በአዲስ አበባ 100 ሠራተኞች በሐሰተኛ የትምህርት ሰነድ መጠቀማቸውን አመኑ

Friday, 12 January 2018 16:59

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ መ/ቤቶች በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተቀጠሩ፣ ዕድገትና ሹመት ያገኙ ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲያጋልጡ በተሰጠው ቀነ ገደብ 100 ያህል ሠራተኞች ብቻ ራሳቸውን አጋለጡ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ቁጥሩ ከሚገመተው አንጻር አነስተኛ ነው ብለዋል።

 

በከተማዋ አስተዳደር በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የሚሰሩ ሠራተኞች ከህዳር 3 እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም እራሳቸውን ካጋለጡ ይቅርታ እንደሚደረግላቸው ይፋ መደረጉ ይታወሳል። በተሰጠው ቀነገደብ ራሳቸውን ያጋለጡ 100 ሠራተኞች ብቻ በመሆናቸው ጊዜው እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2010 እንዲራዘም አስገድዷል።


ከታህሳስ 30 በኋላ ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው የሚሰሩ ሠራተኞች በቀጣይ በሚወሰደው ማጣራት ከተደረሰባቸው ከስራ ከመሰናበት በተጨማሪ በወንጀልም ይከሰሳሉ ተብሏል።


በጊዜ ገደቡ እራሳቸውን ያጋለጡ ሠራተኞች ደግሞ ይቅርታ ተደርጎላቸው የትምህርት ዝግጅታቸውና ልምዳቸው ታይቶ ደሞዛቸው ሳይቀነስ በሚመጥናቸው የስራ ቦታ እንዲመደቡ ይደረጋል።


በመዲናዋ ሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ሠራተኞች በትክክለኛ የትምህርት ማስረጃ እንደሚሰሩ ለማጣራት የሁሉም ሠራተኛና አመራር ዋናውና ኮፒ ሰነዶች እንደ አዲስ መሰብሰቡም ታውቋል።


ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለጹት በመንግሥት ተቋማት የሐሰተኛ ማስረጃ ማጣራት ከተጀመረ በኋላ የሥራ መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረብ ላልተወሰነ ጊዜ መከልከሉ ታውቋል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
262 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 936 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us