የአድዋ ድል በአል በመኢአድ ጽ/ቤት ይከበራል

Wednesday, 28 February 2018 12:17

በይርጋ አበበ

 

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) 122ኛውን የአድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በጽ/ቤቱ እንደሚያከብር ለሰንደቅ ጋዜጣ አስታወቀ። 


የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አበበ ስለ ጉዳዩ ለሰንደቅ ጋዜጣ ሲናገሩ ‹‹በዕለቱ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል›› ያሉ ሲሆን በቅርቡ ከእስር የተፈቱ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ብለዋል። እንደ አቶ ሙሉጌታ ገለጻ መኢአድ ጥሪ ያረገላቸው ፖለቲከኞች የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና ተቀዳሚ ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር መረራ ጉዲና እና አቶ በቀለ ገርባ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አንዷለም አራጌ ናቸው። 


ከእነዚህ ፖለቲከኞች በተጨማሪም የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የፓርቲው አባላትን ጨምሮ መገናኛ ብዙሃን እና ምሁራን ታዳሚ እንደሚሆኑም አስታውቀዋል። በዝግጅቱ ላይ ስለ አድዋ ድል እና ኢትዮጵያዊነትን የሚገልጹ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚቀርቡ የገለጹት አቶ ሙሉጌታ፤ ‹‹ከእስር የተፈቱትና ጥሪ የተደረገላቸው ፖለቲከኞች ለተሰብሳቢዎች ንግግር ያደርጋሉ›› ብለዋል። የድል በአሉ የሚከበረው የፊታችን ዓርብ ዕለት ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ነው።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
2363 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 930 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us