ክስተቱ ሌሎችም እንዲፈተሹ ጠቋሚ ነው

 

ባለፈው ሳምንት በወጣው ጋዜጣችሁ ላይ የሳዕሊተ ምህረት ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ላይ የተከሰተውን አሳፋሪ ድርጊት አስነብባችሁናል። ከዜናው መረዳት የሚቻለው ምእመናኑ ትእግስታቸው መጠን ማለፉን እና የሚፈፀመው ድርጊት በጣም አሳፋሪ መሆኑን ነው። የዚህ ደብር ምዕመናን ታግለው አደባባይ በመውጣታቸው ያለው ችግር ታወቀ እንጂ በየቦታው ያሉ ደብሮችም ቢፈተሹ በርካታ ለማመን የሚከብዱ ምስጢራትን በውስጣቸው ይዘው ይሆናል። እንዲህ ጎልቶ አይታይ እንጂ በየትኛውም ደብር ቢኬድ ምእመናንን የሚያስከፉ በርካታ ድርጎቶች እየተስተዋሉ ናቸው። ለሌላው ህዝብ አርአያ መሆን እና ህዝቡን ማስተማር የሚገባቸው ካህናት እና የሃይማኖት አባቶች ሳይቀሩ የቤተ ክርስቲያናትን ገንዘብ እየበዘበዙ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ይነሳል። ለዚህ ደግሞ ምቹ ሁኔታን የፈጠረላቸው በአብዛኛው ከምዕመናን ለቤተክርስቲያን የሚሰጠው ገንዘብ በአንድ ወጥ በሆነ ስርዓት ከመሆን ይልቅ በባህላዊ እና በእምነት ብቻ መሆን ነው። ቤተክርስቲያናቱ ወጥ እና ግልፅ የሆነ የገንዘብ ገቢ ማድረጊያ እና ወጪ ማድረጊያ ስርዓት ተጠቃሚ ብትሆን በተወሰነ ደረጃ እንዲህ አይነቱን መስመር የሳተ እና ህገወጥ ድርጊት መከላከል የሚቻል ይመስለኛል። አሁን ያለው ነገር ግን ማን ምን እንደሰጠ ስለማይታወቅ በእምነት መመራት ብቻ ነው። ይሄ ደግሞ አንዳንድ ራስ ወዳድ ሰዎች እንዲፈጠሩ እና በምዕመናን ላይም የእምነት መሸርሸር እንዲፈጠር የማድረግ ችግር እየፈጠረ ይገኛል። አካሄዱ እጅግ ውስብስብ እና ጠለቅ ያለ ክትትልን የሚጠይቅ በመሆኑ ሙስናው እና የመልካም አስተዳደር ችግሩ ከዚህ የበለጠ ስር እየሰደደ ከመሄዱ በፊት መፍትሄ ሊፈለግለት ይገባል። ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ግን ደብሮች ዋና የሙስና ቦታዎች እንዳይሆኑ ያስጋል። በተረፈ ግን በሳአሊተ ምህረት የተነሳው ነገር ሌሎች ደብሮችም መፈተሽ እንዳለባቸው አቅጣጫ የሰጠ ነው።

                           አቶ ሰለሞን በለጠ - ከቦሌ 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 949 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us