የጎዳና ተዳዳሪነት ሽክርክሪቱ


በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ መንገዶች ላይ የመዘዋወር ልምድ ያለው ሰው አስተውሎ ከተመለከተ በየመንገዱ ዳርና ዳር ያለ ምንም ስጋት ጎዳና ቤቴ ብለው የተደረደሩ ሰዎችን ማስተዋል ቀላል ነው። ይህ አይነቱ ችግር ቀደም ብሎም የተለመደ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው የሚገኘው። እንዲያውም ቀድሞ የጎዳና ተዳዳሪዎች አንድ ወይም ሁለት ብቻ ሆነው ነበር የሚታዩት። አሁን ግን ብዙ ቁጥር ያላቸው እና የቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች ጭምር ጎዳና ላይ ወጥተው ይታያሉ። እነዚህ ጎዳና ላይ የወጡ ሰዎችም ሴት ልጆችና ታዳጊዎችን ይዘው በጎዳና ላይ ለመኖር እየተገደዱ እናያለን። የዚህ ቤተሰብ የዛሬው ጎዳና ላይ መውጣት ብቻ ሳይሆን መታየት ያለበት አብረዋቸው ያሉት ሴት ልጆች ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውም ጭምር ነው። እነዚህ ታዳጊ ሴቶች ምንም እንኳን ከቤተሰብ ጋር ቢሆኑም በጎዳና ላይ በመገኘታቸው ብቻ ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው። በሚገጥማቸው ጥቃት እና ችግር ሳቢያ እነርሱም ነገ በዚህ አይነቱ ህይወት ውስጥ ላለማለፋቸው ምንም አይነት ዋስትና የላቸውም። በዚህ መልኩ ከቀጠለ ይህ አስከፊ ህይወት ማብቂያ የሌለው ሸክርክሪት ነው የሚሆነው። በዚህ ህይወት ውስጥ እያለፉ ያሉት ሰዎች የችግራቸው መንስኤ ምን እንደሆነ መጠናት እና ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ ይኖርበታል። ምንም አይነት እርምጃ ካልተወሰደ ግን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ችግር የሚሆንበት ጊዜ ቅርብ ነው።


አቶ አስራት ከቦሌ ክፍለ ከተማ

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 251 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us