የሸቀጦች ዋጋ ጉዳይ


በአንድ ሀገር ለሚከሰቱ ችግሮች የመጨረሻውን ዋጋ የሚከፍሉት ዜጎች ናቸው። በሀገራችንም በተደጋጋሚ ሲከሰት የምናየው ይሄው ነው። በተለይ በገበያ ላይ የሚፈጠረው የሸቀጦች ዋጋ መናር በየሰበባሰበቡ እየደጋገመ ሲያዳክመን የነበረው አሁንም እያዳከመን ያለው የመጨረሻ ተጠቃሚ የሆነውን ሸማቾች ነው። ከሰሞኑም በገበያ ላይ ያሉ ሸቀጣሸቀጦች በአጠቃላይ በሚባል መልኩ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል። ሁኔታዎችን ተከትሎ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ የተለመደ ቢሆንም አሁን እየተስተዋለ ያለው ነገር ግን ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ነው። ነጋዴዎች አንዱ ከሌላው እያየ ዋጋ ከመጨመር ውጪ ምክንያት የማያስፈልጋቸው ሆነዋል። ተጠቃውም ዋጋው በቀጣዩ ቀን ቢጨምር እንጂ አይቀንስም በሚል ግምት በተባለው ዋጋ መግዛትን ይመርጣል። ሁሉም የሚኖራቸው ዋጋ ተመሳሳይ በመሆኑ እና ሌሎች አማራጮች ስለሌሉ በተባለው ዋጋ ገዝቶ መሄዱ የተለመደ በመሆኑ ነጋዴዎችም እንደጥፋት የሚቆጥሩት አይመስልም። መንግስትም ከአንድ ሰሞን ማስፈራሪያ የዘለለ እርምጃ ሲወስድ አይታይም። በዚህ መካከል ሸማቹ የማይፈልገውን ዋጋ እየከፈለ ነው የሚገኘው። ሰሞኑን በወጣ መረጃ ደግሞ በገበያ ላይ ባሉ የክብደት መለኪያ መሣሪያዎች ላይ ከፍተኛ ጉድለት መኖሩ እና ህብረተሰቡም እያስተዋለው እንዳልሆነ የንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣን ገልጿል። ይሄንን ስንመለከት ደግሞ ሸማቹ በተለያዩ መንገዶች ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን እንገነዘባለን። ይሄን ችግር መታገሉ ከግለሰብ አቅም በላይ ስሆነ ባለስልጣኑ ከባድ ኃላፊነት አለበት።

                           ከፒያሳ - በስልክ የተሰጠ አስተያየት

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us