ይድረስ ለሰንደቅ ጋዜጣ

ብዙ ጊዜ ልቤን የሚነኩ መጣጥፎችን ጋዜጣችሁ ላይ አነባለሁ። ምንም እንኳን በግሌ የማልስማማባቸውና የማልደግፋቸው አልፎ አልፎ ቢገጥሙኝም የጋዜጠኝነት መርሆን የተከተሉና እውነትን የሚያንፀባርቁ በተለይም በርዕሰ አንቀጻችሁ ከሰፈሩት ተጠቃሽ ላደርጋቸው የምችላቸው ብዙ የጋዜጣችሁ መጣጥፎች ምሳሌዎች አሉኝ። በአሁኑ የጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም እትማችሁ (ሰንደቅ 13ኛ ዓመት ቁጥር 635) መሪ ዜናና የርዕሰ አንቀጻችሁ ዋና ሐሳብ ያደረጋችሁትም ጉዳይ ለአብነት የሚጠቀስ ሆኖ ልቤን ቆሰቆሰውና ይህችን እንኩ አልኳችሁ።

 

እናንተ እንዳላችሁትም የክብር ዶክተር ሼኽ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ በኢትዮጵያችን በግለሰብ ደረጃ የሚመዘኑ ወይም የሚቀመጡ አይደሉም። ስለ ብሄራዊ ጥቅም ከተነሳ የብሄራዊ ጥቅማችን ዋና ገጽታና ውስጣዊ ይዘት የሕዝባችን እድገት ነው። ሕዝብ የሚያድገው በአንድ በኩል ሰርቶ መኖር ሲችል በሌላ በኩል ደግሞ አንዱ ለአንዱ ሲያስብና በሕብረት ችግርን መቋቋም ባህሉ አድርጎ ሲይዘው ነው። ባለፉት ሩብ ምዕተዓመታት በዚህ አቅጣጫ አንጸባራቂ ኮከባችን ሆነው ያልደረሱበት የሕዝብ ችግር ሜዳ፤ ጆሮአቸው ሰምቶ ያልደፈኑት የእንግልት ቀዳዳ፤ በማንም ሆነ በማን ተነግሮአቸውና ተመልክተው የሀገርን ጋሬጣ ለመንቀል ያልፈነቀሉት ድንጋይ አለ ብዬ ስለማላምን ታላቁ የብሄራዊ ጥቅማችን መከበርም አባትና ታላቅ ወንድም ናቸው። የተለያዩ ግለሰቦችን ሕይወት የታደጉባቸውን ስንክሳር ያህል የደጎሰ መጽሐፍ የሚወጣቸውን ጉዳዮች ለታሪክ ትተን የሰሞነኞቹን ለ"ቆሼ" የመናድ አደጋ ተጋላጮች በይፋ የለገሱትን 40 ሚሊዮን ብር፤ ለሶማልያ ክልል ሕዝብና በድርቅ ለተጎዱት ከብቶቻቸው መታደጊያ ያወጡትን የብዙ ሚሊዮን ብር ዘርፈ-ብዙ እርዳታና በኦሮሚያ ክልል የመንግሥትን እጅ ለሚጠባበቁ የወቅቱ ተፈናቃዮች የቸሩትን ሌላ 40 ሚሊዮን ብር እንኳን ቀንጭበን ብናወሳ "ማን እንደሳቸው" ማለታችን ይበዛ ይሆን!? ይህ ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ዘብ መቆም በራሱ ግዙፍ ተምሳሌት ነውና አምሳያውን በሌላ ግለሰብ እጅ ብናፈላልግ ከየት ይገኛል?!


እናም ከወገን ወገን ከተቆርቋሪም ተቆርቋሪ የሆኑት ብርቅዬ የዘመናችን ታላቅ የሕዝብ ባለውለታና የሀገራችን ቁርጥ ቀን ልጅ የክብር ዶክተር ሼኽ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ዛሬ በገጠማቸው ሁኔታ ከጎናቸው የማይቆም እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ሰው አይኖርምና የጋዜጣችሁን ርዕሰ አንቀጽ ታላቅ ድምፅ በየፊናችን ማስተጋባት ይኖርብናል። ስለ የክብር ዶክተር ሼኽ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ከዜና ማሰራጫዎች ለቃቅሜ የማውቀው የውቅያኖሱን በጭልፋ ዓይነት ቢሆንም እናንተም በጋዜጣችሁ "ሼኽ ሙሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ማናቸው?" ካላችሁት በላይ ሊሆኑ እንደሚችሉ አልጠራጠርም።


ስለዚህም በመልእክቴ ማጠቃለያ ዋና ሀሳብ በውጭው ዓለም ታዋቂ ጋዜጦች እንደሚያደርጉት እናንተም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት የሚኖሩ እውነተኛና አመዛዛኝ ወገኖችን ተደራሽ በሚያደርግ ሁኔታ የሕዝብ ድምጽና አስተያየት ማሰባሰቢያ መንገድና ስልት ቀይሳችሁ የርዕሰ-አንቀጻችሁን መሪ መልእክት በአንድነት ብናስተጋባ እላለሁ።


ቸሩ ፈጣሪያችንን ጩኸታችንን ይስማ!!


ከፋሲል ሳህለ 

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 70 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us