የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በሁለት ፋብሪካዎች ላይ ዲስ የማስፋፊያ ግንባታ አከናወነ

Wednesday, 20 December 2017 13:03

የሚድሮክ ሚክኖሎጂ ግሩፕ አባል ኩባንያዎች የሆኑት ዋንዛ ፈርኒሺንግ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር የማስፋፊያ ግንባታዎች ታህሳስ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ተመረቁ።

 

ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ለማስፋፊያ ግንባታ ወጪ የተደረገባቸው ሁለቱ ፋብሪካዎችና ቢሮዎቻቸው በአዲስ መልክ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው ሰሚት ፓርትነርስ ኩባንያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲከትሙ ተደርገዋል።


ዶ/ር አረጋ ይርዳው የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር በዚሁ ሥነሥርዓት ላይ ባደረጉት አጭር ንግግር ሁለቱም ኩባንያዎች ከመንግሥት ላይ በፕራይቬታይዜሽን የተገዙና ብዙም ውጤታማ ያልነበሩ፣ የፋብሪካዎቹ የማምረቻ መሣሪዎችም እጅግ ኃላቀርና ያረጁ የነበሩ መሆናቸውን አስታውሰው እነዚህን ኩባንያዎች ትርፋማ እንዲሆኑ፣ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እንዲራመዱና ተወዳዳሪነታቸው እንዲያድግ ታስቦ ለማስፋፊያ ግንባታ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ እንዲፈስባቸው መደረጉን ጠቁመዋል። በተጨማሪም ፋብሪካዎቹ የነበሩበት መሀል ከተማ ማለትም ልደታ እና ሜክሲኮ አካባቢ ለማስፋፊያ አመቺ አለመሆኑን በመገንዘብ ዘመናዊ የማስፋፊያ ፋብሪካዎቹ በሰሚት ፓርትነርስ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲከናወን መወሰኑንም ጠቁመዋል።


አቶ ኤፍሬም አበራ የዋንዛ ኩባንያ ዋና ሥራ አስኪያጅ በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ኩባንያው በአዲስአበባ ልደታ የማምረቻ ፋብሪካ፣ ጅማ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ገላን የእንጨት መቀቀያ ማዕከል አደራጅቶ በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ አመራር እየተሰጠው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መሆኑን አስታውሰዋል።


የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ምርት ፍላጎት ማደግ ጋር ተያይዞ ገበያው በውጭ ሀገር ምርቶች እየተያዘ መምጣቱን በመገንዘብ ኩባንያው በዘመኑ ቴክኖሎጂ እንዲዘመን ተወስኖ ወደሥራ መገባቱን ጠቅሰዋል። በዚህ መሠረት የዋንዛን ፋብሪካ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማደራጀት በምርት ጥራት ተወዳዳሪ እንዲሆን በባለሃብቱ በኩል ከ 134 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን፣ ለቅድመ ማምረት 346 ሺ 281 ብር ለጥሬ ዕቃዎች ወጪ በማድረግ ሙያተኛው ሙሉ በሙሉ አስተማማኝ የአመራረት ዕውቀት እንዲጨብጥ መደረጉን ተናግረዋል።


ኩባንያው እስካሁን 30 ለሚሆኑ የእንጨት ቴክኖሎጂና ሚካኒካል ኢንጂነሮች የሥራ ዕድል መፍጠሩን በቀጣይም ሙሉ በሙሉ ወደምርት ሲገባ ተጨማሪ ባለሙያዎችን እንደሚቀጥር ገልጸዋል።


የአዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ምትኩ በበኩላቸው ፋብሪካው ሰኔ 25 ቀን 1996 ዓ.ም ወደሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በብር 5 ሚሊየን የተከፈለ ካፒታል መቀላቀሉንና የፕላስቲክና የጋዝ ምርቶችን በማምረት የረዥም ጊዜ ልምድ ያለው መሆኑን አመልክተዋል።


ፋብሪካው የማስፋፊያ ሥራውን ካከናወነ በኃላ ከፕላስቲክ ምርቶቹ መካከል ለፔፕሲ መያዣ ሳጥን በ275 በመቶ፣ የአልኮልና ፍራፍሬ መያዣ ሳጥን መቶ በመቶ እና የቀለም መያዣ ባልዲዎች በ285 በመቶ ማሳደግ መቻሉን አቶ ሚካኤል ተናግረዋል። በተጨማሪም ፋብሪካው የሚመርታቸው የጋዝ እና የኦክስጅን ጋዝ ምርቶች በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉን ተከትሎ ዓመታዊ የሽያጭ መጠኑ ከ20 ሚሊየን ወደ 100 ሚሊየን ብር ማሳደግ መቻሉ ታውቋል።


ለሁለቱም ኩባንያዎች ውጤታማነት የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉት የሚድሮክ ሊቀመንበር የክብር ዶ/ር ሼህ ሙሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ እና የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው እና ሌሎች የሥራ መሪዎች በሥራ አስኪያጆቹ ተመስግነዋል።


በምረቃው ሥነሥርዓት ላይ የተገኙ የቴክኖሎጂ ግሩፑ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የፋብሪካዎቹ ደንበኞችና እንግዶች ዘመናዊ ፋብሪካዎቹን የአመራረት ሒደት ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። 

ይምረጡ
(1 ሰው መርጠዋል)
362 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 142 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us