ስለሰሞኑ ሁኔታ በቂ መረጃ ቢሰጠን


ሰሞኑን በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ አለመረጋጋቶች የሰዎች ህይወት እስከ ማለፍ እየደረሰ ነው። በተለይ የተማረ ዜጋን የማፍራት ትልቅ አላማ ሰንቀው በሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘንድ ችግሩ በስፋት እየተስተዋለ ይገኛል። የችግሩ መንስኤ ምንም ይሁን ምንም በተለይ ተማሪዎች በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መግባታቸው በጣም አስጨናቂ ጉዳይ ነው። ልጆች ተገቢውን እውቀት ቀስመው ይመጣሉ ብሎ የቻለውን ነገር ሁሉ አድርጎ ልጁን ለላከ ወላጅ ደግሞ እጅግ አስጨናቂ ነው። በርካታ ወላጆችም በከባድ ጭንቀት ውስጥ ነው ያሉት። በምን ሰዓት ምን ሊከሰት እንደሚችል እርግጠኛ መሆን ባለመቻላችን በከባድ ስጋት ውስጥ ነው ያለነው። ተማሪዎቹን ወደ ቤታቸው ለመመለስ ከትምህርት ገበታቸው ላይ  ማራቁ ሌላ ችግር እንዳለው በመገንዘብ እዚያው ባሉበት እንዲቆዩ ለመወሰን የተገደድን ብንኖርም ይሄንኛውም አማራጭ ሌላ ስጋት ውስጥ ከቶናል። መንግስት ከሌሎች በተለየ ሁኔታ በትምህርት ተቋማት አካባቢ እየተስተዋለ ያለው ችግር መፍትሄ እና መቋጫ እንዲኖው ጥረት ሊያደርግ ይገባል። በአሁኑ ወቅት ልጆችም ወላጆችም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ነው ያሉት። በየተቋማት ስላለው ሁኔታም ወላጆችም ሆኑ ሌላው ማህበረሰብ በቂ መረጃ እንዲያገኝ መደረግ ይኖርበታል። 

 

                           አቶ ሰኢድ - ከሳሪስ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us