ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አንዷለም አራጌ በብሔራዊ እርቅ ጉዳይ ከአሜሪካ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ጋር ተወያዩ

Wednesday, 28 February 2018 12:24

በይርጋ አበበ

 

የአሜሪካ ኤምባሲ የፖለቲካ ክፍል ኃላፊውን ጨምሮ ከፍተኛ የኤምባሲው ባለስልጣናት በቅርቡ ከእስር ለተፈቱት ለጋዜጠኛ ለእስክንድር ነጋ እና አቶ አንዷለም አራጌ ባሳለፍነው ሰኞ በራዲሰን ብሉ ሆቴል የምሳ ግብዣ አደረገላቸው።


በጉዳዩ ላይ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጥያቄ የቀረበለት ጋዜጠኛ እስክንድር ‹‹ኤምባሲው የምሳ ግብዣ ያደረገልን ለእኔ፣ ለአንዷለም እና ለሁለት ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን ነው። በግብዣው ላይ በእኛ በኩል አራታችን ስንሆን በኤምባሲው በኩል ሶስት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ ከአሜሪካ ለጉብኝት የመጡ ሶስት አሜሪካዊያን ነበርን የታደምነው›› ያለ ሲሆን፤ ውይይቱን በተመለከተም ‹‹በብሔራዊ እርቅ ጉዳይ ውይይት ያደረግን ሲሆን አሁን አገራችን ላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መፍትሔ እንደማይሆንም ተነጋግረናል›› ብሏል።


ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አያይዞም ‹‹ለኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር ብቸኛ መፍትሔ ሰለማዊ እና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደሆነ ተነጋግረናል›› ያለ ሲሆን የአሜሪካ ኤምባሲ የኢትዮጵያ መንግስት ባወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ የአቋም ለውጥ አለማድረጉንም በውይይታቸው ላይ መነሳቱን አስታውሷል። ‹‹የኤምባሲው ተወካዮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምዕራባዊያን ዲፕሎማቶችን በጽ/ቤታቸው ሰብስበው ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ገለጻ ባደረጉበት ወቅትም አቋማቸውን ገልጸዋል›› ሲል ተናግሯል።

ይምረጡ
(0 ሰዎች መርጠዋል)
2364 ጊዜ ተነበዋል

ድርጅትዎ ያስተዋውቁ!

  • Advvrrt4.jpg

እዚህ ያስተዋውቁ!

  • Aaddvrrt5.jpg
  • adverts4.jpg
  • Advertt1.jpg
  • Advertt2.jpg
  • Advrrtt.jpg
  • Advverttt.jpg
  • Advvrt1.jpg
  • Advvrt2.jpg

 

Advvrrt4

 

 

 

 

Who's Online

We have 952 guests and no members online

Sendek Newspaper

Bole sub city behind Atlas hotel

Contact us