ዘመቻ ብቻውን ሴቶችን አይታደግም

በሴት ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንደኛ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሰለጠነው ዓለም ላይም ይተገበራሉ። ድርጊቱ በሌሎች ሀገራት ከተተገበረ በእኛ ሀገር ቢተገበር ምን ይደንቃል ለማለት ሳይሆን፤ በእኛ ሀገር ያለው ግን እጅግ ሰብአዊነት የራቀው መሆኑ ያሳዝናል። ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበር ቅንጅት እንደገለፀው በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ብቻ ሦስት ሴቶች በአሲድ ጥቃት ደርሶባቸዋል። ይሄን መረጃ መስማት ለሰብአዊ ፍጡር እጅግ አሰቃቂ ሲሆን፤ ለሴቶች ደግሞ ተስፋ አስቆራጭ ነው። በየትኛውም ዓለም ላይ የሚገኙ ሴቶች ከድሮ ጀምሮ ለተለያዩ ጾታዊ ጥቃቶች ሲጋለጡ የኖሩ ቢሆንም በዚህ መልኩ ለዘግናኝ ጥቃት መጋለጥ ግን ለዚያውም በዚህ በሰለጠነ ዘመን፤ እጅግ አሳዛኝ ነው። ማኅበሩ በሆነ አጋጣሚ የደረሰውን መረጃ ጠቅሶ እነዚህን ሴቶች ይፋ አደረገ እንጂ በየአካባቢው እና በየቤቱ በርካታ ሴቶች ለመሰል ጥቃቶች ተጋልጠው የሚደርስላቸው ሳይኖር ተቀምጠው አሊያም ህይወታቸው አልፎ ሊሆን ይችላል።

 

የሴት ልጆች ጥቃት ሲነሳ ዋናው እና ግንባር ቀደሙ ተዋናይ ወንድ እንደመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ የመጀመሪያው ተግባር የወንዶችን አመለካከት መቀየር ነው የሚሆነው። ከወላጅ አባት እና ወንድም ጀምሮ ወንዶች ለሴት ልጆች ያላቸው የተንሻፈፈ አመለካከት እንዲቃና ማድረግ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆን አለበት። በሴቶች እና ህፃናት ላይ አተኩረው የሚሰሩ አካላትም ከስር ጀምረው ወንዶች የግንዛቤ ለውጥ እንዲያመጡ የመስራት ኃላፊነት አለባቸው። አሁን እየታየ ያለው ነገር በዓመት አንድ ጊዜ ቀኑን ጠብቆ ይሄን ያህል ሴቶች ጾታዊ ጥቃት ደርሶባቸዋል። እያሉ ሪፖርት ከማቅረብ የዘለለ ቀጣይነት ያለው ስራ ሲሰሩ አይታዩም። በእርግጥ ቀኑን አስቦ መዋሉ እና ሌሎችንም ጉዳዩን እንዲያስቡበት ማስታወሱ መልካም ቢሆንም፤ ነገር ግን በ16 ቀናት ዘመቻ ብቻ ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ለውጥ ማምጣት እና ሌሎች ሴቶችን ማዳን ከተፈለገ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን መስራት እንዲሁም ሕጉ ጠንከር በሚልበት ሁኔታ ላይ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል

/ሮ ሰላማዊት - ከፒያሳ¾

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 898 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us