ከገበያ ስፍራው ጎን ለጎን ሊታሰብበት የሚገባው


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለመንገድ ላይ ነጋዴዎች ክፍት የገበያ ስፍራ ሊያዘጋጅ መሆኑን ከሰሞኑ ገልጿል። እነዚህ የመንገድ ላይ ነጋዴዎች በተደጋጋሚ ችግር እያስከተሉ መሆናቸው ሲነገር ነበር። እነርሱም ስራቸውን ተቆጣጣሪዎች አዩን አላዩን እያሉ በሰቀቀን ውስጥ ሆነው ነው የሚሰሩት። በዚህ መካከል የሌላውን ሰው እንቅስቃሴም እያወኩ እነርሱም ለተለያዩ ኪሳራዎች የሚዳረጉበት ጊዜ አለ። ሁልጊዜም የምንመለከተው በራሳችን አቅጣጫ ብቻ በመሆኑ ግን ይሄንን ችግራቸውን ልንረዳላቸው አልቻልንም። ቢሮው አሁን ያሰበው ነገር ለማህበረሰቡም ሆነ ለነጋዴዎቹ የሚያዋጣ እና እጅግ ጠቃሚ ነው። እቅዱ በፍጥነት ተግባራዊ ቢደረግ ደግሞ የበለጠ ጠቃሚ ይሆን ነበር። ከዚህ እቅድ ተግባራዊነት ጋር ተያይዞ ግን የሚያሰጉን አንዳንድ ነገሮች አሉ። ከዚህ ቀደም እንደተለመደው የመደብ ቀረጥ እና የሱቅ ኪራይ እየተባለ የተለያዩ ጫናዎች የሚደረጉባቸው ከሆነ ነጋዴዎቹ በሚሸጧቸው እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ያሰጋናል። ይሄ ደግሞ በማህበረሰቡ ላይ ሌላ ችግር ሊፈጥር ይችላል። እንዲህ አይነቱ ችግር ከዚህ ቀደምም የተስተዋለ እና አሁንም እየተስተዋለ ያለ በመሆኑ ከእቅዱ ጎን ለጎን ይህን ችግር መከላከል የሚቻልበትን መንገድም አብሮ ማሰብ ያስፈልጋል። ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ግን አንዱን ለማስተካከል ሌላውን ማበላሸት ይከሰታል።

 

ታከለ ኃይሉ - ከመገናኛ

 

 


ማረሚያ


ባለፈው ሳምንት ዕትማችን የዶ/ር አቢይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን በሚመለከተው ዜና ውስጥ የዕጩዎች ድምፅ አስመልክቶ የቀረበው የቁጥር መረጃ በዘገባ ወቅት ስህተት መፈጠሩን ተረድተናል፡፡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡
የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 59 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us