በእውቀት ላይ ቁጥጥር ያስፈልጋል

 

የትራፊክ አደጋ አለም አቀፍ ገዳይ ከሚባሉት በሽታዎች ተርታ እንደሚመደብ የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል። አደጋው በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመግለፅ የሚከብድ እና ከመጠን ያለፈ ነው። የችግሩን ስፋት በመመልከትም የትራፊክ ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ ተካቶ በየትምህርት ቤቱ እንዲሰጥ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ስለሁሉም ነገር ዜጎች በቂ እውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው መደረጉ መልካምና የሚበረታታ ሃሳብ ነው። ነገር ግን እውቀት ብቻውን ለውጥ ላያመጣ ይችላል። የትራፊክ አደጋን በተመለከተ አሁን እየተስተዋለ ያለው ችግር መንስኤ በአብዛኛው የቁጥጥር እና የአሰራር ክፍተት ይመስላል። በተለይ ከመንጃ ፈቃድ አሰጣጥጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ ሲነሳ እንደነበረው በርካታ ህገ-ወጥ ስራዎች ይከናወናሉ። መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የሚያስፈልገውን ሂደት ከማጠናቀቅ ይልቅ በአጭር ጊዜ እና በቀላሉ ወረቀት ለማግኘት የማይደረጉ ነገሮች የሉም። በአንድ ወቅት በኦሮሚያ ክልል ከነበረው የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ብዙ ነገር ሲባል እንደነበረ ሁላችንም የምናስታውሰው ነው። በአሁኑ ወቅትም አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ያለው የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ሊፈተሽ ይገባዋል። ብዙዎች የመንጃ ፈቃድ ለማግኘት ገንዘብ ብቻ በቂ እንደሆነ እያሳዩ ነው የሚገኙት። እነዚህ ከስልጠና ይልቅ በገንዘብ የሚገኙ የመረጃ ፈቃዶች ደግሞ የሚያስከትሉትን ውጤት በየዕለቱ እየተመለከትን እንገኛለን። በዘርፉ ባለው የቁጥጥር ክፍተት ሳቢያ በየእለቱ በርካቶች ህይወታቸውን አጥተው፣ ጥቂት የማይባሉም ንብረታቸው ወድሞ እና ህይወታቸው ተመሰቃቅሎ ቀርቷል። ቁጥጥር መፈለግ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪይ መሆኑን በመገንዘብ በየጊዜው ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር ማድረግ ቢቻል እየደረሰ ያለውን ችግር በተወሰነ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። መማር እና መመራመር ባይከፋም ጎን ለጎን ግን ቁጥጥሩን አሰፈላጊ ነው።

                           በስልክ የተሰጠ አስተያየት 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us