ቆሻሻን የሚጠየፍ ትውልድ መፍጠር ይቀድማል


በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ ወጪ የሚወጣበት የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ሰሞኑን በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ሲዘገብ ሰንብቷል። ሃሳቡ የዘገየ ቢሆንም የሚደገፍ ነው። ነገር ግን ዋናው ከቆሻሻ ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው ችግር የማዕከል እጦት ነው ወይ የሚለው ሊጠና ይገባዋል። እኔ እንደሚመስለኝ ከሆነ ዋናው ችግር የቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከል እጦት ሳይሆን የግንዛቤ እጥረት ነው። ትውልድ ራሱ ቆሻሻን የሚጠየፍ አመለካከት ሊኖረው ይገባል። በአስተሳሰብ ላይ መሰራት ያለበት ስራ ሳይሰራ ማዕከል መገንባቱ ከብክነት የሚቆጠር ይመስለኛል። ይሄንን ለማለት ያስደፈረኝ ደግሞ ከዚህ ቀደም የነበረው ተሞክሮ ነው። ቀደም ባሉት ዓመታት የከተማዋን ንፅህና ለመጠበቅ ሲባል በየመንገዱ ዳርና ዳር ላይ ደረቅ ቆሻሻ የሚጣልባቸው እና ባለሁለት በር ከብረት የተሰሩ ማጠራቀሚያዎች ተተክለው እንደነበር ሁላችንም እናስታውቃለን። ነገር ግን በእነዚያ ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች ውስጥ ምን ያህል ቆሻሻ ነው የሚጣለው? ሁላችንም እንደታዘብነው ማጠራቀሚያዎቹ ውስጥ ከሚጣለው ቆሻሻ ይልቅ በማጠራቀሚያዎቹ ስር ተከምሮ የሚገኘው ቆሻሻ ይበልጥ ነበር። እነዚህ ማጠራቂሚያዎች እያሉ እነሱን አልፎ ደረቅ ቆሻሻን መንገድ ላይ ወይም የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ውስጥ መጣል የሚቀናው ማህበረሰብ ነው ያለው። ማጠራቀሚያዎቹም ምንም ያህል ጊዜ ያገልግሉ ተሰባብረው እና ተገነጣጥለው አልቀዋል።

 

በመኖሪያ ቤት ያለውን ነገርም ብናይ ብዙዎቻችን የራሳችን ቅጥር ጊቢ ጽዳት እንጂ ከበራችን ውጪ ያለው ፅዳት አያሳስበንም። ለዚህም ይመስላል ብዙዎቻችን ጨለማን ተገን አድርገን እና ሰው አየን አላየን ብለን ቆሻሻን ከበራችን ውጪ አውጥተን በአጥራችን ስር የምንጥለው። እዚህ ላይ መገንዘብ የምንችለው ችግሩ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ እጦት ሳይሆን ቆሻሻን በተመለከተ ያለን ግንዛቤ የተዛባ መሆኑ ነው። ማዕከል መገንባቱ ችግሩን በተወሰነ ደረጃ ሊቀርፈው ይችል ይሆናል እንጂ ይሄን ያህል ሙሉ ተስፋ የሚጣልበት አይመስለኝም። የሚፈለገውን ውጤት ለማግኘት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቱ ከማእከል ግንባታው ጎን ለጎን ሰፊ የሆነ ግንዛቤን መፍጠር ይጠበቅበታል።

 

                በስልክ ከአራት ኪሎ የተሰጠ አስተያየት

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 60 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us