ወባን መከላከል የሚያስችሉ የጤና ተቋማት ተደራጁ

Wednesday, 28 February 2018 12:21

በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) እና በአሜሪካ መንግሥት የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (CDC) የሚመራው፤ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የወባ መርሃ-ግብር (PMI)፤ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሲተገብረው የቆየውንና የኢትዮጵያን የጤና ተቋማት ወባን የመለየት፤ ምርመራ የማካሄድና የማከም አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረውን የዘጠኝ ዓመት መርሃ-ግብር በስኬት ተጠናቀቀ።

 

የዘርፉ ባለሙያዎች በPMI የወባ ላቦራቶሪ ምርመራ እና ክትትል ፕሮጀክት አማካይነት፤ ከ3ሺህ 500 በላይ ለሆኑ የላቦራቶሪ ባለሙያዎች አስተማማኝ የማይክሮስኮፕ አጠቃቀም ስልጠና የሰጡ ሲሆን፤ 2ሺህ 400 የጤና ክብካቤ ባለሙያዎች ደግሞ ለወባ በሽተኞች የተሻለ ህክምና መስጠት የሚያስችላቸውን ስልጠና ወስደዋል። በውጤቱም፤ ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚገኙ ከ1ሺህ በላይ የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማሻሻላቸውን በኢትዮጵያ አሜሪካ ኤምባሲ የላከልን ዜና ያስረዳል።


ከሁለት ሦስተኛ በላይ ህዝቧ በከፍተኛ ሁኔታ ለወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩባትና፤ በየዓመቱ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የወባ በሽታ ክስተቶች በሚመዘገቡባት ኢትዮጵያ፤ ወባ ቀዳሚው የጤና ስጋት ነው። ለክስተቶች ትክክለኛ እና አፋጣኝ ምርመራ እና ህክምና ማድረግ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዋነኛው መንገድ ነው።


ባለፈው አስር ዓመት፤ ኢትዮጵያ የወባ በሽታን በመዋጋት አስደናቂ ውጤት አስመስግባለች። እ.አ.አ. በ2011 ሃምሳ ዘጠኝ በመቶ (59 በመቶ) የነበረው በሽታውን በአስተማማኝ ሁኔታ በላቦራቶሪ የመለየት አቅም፤ በ2016 ወደ ዘጠና ሰባት በመቶ (97 በመቶ) የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከወባ በሽታ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የሞት መጠንን በእጅጉ እንዲቀንስ ረድቷል። እ.አ.አ. በ2012 ሁለት ሺህ (2ሺህ) ደርሶ የነበረው የሟቾች ቁጥርም በ2017 ወደ ሦስት መቶ ሰባ አራት (374) ዝቅ እንዲል ተደርጓል።


10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የወጣበት የወባ በሽታ ላቦራቶሪ መመርመሪያና መከታተያ ፕሮጀክት፤ በኢትዮጵያ በአይካፕ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ (ICAP-Columbia University) አማካይነት እ.አ.አ. ከጥቅምት 2008 እስከ የካቲት 2018 ድረስ ሲተገበር ቆይቷል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የወባ መርሃ-ግብር (PMI)ድጋፉን በመቀጠል፤ በአዲሱ የሁለተኛ ምዕራፍ ፕሮጀክት አማካይነት፤ የወባ በሽታ ስርጭትን በተሻለ ለመቆጣጠር የሚያስችል የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ፤ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተወጠነውን ሁሉንም የወባ ክስተቶች የመመርመርና የማከም ዕቅድን ያግዛል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
2339 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 944 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us