የኋሊት አፈፃፀሞች ይታሰብባቸው

 

አብዛኞቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ባለፉት ሶስት ወራት (ሩብ ዓመት) ያከናወኗቸውን ተግባራት በተመለከተ ሰሞኑን ሪፖርት በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እየቀረቡ ካሉት ሪፖርቶች መረዳት የቻልነው ሁሉም ማለት በሚያስችል ሁኔታ አፈፃፀማቸው አለመሳካቱን ነው የሚያመለክተው። አንዳንዶቹማ ሃምሳ በመቶ እንኳን ማከናወን አልቻሉም። የማይሰራ አይሳሳትምና ሰርተው ሳይሳካላቸው ቢቀር ልንታገሳቸው እንችል ነበር። አሁን ያለው ሁኔታ የሚያመለክተው ግን እቅድ ከማጽደቅ ሌላ የሰሩት ስራ አለመኖሩን ነው። በእነዚህ ጥቂት ወራት ውስጥ የታየው ደካማነት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ስላለመዝለቁ ምንም አይነት ማረጋገጫ አይኖርም። የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል እንዲሉ የአሁን አፈፃፀማቸውን አይቶ ቀጣዩን መገመት ትልቅ ምርምር የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም። የዚህ ድምር ውጤት ግን ልንመልሰው የማንችለውን ኪሳራ ያሸክመናል። በየአቅጣጫው መውደቅ ለበዛበት ነገር እንዲህ አይነቶቹ ድክመቶች ሲደማመሩ ውጤታቸው የከፋ ነው የሚሆነው። ለዚህ ውድቀት የየራሳቸውን አስተዋጽኦ ላለማበርከት ሁሉም በየራሳቸው ዘርፍ ጠንካራ ጥረትን ይጠይቃልና በተቻለ አቅም በቀሪዎቹ ወራት መሻሻል ያስፈልጋል። አመቱ ገና ሶስት ቀሪ ሩብ ዓመቶች ስላሉት ለመለወጥ ቆርጦ ለተነሳ ሰው የሚናቁ አይደሉም።

                          አቶ ደጀኔ - ከፒያሳ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 71 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us