አወዛጋቢውን የቀንትቻ ሊትየም-ታንታለም ማዕድንን በጋራ ለማልማት ጨረታ ወጣ

Wednesday, 07 February 2018 13:01

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ሰባ ቦሮ ወረዳ የሚገኘውን የቀንትቻ ሊትየም ማዕድን ማምረቻ በጋራ ለማልማት ፍላጎት ላላቸው ባለሀብቶች ሰሞኑን ግልጽ ጨረታ አወጣ።

ጨረታው ከጥር 15 ቀን ጀምሮ የወጣ ሲሆን እስከ ሚያዝያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።


የቀንትቻ የታንታለም ማዕድን ማምረቻ ፋብሪካ ከ25 ዓመታት በላይ በላይ በሥራ ላይ የቆየ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን የማዕድን ምርቱ ለአገሪቷ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም ከፋብሪካው የሚወጣው ኬሚካል በአካባቢና በሰዎች ላይ ብክለትና ጉዳት እያስከተለ ነው በሚል በኦሮሚያ ክልል የአካባቢ ደንና የአየር ጥበቃ ባለሥልጣን ከህዳር አጋማሽ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ እንዲታገድ ተደርጓል።


የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅና ባዮ ፊዩል ኮርፖሬሽን ችግሩ በምክክር ለመፍታት ያደረጋቸው ጥረቶች እንዳልተሳኩ ከኮርፖሬሽኑ የተገኘ መረጃ አመልክቷል።


ውዝግቡ ባልተፈታበትና ፋብሪካው ከ600 በላይ ሠራተኞቹ ጋር የሕልውና አደጋ ላይ እንዲወድቅ ያደረጉ ኃላፊዎችን ተጠያቂ ሳያደርግ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር የጋራ ልማት ጨረታ ማውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል። 

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
1400 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 1051 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us