በእኛ ሀገር ስንት አይነት ሴት ነው ያለው?

ሰሞኑን ፓርላማው ሴት የመንግሥት ሠራተኞች የወሊድ ፈቃድን በተመለከተ የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አፅድቆታል። አዋጁ ሴት የመንግሥት ሠራተኞች ከወሊድ በኋላ የሚያርፉበት ጊዜ ከ60 ቀናት ወደ 90 ቀናት ከፍ እንዲል በአጠቃላይም የወሊድ እረፍቱ ከሦስት ወራት ወደ አራት ወራት ከፍ እንዲል አድርጓል። የአዋጁ መጽደቅ የሰው ልጅ ለሆነ ሁሉ የሚያስደስት ነው። በሰለጠነው ዓለም ያለውን ሁኔታ ስንመለከት የወሊድ ፈቃድ የሚሰጠው ለስድስት ወራት ነው። ይሄ ደግሞ ልጆች እስከ ስድስት ወራቸው ድረስ የእናታቸውን ጡት ብቻ እንዲጠቡ ለማድረግ ነው። በእኛ ሀገር ግን የወሊድ እረፍቱ ሦስት ወራት ሆኖ ሳለ ህፃናት እስከ ስድስት ወራቸው ድረስ የእናታቸውን ጡት ብቻ ይጥቡ እየተባለ ምክር ሲሰጥ ነበር። አሁን ግን ቢያንስ ጊዜው ከተጨመረ ይሄንን መምከሩ ብዙም ላያሳፍር ይችላል። ነገር ግን እዚህች ላይ ግራ የሚያጋባው ነገር ቢኖር በሀገራችን ስንት አይነት ሴቶች እንዳሉ ነው። አዋጁ የሚመለከተው ሴት የመንግስት ሰራተኞችን ነው ሲባል ለግል ድርጅት ሠራተኞች አይሰራም ማለት ነው። ነገር ግን በሁለቱም መስሪያ ቤቶች የሚገኙት ያው ሴቶች ሆነው ሳለ አዋጁ ለእነዚህ የማይሰራበት ሁኔታ መፈጠሩ ቅር ያሰኛል። ሁሉም ሴቶች በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ እንደማለፋቸው አገለግሎት ላይ የሚውሉ ተመሳሳይ ሕጐችን መተግበርም አስፈላጊ ይመስለኛል። ነገር ግን አሁን ያለው ሁኔታ የመንግስት ሠራተኛ ለሆኑት ሴቶች ያደላ ነው። ይሄንን ጉዳይ በጥልቀት በመመልከት ለሁሉም ሴቶች እኩል ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ ይኖር እንደሆነ ያሉትን መንገዶች ሁሉ መጠቀም ቢቻል መልካም ነበር። ነገር ግን አሁን ያለው ሁኔታ አንዷ ሰት ከሌላዋ የተለየች ናት እንዴ ያስብላል።

ወ/ሮ መሠረት ገበያው - ከሾላ

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 984 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us