የአደጋው ምክንያቶች በርካታ ናቸው

የትራፊክ አደጋ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ የበርካታ ዜጎችን ህይወት ከሚቀጥፉ ቀዳሚ በሽታዎች ተርታ የሚመደብ ነው። በቅርቡ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱትም በቀን እስከ 12 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጣሉ። ይህ እውነታ በሀገሪቱ ካለው የተሽከርካሪ ብዛት አንፃር ሲታይ ግራ የሚያጋባ ነው። ከሰው ቁጥር ያልተናነሰ ተሽከርካሪ ያለባቸው ሀገራት እንኳን እንዲህ አይነቱን አሰቃቂ አደጋ የሚያስተናግዱ አይመስልም። እርግጥ ነው አንዲት ተሽከርካሪ እንኳን የበርካታ ሰዎችን ህይወት የመቅጠፍ አቅም አላት። ዋናው እና ሊጠና የሚገባው ጉዳይ ግን ለዚህ ችግር መንስኤው ምንድን ነው? የሚለው ነው። አንድ ጊዜ አንድ ምክንያት ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ ምክንያት መደርደር ብቻውን መፍትሔ እንደማይሆን እያየነው ነው። አሽከርካሪው ኃላፊነት መውሰድ ካልቻለ ጠበቅ ያለ ህግን መተግበር ያስፈልጋል። ችግሩ ያለው ከትራፊክ ፖሊሶች ዘንድ ከሆነም እነርሱንም ጭምር ስነስርዓት የሚያስይዝ ህግ መውጣት ይኖርበታል።

 

የማይገባበት የሌለው ሙስና ይሄንንም ዘርፍ እያሽመደመደው መሆኑም ግልፅ ነው። ትራፊክ ፖሊሶችም ህግ ሲጣስ እና አሽከርካሪዎች ጥፋት ሲያጠፉ ተገቢውን ቅጣት ከመቅጣት ይልቅ በገንዘብ እየተደለሉ እንደሚያልፏቸው በተደጋጋሚ ሲነገር እንሰማለን። ይህ ማለት አሽከርካሪው በሚፈፅመው ስህተት ሳቢያ ለሚጠፋው የሰው ህይወት ያ ጥፋቱን ያለፈው ትራፊክ ፖሊስም ተጠያቂ ነው። እኔ እንደሚመስለኝ ለዚህ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎቹ ከላይ እስከ ታች የተያያዘ እና የብዙ መንስኤዎች ስብስብ ነው።

 

                              አቶ ሳህሉ ተሰማ ከቦሌ    

 

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 61 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us