙ ብዙዎችን በቫይረስ ምክንያት ልናጣ እንችላለን። አሁን ዙሪያ ጥምጥም የምንሄድበት እና አንዱ በሌላው ላይ የሚያላክክበት ጊዜው ሳይሆን የሚመለከተው ሁሉ የየራሱን የቤት ስራ የሚሰራበት ነው።

                / አሰለፈች - ከአዋሬ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us