መልዕክቶቹ አሰልችተውናል

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በባለ አራት ዲጂት ወደ ሞባይል ስልክ የሚላኩ አጭር የፅሁፍ መልዕክቶች በርክተዋል። ብዙ ቁጥር ያላቸው መልዕክት መላኪያዎች ከመኖራቸውም በላይ መልዕክት የሚልኩበት ድግግሞሽ እጅግ አሰልቺ ነው። በዚያ ላይ መልዕክት የሚላክበት ሰዓት የተወሰነ ባለመሆኑ ለተቀባዮቹ ምቹት እያሳጣን ይገኛል። ድርጊቱ መብትን መጋፋት እና ነፃነትን ማሳጣትም እየሆነ ነው። መልዕክቶቹ ያለፍላጎታችን ወደ ስልካችን የሚገቡ ከመሆናቸውም በላይ አንዳችም የማስተማር ወይም የማሳወቅ ፋይዳ የሌላቸው ናቸው። ሌሊት ላይ ጭምር ወደ ስልካችን በመግባት ህይወትን እስከ መበጥበጥም እየዳረጉን ይገኛሉ።

 

እነዚህ መልእክቶች የሚላኩት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በተደረገ ስምምነት እንደመሆኑ ድርጅቱ በአሰራራቸው ላይም ቁጥጥር እና ክትትል ሊያደርግባቸው ይገባል። መልእክቱ ሊሰራጭ በሚገባበት ሁኔታ እና ለሚፈልገው አካል ብቻ ተመርጦ ሊላክ በሚችልበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ይኖርበታል። መልዕክቶቹ በአብዛኛው ገቢ የማግኛ እንደመሆናቸው መጠን ኢትዮቴሌኮም የጥቅሙ ተጋሪ እንደመሆኑ በድርጊቱ ላይ ገደብ ሊያበጅ እና የእኛንም መብት ሊጠብቅልን ይገባል።

 

                             በስልክ ከመገናኛ የተሰጠ አስተያየት      

 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 971 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us